Tuttuqaan dhimma Finfinnee bara 2014-15 warra TPLF aangoo motummaa Fedaraalaa irraa ka’anii akka baqatan godhe.

Tuttuqaan dhimma Finfinnee bara 2014-15 warra TPLF aangoo motummaa Fedaraalaa irraa ka’anii akka baqatan godhe. Tuttuqaan motummaa nafxanyaa kanaa ammoo hundumashee xaxxaragee qillee buusuuf ta’a. Eeggadhaa!
#Finfinneen_seeranis_seenaa_dhaanis_kan_Oromooti!

#Tuttuqanii_nama_dubbisu_yartuuwwan_kun

ፎረም 65፦ የአዲስ አበባ ማንነት፣ ጥቅምና ፓለቲካ (ዶ/ር ጸጋዬ አራርሳ) #Ethiopia #Forum65


ኦሮሞ እያደረገ ያለው ትግል አባት ሀገሩን መልሶ የመረክብ እንጂ ፈራርሳ በባላ የቆመች ሀገርን መደገፍ አይደለም ቢመርህም በስኳር እያደረክ ዋጠው

ፈንፈኔ: የኦሮሞ ሀገር እምብርት
የኦሮሞ ሕዝብ በሚኖርበት ሀገር ከነመሬቱ ለመልከኛ በገባርነት የማስረከብ ተግባር በስፋት የተከናወነው ከ1890ዎቹ ብውኋላ ፥ በአፄ ምኒልክ ዘመነ መንግስት መሆኑ ይታወቃል። ይሁንና ኦሮሞ የኖረበትን መሬት በንጉሥ ተነጥቆ ለሌላ የተሰጠበት የጽሑፍ ማስረጃ በ1693 ዓ.ም ንጉስ ኢያሱ (ቀዳማዊ) በሰሜን ኢትዮጵያ የነበሩ የኢቱ ኦሮሞ ይዞታ የነበረውን ኮምኮምባ እና ሳራቆ የተባሉትን ቦታዎች እንዲሁም ኤዶ የሚባሉ ኦሮሞ ጎሣዎችን ይዞታ ለአንድ ገዳም ማደሪያነት የሰጡበት ማስረጃ ነው።

ማዕከላዊውና ደጋማው የኢትዮጵያ ክፍሎች ከጥንት ጀምሮ የኦሮሞ ሕዝብ ሰፍሮ የሚኖርባቸው እንደሆነ ብዙ የታሪክ ፀሐፍት ያረጋገጡት ዕውነታ ነው። ይህም የኦሮሞ አሰፋፈር ከደቡብ የኢትዮጵያ ጫፍ ማዕከላዊውን የሃገሪቱን ክፍል አልፎ እስከ ሰሜን አጋማሽ ድረስ የሚዘልቅ ስለነበረ ‪#‎ፊንፊኔንምየሚያጠቃልል‬ ነው። ለዚህም ማረጋገጫ ሊሆኑ ከሚችሉ ሰነዶች በመጀመሪያ ደረጃ ጄ. ሉዊ ክራፕፍ በተባሉ ጀርመናዊ ሚሲዮናዊና ሀገር አሳሽ የተፃፈውን እናገኛለን።

ሉዊ ክራፕፍ በ1839 ዓ.ም በጥርና በየካቲት ወራት ንጉስ ሣህለስላሴ ከአንኮበር ተነስተው በስተ ደቡብ ወደ ሚገኙ የኦሮሞ መሬቶች ባደረጉት ተደጋጋሚ ዘመቻዎች አብሮ እንደነበርና ከእርሱም ሌላ ኤም ሮሽ የተባለ ሃገር አሳሽም አብሮአቸው እንደነበር እማኝነቱን የሰጠ ሲሆን ፥ ወታደራዊ ዘመቻ የተካሄደባቸውን የኦሮሞ አከባቢዎችንና ጎሳዎችንም ሲዘረዝር አቢቹ ፥ ወበሪ ፥ ገላን ፥ ጉንቢቹ፥ ጉላሌ ፥ ፈንፈኔ ፥ ሙሎ-ፈርዳ፥ ሜታ ሮቢ ፥ ዋገዲን ጨምሮ ይጠቅሳል።

በዚህ ወቅት ፥ ኦሮሞ በራሱ ሥርዓትና ባህል እየተዳደረ ከአንጎላላ ጀምሮ በስተደቡብና በስተድቡብ ምዕራብ ባሉት አካባቢዎች ይኖር ነበር። ከእነዚህም መካከል አንዱ የአዲስ አበባና የአካባቢዋ የጥንት መጠሪያዋ ‪#‎ፈንፊኔ‬ እንደነበር የክራፕፍ መጽሃፍ የጽሑፍ ማስረጃ ነው።

አፄ ሚንልክ ማረፊያቸውን ከእንጦጦ በላይ ከማድረጋቸዉ በፊት በመስከረም 1868 ዓ.ም በፈንፊኔ አከባቢ ካቶሊክ ሚሲዮኖች “‪#‎የፊንፊኔ_ሚሲዮን‬” በሚል መጠሪያ ቤተክርስቲያንና የዕምነት ማስፋፊያ ጣቢያዎችን ከፍተው ሲንቀሳቀሱ እንደነበር የወቅቱ የፊንፊኔ ካቶሊክ ሚሲዮን ጣቢያ ሀላፊ አባ ማስያስ [Missione di Finfinni, Da un disegno di Monsignor Luigi Lasseirre ] ከነ ጣቢያው ፎቶ ጽፈዋል። ፊንፊኔ ቀደም ሲል በሚሲዮናውያን በአካባቢው መስፈር ምክንያት በመልማትዋ ምኒሊክ መቀመጫውን ወደ አካባቢው እንዲያዛውር በዋነኝነት እንደገፋፍው ተጠቅሱአል። በዚህ ወቅት በአካባቢው የነበሩ ኦሮሞዎች ላይ በአፄ ምንሊክ ወረራ የደረሰውን ጥፋት እና የነበረዉን ሁኔታ እነዚሁ ሚሲዮናዊያን መዝግበዉታል።

በቤተክርስቲያኒቷ ታሪክ መሠረት እኚህ ሚሲዮናዉያን በመስከረም 11 ቀን 1868 ዓ.ም የደረሱ ሲሆን በአካባቢዉ የነበረዉ የኦሮሞ ሕዝብ ወንድማዊ የሆነ ድጋፍ ስለሰጣቸው እዚያ እንደ ደራሱ አንድንድ ቤቶች መሥራት ጀመሩ። ፊንፊኔ በወቅቱ የጉላሌ ጎሳዎች የሚበዙባት የኦሮሞ እምብርት እንደ ነበረችም ተጽፎአል።

ለሚኒልክ ከእንጦጦ ወደ ፊንፊኔ መውረድና ለአዲስ አበባ የንጉሱ መቀመጫነት መመረጥ ዋንኛ ምክንያት የፊንፊኔ ካቶሊክ ሚሲዮን ተመስርቶ የአካባቢው በተሻለ ሁኔታ በካቶሊካዊያኑ መልማት እንደሆነ የሚገልጹ አሉ። ዶ/ር ተወልደ ትኩእ እንደጻፈው

“…ፊንፊኔ አካባቢ 10 ኪ ሜ ርዝመት ያለው መሬት … ተሰጥቶአቸው ቤትና ቤተክርስቲያን ሰርተው ይኖሩ ነበር። … ይህ ሁኔታ አዲስ አበባ በጣሊያን ዜጎች የተቆረቆረች ከተማ ብለው እንዲኮሩባት ምክንያት ሆኖአቸው ነበረ:። የተቆረቆረችውም በ1868 ዓ.ም ነበረ። ”

የዛሬይቷ አዲስ አበባ የጥንቷ ‪#‎ፊንፊኔ‬ በአንድ በኩል የፊንፊኔ ካቶሊክ ሚሲዮን ተመስርቶ በተሻለ ሁኔታ መልማቷ በሌላ በኩል ደግሞ በተፈጥሮዋ በፍልውሃ የታደለች እና አካባቢዋን ለመቃኘት የሚያስችሉ እንደ እንጦጦ ያሉ ከፍታዎች የሚገኙባት መሆኗ በመሃል የቱለማ-ኦሮሞ ምድር ያላንዳች ተወዳዳሪ እንድትከትም አድርጓታል። እንደዛሬ በህንጻዎች ከመሸፈኗ በፊት የፊንፊኔ ፍልውኃ ደመና መሳይ እንፍሎትን ከመሃል ምድር ወደ አየር በመልቀቅ ለአካባቢዋ ከርቀት የሚታይ ማራኪ ውበት የሚሰጣት ነበር።

ምኒልክ ኦሮሞዎች ይጠቀሙባቸው የነበሩትን ማህበራዊ ሥርዓችን ማፍረስ አንዱና ዋንኛ ተግባራቸው ስለነበር በፊንፊኔ ከፍታ ቦታ ባለውና በጉለሌ መሰብሰቢያ ሥፍራ/ አደባባይ ላይ የራሳቸውን ቤት አሰርተዋል። ዛሬ ቤተ መንግሥት ተብሎ የሚጠራው ሥፍራ ዳለቲ በመባል የሚታወቅ ነበር ፥ በዚሁ ዳለቲ በሚባል ስፈራ አፄ ምኒልክ የፍልውሃን ፈዋሽነት ሰምተው ወደ አካባቢው ብቅ ብለው በነበሩበት ጊዜ ድንኳናቸውን አስተከሉ ፥

አንድ ቀን አፄ ምኒልክ ፍልውሃን ታጥበው ወደ ድንዃናቸው እንደተመለሱ ባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ በድንዃናቸው በር ወደ ውጭ ሲያዩ በመንዝ አይተው የማያውቁትን አበባ ያያሉ ፥ ከዚያም ለባለቤታቸው#አዲስ_አበባ እንዳዩና ቦታው ውብ መሆኑን በዚያም የተነሳ በሥፍራው ቤት መሥራት መፈለጋቸውን ነገሩኣቸው ፥ አፄ ሚኒልክም በ1887 በዳለቲ ለይ ቤት ሰሩላቸው ፥ የጥንቷ ፊንፊኔም በአጼ ሚኒልክ ወራሪ ሰራዊት ተጥለቀለቀች ፥ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ፊንፊኔ – አዲስ አበባ መባል ጀመረች። የህዝቦችን ታሪክ ፥ ቋንቋና ባህል ብቻ ሳይሆን የአካባቢዎችንም ነባር ስያሜዎች ለውጥ አንድ ተብሎ ተጀመረ።

የጥንቷ ፊንፊኔ ከነ አካባቢዋ ባህላዊ ህይወትና ታሪክ ጭምር ትናንት በመጡ ወገኖች ተለወጠች ፥ የክልሉ ማህበራዊ ትስስሩም ተናጋ ፥ ይህንን በማስመልከት በጊዜ የነበሩ የኦሮሞ ልጆች ያሰሙ የነበሩት እንጉርጉሮ ፥ ሀበሾች የህዝቡን ማህበራዊና ባህላዊ ሥር እንዴት እንደቆረጡ የሚያሳይ ነው።

Inxooxxoo dhaabbatanii
Caffee gadi ilaaluun hafe
Finfinnee loon geessanii
Hora obaasuun hafe
Tullu Daalatti irratti
Yaa’iin Gullallee hafe
Gafarsatti dabranii
Qoraan cabsuunis hafe
Hurufa Boombii irratti
Jabbilee yaasuun hafe
Bara jarri dhufan
Loon keenyas ni dhumani
Erga ‪#‎Mashashaan‬ dhufe
Birmadummaanis hafe.

‪#‎ትርጉም‬:-

እንጦጦ ላይ ሆኖ
ለምለሙን መስክ ወደታች ማየቱ ቀረ።
ከብቶቹን ፊንፊኔ ወስዶ
ሆራ ማጠጣቱ ቀረ።
በዳለቲ ላይ
የጉለሌዎች መሰብሰብ ቀረ።
ገፈርሳ ሄዶ
እንጨት መስበሩም ቀረ።
በሁሩፋ ቦምቢ ላይ
ጥጆቹን ማገዱ ቀረ።
ሰዎቹ እንደመጡ
ከብቶቻችንም አለቁ ፥
‪#‎መሸሻ‬ ከመጣ ወዲህ
የኛ ነፃነት ቀረ።

እርግጥም መሸሻ (አቢሲኒያውያንን የሚወክል አጠራር) እንደመጣ የኦሮሞ ህዝብ ነፃነት አበቃ።

የኦሮሞ ህዝብ በወራሪ ሰራዊት የህልውናው መሰረት የሆነውን መሬቱን በኋይል ከተነጠቀና በፍፁም ገባርነት ሥር እንዲወድቅ ከተደረገ በኋላ ፥ ለዚህ አስከፊ ተግባር ሕጋዊ መሠረትና ድጋፍ ለመስጠት ሲባል በ1907 ዓ.ም የመሬት አዋጅ (Land Charter) ወጣ። የአዋጁ ዋና ይዘትም በከተሞች አካባቢ በተለይም በፊንፊኔ የመሬት ባለቤት ለመሆን የመሬት ካርታ ግዴታ መሆኑን የሚደነግግ ሲሆን ፥ በአዋጁ መሠረት “የመሃንዲስ ሥዕል” በመንግሥት ያልተሰጠው [ለሺህ አመታት በመሬቱ ላይ የነበረውንም ህዝብ ጨምሮ] የመሬት ባለቤት ሊሆን እንደማይችል የሚደነግግ ነው። እንዲሁም አብዛኞቹ ታጣቂ ነፍጠኞች ህዞቦችን በመውረራቸው ፥ ህይዎትን በማጥፋታቸው ፥ ንብረት በማውደማቸው ፥ በመንግሥታችው አቀራረብ “ሀገር በማቅናታቸው” የመሬት ስጦታ ሊበረከትላቸው እንደሚገባ ይደነግጋል ።

ይህ አንሶ በጊዜው የነበረው የግብር አከፋፈል ሁኔታ ከወርቅ እስከ ቤት እንስሳተና ቁሳቁስ ድረስ ስለነበር ሥርዓቱ ህዝቡን ክፉኛ አደሀይቶታል። በዚህ በዘር ልዩነት ላይ በተመሠረተው የኢኮኖሚ መርሆኣችው በመደገፍ ከሰሜን ያለስባሪ ሳንቲም ወዳ ኦሮሚያ የጎረፉ ሀበሾች በመሃል አዲስ አበባ የትላልቅ ቪላዎች ፥ አፓርታማዎችና ፥ ትላልቅ የንግድ ድርጅቶች ባለንብረት ሊሆኑ ችለዋል።

የመሬት ባለቤትነት የካርታ ዕደላ ጣሊያን ፊንፊኔን ከመያዙ [ከ 1934] በፊት የተጠናቀቀ ሲሆን በካርታው ምክንያት የከተማው እምብርት በንጉሱ ፥ በወቅቱ በነበሩት ገዢዎችና የጦር ሠራዊት በመያዙ የትህምርት ፥ የሆስፒታል ፥ የንግድ ማዕከሎችና ሌሎች አገልግሎቶች ከሚገኙበት አከባቢዎች ኦሮሞው ተገፍቶ እንዲርቅ በማድረግ በአዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች መሃል የኦሮሞ ቁጥር አናሳ እንዲሆን ተደረጓል።

በተለያዩ ጊዜያት የከተሞችና የቦታ ስሞች ጥንታዊ መጠሪያም እንዲቀየር ተደረጓል ፥ ከነዚም ውስጥ ጥቂቶቹ እንደሚከተለው ቀርበዋል :-

Daalattii (ዳላቲ) =============> አረት ኪሎ
Doobbii (ዶቢ) ==============> ቀጨኔ
Muujjaa (ሙጃ) =============> ሽሮ ሜዳ
Garbii (ገርቢ) ===============> ሰንጋ ተራ
Golboo (ጎልቦ) ==============> ቄራ, ቂርቆስ
Calcalii (ጨልጨሊ) ===========> ሳር ቤቶች
Eekka (ኤካ) ================> የካ
Roobii (ሮቢ) ===============> ንፋስ ስልክ

Hurufa Boombi (ሁሩፋ ቦንቢ) ==> ጃንሜዳ
Malkaa Daabbu (መልካ ዳቡ) ===> ቸርቺል ጎዳና
Caffee Tumaa (ጨፌ ቱማ) =====> ስድስት ኪሎ
Caffee Aannanii (ጨፌ ኣናኒ) ===> ሜክሲኮ
Baddaa Ejersaa (በዳ ኤጄርሳ) ===> ራስ ካሳ ሰፈር

Birbirsa Gooro (ቢርቢርሳ ጎሮ) ======> ፒያሳ
Agmsa (አገምሳ) ===============> መርካቶ
Qarsaa (ቀርሳ) ================> ካዛንቺስ

Daniel Daba