Stop killing Wolaita!

Stop killing Wolaita!

ከኦሮሞ ቄሮ ለወላይታና ጭቁን ያገራችን ህዝቦች በሙሉ የተላለፈ ጥሪ።
KMN:-Aug. 11/2020
=================
እንደምናውቀቅው ይህች ሀገር ከጥንት ጀምሮ የተመሰረተችው በብሄር ብሄረሰቦች ፍላጎት ሳይሆን፣ በአንድ ብሄር የበላይነት ላይ ነው። ከአንዱ ብሄር ማንነትና ክብር ቀምታ፣ ሌላውን ብሄር ደግሞ ቱገዢና ተላላኪ አድርጋ፣ ለአንድ ልጇ ክብር በመስጠት፣ ለአንዱ ደግሞ ባዳ ሆና ለሮሮና ለእንግልት እየዳረገች ዛሬ ደርሳለች። እንደ ብሄር የኦሮሞ ህዝብ በገዛ ሃገሩ ላይ ሁለተኛ ዜጋ ሆኖ ሲታይ ነበር። ከአመት አመት እየጠቀ እንደ ክረምትና በጋ ሲፈራረቅበት የነበረና ያለውን፣ በነፍጠኛ ስረዓት የሚደርስበትን ደባና እሮሮ ማገባደጃውን እንዲያገኝ ለማድረግ እየታገለ ዛሬ ላይ ደርሷል።

በታሪክ ውስጥ በተለያዩ ግዜያት፣ የኦሮሞ ህዝብ ይህችን ሀገር የጀግኖቹን ህይወት ሰውቶበት ከውድቀት ሲታደጋት የኖረ ቢሆንም፣ ሲመሯት የነበሩትና ያሉት መንግስታት ግን ባህሉን ማጥፋት፣ ታሪኩን መካድ እና ቋንቋውን በመቅበር እና ክብሩን በመቀማት ውለታውን ሲመልሱ ቆይቷል።

የኦሮሞ እና የሌሎች የሀገራችን ጭቁን ህዝቦች የትግል ታሪክ ተመሳሳይ ሲሆን፣ ኦሮሞ ላይ ሲደርስ የነበረው ግፍ ሁሉ በወላይታ፣ ሲዳማ፣ ቅማንት፣ ሶምሌ፣ አፋር፣ ጉሙዝ፣ አኟክ እና ሌሎች ወንድሞቻችን ላይም ሲደርስ የነበር እና አሁንም የቀጠለ መሆኑን ራሳችሁም ምስክሮች ናችሁ።

በአሁኑ ጊዜም የኦሮሞ ህዝብ፣ አፉን ማር ተቀብቶ ህዝባችንን እየጨቆነ ካለው መንግስት ጋር ተናንቆ ይገኛል። ወያኔን በትግል እንደ ጣለው ሁሉ፣ የነፍጠኛን ስርዓት ለመመለስ የሚታትረውን ብልጥግናን አፍርሶ በብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች እኩልነት ላይ የተመሰረተችን ኢትዮጵያ ለመገንባት በትግል ላይ ይገኛል።

ብልጥግና ከሚታወቅበት የነፍጠኝነት ምልክቶች አንዱ፣ ህዝቦች የራሳቸውን ክልል ለመመስረት የሚያቀርቡትን ጥያቄ፣ ለማስተናገድ ፍላጎት የሌለው እና በተቃራኒው ደግሞ ህብረ ብሄራዊ ፌድራሊዝሙን በማፍረስ አንድ ቋንቋ እና ባህል ላይ የተመሰረተችን ሀገር ለመገንባት ደፋ ቀና እያለ መሆኑ ነው።

በአሁኑ ጊዜ፣ የወላይታ ሕዝብ እየጠየቀ ያለው ጥያቄ ህጋዊና ትክክል ነው። ይህ መንግስት የወላታ ሕዝብ ለጠየቀው የመብት ጥያቄ መልስ መስጠት ትቶ፣ በሰላማዊ ሕዝብ ላይ የታጠቀ ሃይል ማዝመት ፍፁም ተቀባይነት የለውም። የሕዝብን ጥያቄ በአፈሙዝ ለማፈን መጣር፣ የሀገሪቷን ህግ የሚጥስ ብቻ ሳይሆን አምባገነንነት ነው። ይህ መንግስት ሕዝቦች ለጠየቁት የመብት ጥያቄ መልስ እስኪያገኙ ድረስ ለግድያ እና ለእስራት እንደማይንበረከኩ ማወቅ ይናርበታል።

ውድ የወላታ ሕዝቦች፣ ውድ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች፣
በአሁኑ ጊዜ እኛ ኦሮሞዎች ይህንን የነፍጠኛ ስርዓት ከራሳችን ላይ ለመጣል መራራ ትግል በማድረግ ላይ እንገኛለን። እንቁ የሆነውን አርቲስታችን ሀጫሉ ሁንዴሳ ገድለው፣ እንደነ ጀዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ፣ ሀምዛ ቦረና፣ አብዲ ረጋሳ፣ ዶ/ር ሽጉጥ ገለታ እና ሌሎች የኦሮሞ ምሁራን ፖለቲከኞችን በእስር ቤት ውስጥ እያሰቃዩብን ይገኛል። በመላው ኦሮሚያም የጅምላ እስራት ቀጥሏል። የብዙ ብሔር ብሔረሰቦች ድምፅ የሆነውን የOMN ሚዲያ ዘግተው፣ ሰራተኞቹን አስረው ቤተሰቦቻቸውን ጭምር እያንገላቱ ይገኛሉ።

በትላንትናው እሉትም፣ የወላታ ሕዝብ ያሉትን ምሁራን በውይይት ላይ እያሉ፣ በመንግስት ታጣቂ ሀይል ታፍሰው ተወሰደዋል። ያለ ምንም ጥፋት የታሰሩት መሪዎቻቸው እንዲፈቱ እና የመብት ጥያቄያቸው እንዲመለስላቸው ለመጠየቅ፣ ባዶ እጃቸውን በወጡት የወላይታ ወጣቶች እና ሕዝቦች ላይ አሰቃቂ ግድያ በመፈፀም መንግሥት ጠላትነቱን ይበልጥ አረጋግጧል። እኛ የኦሮሞ ቄሮዎች በወላይታ አመራሮች እና ሕዝብ ላይ የተፈፀመውን ሕገወጥ ግድያና እስራት አጥብቀን እናወግዛለን።

ለሰፊው የወላይታ ሕዝብ የምናስተላልፍው ውንድማዊ ምልክት፤

የራሳችሁን ክልል እንዲኖራችሁ እየታገሉ የወደቁት የወላይታ ወጣቶች ደም፣ ፈሶ የሚቀር አይደለም። እየጠየቃችሁት ያለውን የመብት ጥያቄ፣ ይበልጥ ጠንክራችሁ እንደምትቀጥሉ ተስፋ እናደርጋለን። የታሰሩት ሙሁራይ፣ ሽማግሌዎች እና ወጣቶች የሚፈቱት በናንተ ትግል መሆኑን አምናችሁ እንድትቀጥሉም ጥሪያችንን እናቀርባለን።

የኦሮሞ ሕዝብ የወላይታ ሕዝብ እየጠየቀ ያለውን የመብት ጥያቄ የሚደግፍ እና በአስፈላጊውም ድጋፍ ከጎናችሁ መሆናችንን እንገልፃለን። ይወላይታ ሕዝብ እየጠየቀ ያለው የማንነት ጥያቄም በአስቸኳይ እንዲመለስ ምኞታችን ነው።

እኛ የኦሮሞ ቄሮዎች የወላይታ ሕዝብ ጥያቄ ይመለስ ዘንድ የበኩላችንን ድርሻ ለመወጣት ዝግጁ መሆናችንን እንገልጻለን። አብረን በመቆም የሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች እኩልነት እና ማንነት የሚከበርባትን ኢትዮጵያ እንገንባ እያልን፣ የጀመራችሁትን ትግል ከግብ ሳታደርሱ እንዳታርፉ እንላለን።

ድል ለዴሞክራሲ
ድል ለጭቁን ሕዝቦች!!
_____
ቄሮ ኦሮሞ
ነሐሴ 10, 2020
ፊንፊኔ፣ ኦሮሚያ