OMN: በወላይታ ዞን የተካሄደው መፈንቅለ ስልጣን እንዳሳሰባቸው የወላይታ ብሄር ተወላጆች ገለጹ::

OMN: (August 29, 2020) በወላይታ ዞን የተካሄደው መፈንቅለ ስልጣን እንዳሳሰባቸው የወላይታ ብሄር ተወላጆች ገለጹ::

የወላይታን ህዝብ ድምጽ ያስተጋበውን አመራር በወታደራዊ ሃይል አፍኖ በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት ያጡትን የቀድሞ የድህዴን አባላትን ወደ ስልጣን ማውጣት ብልጽግና ለህዝቡ ያለውን ንቀት ያሳያልም ብለዋል።
የወላይታ ህዝብ በታጣቂ ሃይሎች እየተሽበረ፡ እየታሰረና እየተወከባ ይገኛል ያሉት የብሄሩ ተወላጆች የወላይታን ህዝብ በጠብመንጃ አፈሙዝ ለማምበርከክ የሚደረግ መንግስታዊ ዘመቻ መቆም አለበት በማለት አሳስበዋል።
በማከልም የብልጽግና አገዛዝ የወላይታ ህዝብ የጠየቀውን ራስን በራስ የማስተዳደር የክልል ጥያቄ ወደ ጎን በመተው አሃዳዊ ስርዓት ለማስፋን ይሰራልም ብለዋል።
የወላይታ ዞን አመራሮችን ወንጅሎ ለማሰር መሞከር መቆም አለበት፤ ህዝቡም ጥያቄው ምላሽ እስክያገኝ ድረስ ሰላማዊ ትግሉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።