Xaanaan Keenya! ጣና የኛ ነዉ!

Xaanaan Keenya! ጣና የኛ ነዉ!

ጣና የአባይ መነሻ ነዉ። አባይ የኢትዮጵያ አንድነት ተምሳሌት ነዉ። ጣና የአባይ ምንጭ ነው ጉደር፥ አንገር፥ ዲዴሳ፥ ዳቡስ፥ በለስ፥ ዠማ እና የመሳስሉት ወንዞች ከኦሮሚያ፥ አማራ እና ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልሎች በመነሳት ውደ አባይ በመፍሰስ አንድ እጅግ ሀያል የሆነ፥ በዓለም ረዥሙን ወንዝ ይፈጥራሉ። አባይን! የኦሮሞ እና የአማራ ህዝብ በደም ጋብቻ እንደተሳስሩ ሁሉ! ኦሮሞና ጉምዝ ኦሮሞ እና ትግሬ፥ ጉራጌ ውዘተ በደም በጋብቻ በአንድነት እንደትሳስሩት ሁሉ! ልክ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች በአንድነት ቆመዉ ኢትዮጵያን እንደመስርቱ ሁሉ…

ዛሬ ጣና ችግር ላይ ነዉ። እምቦጭ ወሮታል። ጣና ከሌለ የአንድነታችን ምሳሌ የሆነው ታላቁ ወንዛችን አባይ ሊኖር አይችልም። የሀገራችን አንድነት እና የጥንካሬያችን ተምሳሌት የሆነዉ ታላቁ ወንዛችን አባይ እንዳይጠፋ ትናንት ሀገራችን ስትወረር በአንድነንት እንደቆምን ሁሉ ዛሬም በችግር ጊዜ በአንድነት መቆም ግድ ይለናል። በመሆኑም ክ200 በላይ የሚሆኑ የኦሮሚያ ክልል በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች “Xaanaan Keenya! ጣና የኛ ነዉ” እያሉ ጣናን ለመታደግ እየተደረገ ያለዉን ርብርብ ላይ ለመሳተፍ ወደ ባህር ዳር ጉዞ ጀምረዋል

ኢትዮጵያውያን የሚያምርብን በችግር ጊዜ አብሮ መቆም፥ መረዳዳት እና መደጋገፍ ነዉ!

Source Addisu Arega Kitessa facebook post