OMN: ህዝበ ውሳኔን በተመለከተ ቆይታ ከወላይታ ብሄር አክቲቪስቶች ጋር (Dec. 02, 2019)

OMN: ህዝበ ውሳኔን በተመለከተ ቆይታ ከወላይታ ብሄር አክቲቪስቶች ጋር (Dec. 02, 2019)


ዛሬ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ከወላይታ ተወካዮች ጋር ባደረጉት ውይይት ተወካዮቹ ለህዝቡ ጥያቄ ህገመንግስታዊ መልስ መስጠት ብቻ መፍትሔ እንደሆነ ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወላይታ ህዝብ የክልልነት ጥያቄ በመርህ ደረጃ ቢያምኑም ለመፈጸም ፈቃደኛ የሆነ አይመስልም። ይህ ፍርሃት የመጣው የወላይታ በክልልነት መደራጀት ሌሎችንም በተመሳሳይ መንገድ እንዲሄዱ በማድረግ ክልሉን በአራት ወይም አምስት አዲስ ክልል ይከፍላል ከሚል ሥጋት የመነጨ ነው። ተወካዮቹ ህገመንግስቱ እስከፈቀደ ድረስ ክልሉ አምስት ቦታ ቢከፈልም ችግር እንደሌለው ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት የካፋና የወላይታ ህዝቦች የክልልነትን ጥያቄ አምርረው በህገመንግስቱ መሠረት እንዲፈጸምላቸው እየጠየቁ ብሆንም ሌሎች ተመልካች መሆን መምረጣቸው አስገራሚ ነው። በክልሉ ያሉ ህዝቦች ለመብታቸው ቢቆሙ በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ይቀል እንደነበር ተገልጿል።

በዛሬው ውይይት ጠቅላይ ሚኒስተሩ ጋር ከነበረው ውይይት ውስጥ የክልል ዋና ከተማ ወላይታ ሶዶ ቢሆን ህዝቡ የሚያነሳውን የክልልነት ጥያቄው ይቀይር ይሆናል ወይ የሚል እንድምታ ያለው ነጥብ ቢሆንም የወላይታ ተወካዮች ስለሌሎች እነሱ መወሰን እንደማይችሉና ጥያቄያቸው የወላይታ ክልል መሆንን ብቻ የሚመለከት ነው ማለታቸው ጠቅላዩን አላስደሰተም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠብቀው የነበረው የወላይታ ተወካዮች እሳቸው ያነሱትን ሀሳብ ሙሉ በሙሉ በመቀበል የክልልነት ጥያቄው ይቀራል የሚል ቢሆንም እንዳሰቡት ሳይሆን ቀርቷል። ከዚህም የተነሳ ስብሰባውን አቋርጠው ለመሄድ ተገደዋል። ስብሰባውን ለቀው በሚወጡበት ወቅት የመጨረሻ የሚትሉትን ውሳኔ አሳውቁኝና አምስት ሰዎች ወክላችሁ ስጡኝ የሚል ትዕዛዝ ቢኖርም ተወካዮቹ ውሳኔያችን የወላይታ ብሔራዊ ክልል መንግስት ነውና የምንወክለው ሰው የለንም ማለታቸው ስብሰባው ያለ ስምምነት እንዲጠናቀቅ አድርጎታል።

በዚህ አካሄድ የብልጽግና ፓርቲ ብዝሃነትን ለማስተናገድ ዝግጁ አለመሆኑንና በፓርቲው ውስጥ ያሉ ግለሰቦች ከዚህ ቀደም በደኢህዴን ውስጥ ህዝብን ከህዝብ በማጋጨት የሚታወቁ መሆናቸው የነበረውን ውይይት ከባድ እንዲሆን አድርጎታል። በመሆኑም ዛሬ ጠቅላዩ ከወላይታ ተወካዮች ጋር ያደረጉት ውይይት ውጤት አልባና ያለ ምንም ስምምነት የተጠናቀቀ መሆኑን ማወቅ ተችሏል።

Wolayta Digital Channel-WDC


ለስልጣን ሲል የተገዳደለዉ አማራ ነዉ፡፡ በሃሳብ የሚሟገተዉን ‘ኦሮሞ አገር መምራት አይችልም’ ብሎ ትንታኔ ማቅረብ ደደብነት ነዉ፡፡ በሃሳብ መለያየት እና መከራከር መብት ነዉ፡፡ የዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ምንጭም ነዉ፡፡


#Inbox

“የከምባታ ዞብሀ አስተባባሪ ኮሚቴ

“ታሪካዊ የሆነ የራሱ መንግስት የነበረው የአኩሪ ታሪክ ባለቤቱ የከምባታ ህዝብ የኢፌዲሪ ህገ-መንግስት የራስን እድል በራስ ለመወሰን በሰጠው እውቅና መሰረት እና ህገ-መንግስቱ ላይ በተቀመጠው ቅድመ ሁኔታ መሰረት እራሱን ችሎ በክልል ለመደራጀት በዞኑ ምክርቤት በሙሉ ድምጽ ወስኖ ጥያቄውን ወደክልል ከመራ ድፍን አንድ አመት ሊያስቆጥር የቀሩት ጥቂት ቀናት ናቸው። ነገር ግን የክልሉ ምክርቤት ጥያቄውን በማፈን እስከ አሁን ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎት ቆይቷል። ይባስ ብሎ መንግስት በዞኑ ላይ ህገወጥ የሆነ እና ምንም አይነት ምክንያት የሌለውን ኮማንድ ፖስት በማቋቋም ህዝቡ ጥያቄውን በሰላማዊ መንገድ እንዳያቀርብ እገዳ አድርጎበታል። ዞብሀ በነገው እለት በሚያደርገው ስብሰባ የሰላማዊ ትግል አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ክልል የመሆን ጥያቄው በህገመንግስቱ መሰረት እንዲመለስ ትግሉን ወደላቀ ደረጃ ያሸጋግራል። ከምባቶማ እና ህብረብሄራዊት ኢትዮጵያ ያብባሉ!”

#ከምባቶማ_ያብባል!

Tsegaye Ararssa


MUKTAR ADEERO AND KHADRA SILIMO FEAT BACKO 2020 ARAARAMI OROMO SONG (DIRECTED BY STUDIO LIIBAAN