Oromia Media Network: Conversation with Dr Trevor Trueman

Oromia Media Network: Conversation with Dr Trevor Trueman

የኦሮሞን ህዝብ የአርነት ጥያቄ በዚያ በጭለማው ዘመን ከጠየቁት አንዱ ነው የኢሉ አባቦራው ደራሲና ጋዜጠኛ በዓሉ ግርማ ኤጀርሶ…
.
ደራሲና ጋዜጠኛ በዓሉ ግርማ ኤጀርሶ በኡሉ አባቦራ ዞን በሱጴና ሶዶ ወረዳ ሱጴ በምትባል የገጠር ከተማ መስከረም 11: 1932 ዓ.ም ተወለደ። የበዓሉ ወላጅ አባት በወቅቱ ወደ ኢሉአባቦራ ለንግድ ስራ የተሰማራ የነበረና ጂምናዳስ የተባለ የህንድ ዜግነት ያለው ሲሆን እናቱ ደግሞ ወ/ሮ ያደቴ ኤጀርሶ ትባላለች።
የበዓሉ እናት ቤተሰሰቦች ጋብቻቸውን ስለተቃወሙና ወደ ፊንፍኔ መሄዱን የበዓሉ እናት ባለመቀበሏ ወላጅ አባቱ በዓሉንና ሚስቱን ጥለው ፊንፍኔ ገባ።
ከቆይታም በኋላ የበዓሉ እናት ወላጅ አባቱን እንዲያገኝ በማለት የወላጅ አባቱን አድራሻ ትሰጠውና በዓሉን ከነጋዴዎች ጋር ወደ ፊንፍኔ ትልከዋለች። በዓሉ በወቅቱ ተቀባይ አላገኘም ነበር። አማርኛ ቋንቋን አለመቻሉ ደግሞ ፍለጋውን አስቸጋሪ አድርጎበት ነበር። በመጨረሻ ግን መንገድ ላይ እያለቀሰ ያገኙት አንድ አባት ጠርተውት በራሱ ቋንቋ ሁኔታውን ከጠየቁት በኋላ ይዘውት ወደ ቤታቸው ገቡ። ከዚያም በኋላ ምንም የስጋ ዝምድና ሳይኖራቸው በዓሉን እንደልጃቸው ያሳደጉትና ያስተማሩት አባት አቶ ግርማ ወልዴ ይባላሉ። ከቆይታ በኋላ ወላጅ አባቱን አኝተው የነበረ ቢሆንም እርዳታውን አልፈለገም። በዓሉም የአንደኛ አመት የዩኒቨርሰቲ ተማሪ እያለ የአባቱን ስም ወደ ግርማ በማስቀየር በዓሉ ግርማ ተብሎ መጠራት ጀመረ።
በዓሉ የአያቱን ስም ግን በአሳዳጊው አቶ ግርማ አባት ወልዴ ከመጥራት ይልቅ
የእናቱን አባት ስም ኤጀርሶን መጠቀሙን ነበር የመረጠው። ሙሉ ስሙም በዓሉ ግርማ ኤጀርሶ ሆኖ ፀና።
የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በልዕልት ዘነበወርቅ ት/ቤት ፤ ሁለተኛ ደረጃ
ትምህርቱን ደግሞ በጄኔራል ዊንጌት ት/ቤት አጠናቀዋል። የመጀመሪያ ዲግሪውን በፖሊቲካል ሳይንስ እና አለምዓቀፍ ግንኙነት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያገኘ ሲሆን፤ በአሜሪካ በሚገኝ ሚችጋን ስቴት ዩኒቨርሲቲ ደግሞ የማስተርስ ድግሪውን በፖለቲካል ሳይንስና ጋዜጠኝነት አጥንቷል። ደራሲ በዓሉ ግርማ በተለይ በልብ ወለድ እና በፈጠራ የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች ከታወቁት የኢትዮጵያ የዘመኑ ደራሲዎች መካከል ተወዳጅነትና ዝናን ያተረፈ ዕውቅ ደራሲ ነበር። ከጻፋቸው በርካታ ድርሰቶቻቸው ውስጥ «ከአድማስ ባሻገር» የተሰኘው መጽሐፉ በሩስኛ ቋንቋ ተተርጉሞ በቀድሞዋ የሶቪየት ሶሽያሊስት ህብረት ሪፑብሊክ ቀርቧል።
በተጨማሪም በጋዜጠኝነት ሙያም ስሙን ያስጠራ፤ ሙያውንም ያስከበረ ደራሲ ነበር። «የዛሬይቱ ኢትዮጵያ» ጋዘጣ፤ የመነን መጽሔት ፤ የአዲስ ረፖርተር መጽሔት፤ የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በመሆን ከመሥራቱም ባሻገር፤ ብዙ ወጣት ጋዜጦችን ለማፍራት ጥረት አድርገዋል። አዲስ ሪፖርተር የተባለውን መጽሔትም ደረጃው ከፍ እንዲልና በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲገመገም አድርገዋል። በጋዜጠኝነት ሙያው በኢትዮጵያ ራዲዮ ሰርቷል።
በኢሉ አባቦራ ደን ምድር ከአዴ አያኔ ኤጀርሳ ማህፀን የተገኘውና በአፋን ኦሮሞ
አፉን የፈታው ደራሲ በዓሉ ግርማ ለኢትዮጵያ ሥነጽሁፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ
ያበረከተና ብዙ ሥራዎችን ያቀረበ ሲሆን፤ የመጨረሻው መጽሐፉ «ኦሮማይ»
በመባል ይታወቃል። ይሄውም መጽሐፍ በወቅቱ በነበረው የደርግ መንግስት
ሊደገፍ ባለመቻሉ በ1976 ዓ.ም ለደራሲው ህይወት መጥፋት መንስኤ ለመሆን በቅቷል። ከድርሰቶቹ መካከልም ከአድማስ ባሻገር የኅሊና ደወል የቀይ ኮከብ ጥሪ ሐዲስ ደራሲው እና ኦሮማይ ይገኙበታል።
ይህ ብቻም አይደለም በአሉ የኦሮሞን ህዝብ የአርነት ጥያቄም በዚያ በጭለማ ዘመን “ካድማስ ባሻገር” በሚለው መፅሃፉ የተለያዩ ገፀባህርያትን በመሳል የወገኖቹን ጥያቄም ጭምር አንስቶአል። በዚህ “ከአድማስ ባሻገር” በተባለ መፅሃፉ ጫልቱ የተባለች ዋና ገፀባህሪ አስተዋውቆናል። ስሟን ሉሊት ታደሰ ብላ ቀይራ ትታያለች። ሞታ በተቀበረችው በቀድሞይቱ የኢትዮጵያ ኤምፓየር ውስጥ፣ “ጫልቱ” በሚል ስም መኖር ስለማይቻል ስሟን መቀየሯን አበራ ለተባለ ጓደኛዋ በምስጢር ታጫውተዋለች። መፅሃፉ ሲያልቅ ግን አበራና ሉሊት ጋብቻ ለመፈፀም አይበቁም። አበራ ወርቁ እስርቤት ገባ። “ጫልቱ ” ወደ ማንነቷ ሳትመለስ እንደ “ሉሊት” ህይወቷን ቀጠለች።
አዎ አማርኛ ቋንቋን ሳይቀር ህይወት ከዘሩበት የአባገዳ ልጆች አንዱ….
ክብር ለሱ ይሁን
Via:- Guma Saqeta

OMN: የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦ.ነ.ግ) መግለጫ (April 29,2021)