The Somali parliament Vs the Ethiopian parliament.

The Somali parliament Vs the Ethiopian parliament.

The Somali Lawmakers voted 140- 0 to reverse the 2 year term extension for president Formajo.
Can anybody remember the vote of Ethiopian parliament to extend the term in office for the PM of Ethiopia aka Rooba? It must be the opposite 0- 140.
700

ሽሬ የመንግስታት ፍጻሜ።
ታሪክ እንደምያስተምረን የWaterloo ቅሌት የናፖሊዮን ጦር በፈረንሳይ፣ በእንግሊዝና በፕሩሲያ ጥምር ጦር ለመጨረሻ ጊዜ የተሸነፈበትና ናፖሊዮን ከሥልጣን የተወገደበት ወሳኝ ጦርነት ነበር።
 
በእኛም አገር የሽሬው የWaterloo ዓይነት ቅሌት የተፈጸመዉ የቀድሞ የኢትዮጵያ ጦር (604ኛ ኮር) በትግራዩ ወያኔ፣ በኢህድን እና ዛሬ ወዳጅ መስላ በቀረበችዉ በኤርትሪያዉ ሻቢያ የጥምር ጦር የተሸነፈበትና ኮ/ል መንግስቱ ከሥልጣን የተወገደበት ወሳኝ ጦርነት ነዉ። የደርግ መንግስት የወደቀባቸዉን በርካታ ምክንያቶችን መዘርዘር ቢቻልም ከዚህ ርዕስ ጋር የሚሄዱትን አንዳንድ ነጥቦችን እናንሳ።
 
በሰሜኑ የአገራችን ከፍል በኤርትሪያና በትግራይ በምሥራቁና በምዕራቡ ክፍል በኦነግ የሚካሄደዉ ጦርነት በመራዘሙ ምክንያት የጦሩ የመዋጋት መንፈስ ከጊዜ ወደ ጊዜ ማሽቆልቆሉ ለደርግ መንግስት ዉድቀት ከምክንያቶቹ አንዱ ነበር። ሠራዊቱ ከተራ ወታደር እስከ ጄኔራሎች ጦርነትን ተሰላችተዉ ነበር። ለምሳሌ ብ/ጄ ታሪኩ አይኔ በትግራዩ ጦርነት ከተሰላቸ በኋላ ከአለቆቹ ጋር በነበረዉ አለመግባባት የተነሳ እንደ መቀጣጫ የናደዉ ዕዝ አድርገዉ ወደ ናቅፋ ግንባር ይላካል። ብዙም ሳይቆዩ ጄኔራሉ ለሕክምና አስመራ እያሉ ሻቢያ በህዳር ወር 1980 በአፋቤት ግንባር በወሰደዉ ማጥቃት በወገን ላይ ከፍተኛ ዉድቀት ደርሷል። ጄ/ል ታሪኩም ሌሎች ጥፋቶች ተጨማምረዉ በሚመሩት ጦር ፊት ተረሸነ። ብ/ጄ ከበደ ጋሼ በአስመራ ዙሪያ የመክት ዕዝ አዛዝ የያዘዉን ቀጠና በሚገባ አልመራም በማለት 35 ዓመት የኢትዮጵያን ሠራዊት ያገለገሉትን ጄኔራል በሚያዙት ጦር ፊት ማዕረጉ ተገፎ ያለ ጡረታ ከሠራዊቱ እንድሰናበት ተደረገ። ያም እርምጃ በጦሩም ሆነ በሌሎች ጄኔራሎች ዘንድ በአንድ
 
በኩል ቁጣን በሌላ በኩል ፍርሃትን አስከተለ። ያልሆነዉን እንደሆነ አድርጎ የዉሸት ሪፖርት ማቅረብ የአዛዦችም ሆነ የካድሬዎች የዕለት ተዕለት ሥራ ሆነ።
የኢትዮጵያን ችግር ለመፍታት ጦርነት መፍትሔ እንዳልሆነ የተገነዘቡት የተወሰኑ ጄኔራሎች በ1981 በመፈንቅለ መንግስት ኮ/ል መንግስቱን ካስወገዱ በኋላ ከሻቢያም ሆነ ከወያኔ ጋር ችግሮችን በድርድር ለመፍታት የነበረዉም ተስፈ መፈንቅለ መንግስቱ በመክሸፉ አልተሳካም። በዚህም ምክንያት አገሪቷ ያላት ምርጥ ጄኔራሎች በሙሉ በአንድ ሌሊት ተረሸኑ።
 
ፕሬዚዳንቱም ከዚያ በኋላ በሚቀርብለት የዉሸት ሪፖርት ላይ በመመርኮዝ ሠራዊታችን እነዚህን ቅጥረኛ ወንበዴዎች በየጋራዉና በየሸንተረሩ አሳዶ ድባቅ እየመታ ነዉ እያለ ልክ እንደ ዛሬዉ በመግለጫ ሕዝቡን ያሰለች ነበር። መንግስቱም ሲቀርብለት የነበረዉ ሪፖርት በሙሉ ዉሸት መሆኑን ከተረዳ በኋላ የኢሠፓ ማዕከላዊ ኮሚቴን አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቶ «ጓዶች፣ የትግራይና የኤርትሪያ ወንበዴዎች ባደረጉት ስብሰባ አጥፍቶ መጥፈት ነዉ ብለዋል። ይጥፉ ወይስ እንጥፋ ነዉ ጥያቄዉ………… ይኸ አደገኛ ፎርስ ነዉ ጓዶች!! በፍጥነት መጥፋት አለበት። ይህ ገበሬ ባለመሬት እንዳላደረግነዉ ሁሉ፣ ዛሬ በአክሱም፣ በአድዋ፣ በሽሬ ወዘተርፈ እንደጠላት ጦር ሠራዊታችንን እንደ አንበጣ እየተገተገዉ ነው» በማለት በከፍተኛ ቁጭት ተናግሮአል። ዛሬም እነዚህን የኦነግ ሸኔ ሽፍቶችን በ15 ቀን አመድ እናደርጋቸዋለን ሲባል የተባለበት የአነጋገር ስታል እንኳን አልተቀየረም።
 
ዛሬም ቢሆን በተመሳሳይ ሁኔታ ወይም ከዚያም በበለጠ መልኩና በተደጋጋሚ ጁንታዉ መደምሰሱንና ዱቄት ሆኖ በአየር ላይ መበተኑን መግለጫ ይሰጣል። ትንሽ ቆይተዉ ደግሞ ዱቄት ሆኖ የተበተነዉን ጁንታ ወይም ሸኔን ቴሮሪስት ብሎ ይሰይማል።
ኮ/ል መንግስቱ የኢትዮጵያ ችግር ከጦርነት ይልቅ በሰላማዊ መንገድ የመፍታት አማራጭ ያቀረቡትን የጦር ጄኔራሎችን እንደ ፈሪ በመፈረጅ «አንድ ጥይትና አንድ ሰዉ እስከሚቀር» በሚለዉ ግትር ሃሣብ ገፋበት። ችግሮች በድርድርና በብሔራዊ እርቅ እንድፈቱ ሃሣብ ያቀረቡ ሁሉ በጠላትነት ተፈረጁ። መንግስቱም ከዚያ በኋለ በወታደራዊ ብቃታቸዉ ሳይሆን ለፓርቲያቸዉ ታማኝ የሆኑትን እንደነ ለገሠ አስፋዉን የትግራይ ክ/ሀገር እንደራሴና የሦስተኛ አብዮታዊ ሠራዊ አዛዥ አድርጎ ወደ መቀሌ ተላከ። ለማነጻጸ እንደዛሬዉ ዶክተር ሙሉ ነጋ ማለት ነዉ። ረጅሙን ታርክ ለማሳጠር፣ ለገሰ አስፋዉም ጄኔራሎቹ ወታደራዊ ልምዳቸዉንና ችሎታቸዉን እንዳይጠቀሙ እንቅፋት በመሆኑ በሠራዊቱ ላይ ከፍተኛ ሽንፋት ደረሰ። የ604ኛ ኮር በሽሬ መደምሰስ የ2ኛ አብዮታዊ ሠራዊትም ተስፋ እንዲቆርጥ አደረገ። የሽሬ ዉድቀትም ለደርግ መንግስት ዉድቅት ዋነኛዉ ምክንያት ሆነ። የአሁኑም መንግስት ችግሮችን ከሁሉም ተቃዋሚ ኃይሎች ጋር በድርድር ፖለቲካዊ መፍትሔ ካልፈለገ ዳግማዊ የሽሬዉ የWaterloo ቅሌት ሊያጋጥመዉ ይችላል።
 
ዛሬም ቢሆን ገና ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት ጀምሮ የተቃወሙትን የጁንታ ደጋፊ ብሎ የማሸማቀቅ ሁኔታ ይታያል። ልደቱ አያሌዉ በዚህ ከተወነጀሉት አንዱ ፖለቲከኛ ናቸዉ። ጀዋር መሃመድ ገና ጦርነቱ ሳይጀመር ይኸ የጦርነት ከበሮ መምታት በሁለቱም በኩል ቆሞ ችግሮች በዉይይት እንዲፈቱ ካልተደረገ አገሪቷ የመፍረስ አደጋ እንደሚያጋጥማት በግልጽ ቋንቋ ነግሮአቸዋል።
 
ዛሬም ቢሆን በድሮዉ የተሳሳተ መንገድ የቁልቁለት ጉዞ ጀምረናል። ብዙ ሕይወትና ንብረት ሳይባክን አስቸኳይ ፖለቲካዊ መፍትሔ እንደ መፈለግ ፈንታ ዛሬም እንደ ቀድሞዉ ተቃዋሚን በአሸባሪነት ለመፈረጅ እየተጣደፍን ነዉ። የዓለም መንግስታት የሚያቀርቡትን የዕርቅ መንገድ እያጣጣልን አገሪቷ ተደርጎ በማይታወቅ ሁኔታ አለም አቀፋዊ የፖለቲካ ኪሳራ እንዲደርስባት እየተደረገ ነዉ።
የመንግስት ካድሬዎችና የአሃዳዊዉ ሥርዓት «የግፋ በለዉ» የጦርነት ከበሮ ወደባሰዉ የሰዉ እልቂትና የኢኮኖሚ ወድቀት እያመራን እንጂ ጦርነት መፍትሔ አይሆንም።


ኢህአዴግ the father.

ከሽብርተኛ ድርጂት ጋር የተገናኘ፣ ያወራ ወይም ቡና ቤት ቁጭ ብሎ ሻይ ቡና ያለ በሽብርተኝነት ይፈረጃል።

ኢህአዴግ the son.

ከሽብርተኛ ድርጂቶች ጋር ትብብር ወይም ትስስር ወይም የሃሣብና የተግባር ዝምድና ያላቸዉ ሌሎች ድርጂቶች ወይም ግለሰቦች በሽብርተኝነት ይጠየቃሉ።