SHOCKING!የዛሬው የመሬት አስመላሽ ኮሚቴውና ምልሻው ውሎ በቤንሻንጉል ጉምዝ ይህን ይመስላል።

Shocking! የዛሬው የመሬት አስመላሽ ኮሚቴውና ምልሻው ውሎ በቤንሻንጉል ጉምዝ ይህን ይመስላል።

አንዱ የአብን አመራር ጧት እንዲህ ጽፎ ነበር
“የመተከል የማያበራ ዘር ፍጅት የፌዴራል፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝና የአማራ መንግስታት እንዲሁም የብልጽግና ፓርቲ ቸልተኝነት፣ ዳተኝነትና ግድየለሽነት የሚፈፀም ነው። ዘር ፍጅቱን ማስቆም እንኳንስና ከፀጥታ ኃይሉ ከአካባቢው ነዋሪዎች አቅም በላይ ሆኖ አይደለም። ችግሩ ሌላ ነው። ማድበስበስ አያስፈልግም!” ይህን የጻፈው ከዚህ በፊት አማራ የሰው ልክ ነው ያለው ሰው መሰለኝ።
ሌሎች ደግሞ የአማራ ምልሻ መላክ አለበት የሚል ጥሪ ሲያስተላልፉ ነበር።
እንዳሉትም አደረጉት። መንግስት አውቆ ተኝቷልና እኛው ራሳችን ሔደን ልክ እናስገባቸው አሉ። አደረጉት። እዚህ ላይ ፒፒ ህገመንግስት ተጣሰ ምናምን አትልም፣ በስልጣኗ ስላልመጡ።
በክልላቸው እንኳን ሊደረግ የማገባን ድርጊት ከክልላቸው ውጪ ሔደው እንደፈለጉ ገርፈው፣ አድምተው፣ እንደእንስሳ የኋሊት ጠፍንገው ሲጫወቱባቸው ዋሉ።
እንዲህ እያለ የመንጋ ህግ 3ኛ አመቱን አስቆጠረ።
ብሔር ብሔረሰቦች ሆይ በሰው ልኩ አማራ አይን ተመዝናችሁ ቀላችሁ ተገኝታችኋልና ቻሉት።