KMN: እስራት እና ግድያ በኦሮሚያ እንደቀጠለ ነዉ::

እስራት እና ግድያ በኦሮሚያ እንደቀጠለ ነዉ::
KMN:-November 25/2020
=====================
እስራት እና ግድያ በኦሮሚያ እንደቀጠለ ነዉ::
የቄሮ ትግል በሌላ በኩል እንደ ሰደድ እሳት እስካሁን ባልተደረሰባቸዉ ቦታዎች ጭምር ደርሶ እስረኞችን በሀይል እስከማስፈታት ደርሶዋል:: በሌላ በኩል መንግስት አሁንም በእስር ቤት የሚገኙ ታሳሪዎችን ከእስርቤት እያወጣ መርሸኑን ቀጥሎል::
ሰሞኑንን ብቻ በኦሮሚያ ምዕራብ ወለጋ,ቄለም ወለጋ,ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ, ጅማ, ሰሜን ሸዋ ዞኖች እስረኞችን ከእስር ቤት አዉጥተዉ የረሸኑ ሲሆን ባለፈዉ እሁድ እለት ማለትም ሕዳር 21/2020 ደግሞ በአምቦ ከተማ ታስሮ የነበረን በኣምቦ ከተማ የኦነግ ስራ አስፈፃሚ አባል የሆነዉን አቶ ገላና ኢማናን ከእስር ቤት አዉጥተዉ ገድለዉ ከጣሉት ቦኃላ አስክሬኑ ከሁለት ቀን ፍለጋ ቦኃላ 23/11/2020 አምቦ ከትማ ዳርቻ ደቢስ የሚባል ወንዝ ውስጥ ተጥሎ ተገኝቶዋል::
ይህን አሰቃቂ ግድያ እና እስራት ከስሩ ለምንቀል በመላዉ ኦሮሚያ የሚደርገዉ ትግል በምስራቅ አርሲ ሁለት ቦታዎች እስርኞች በኃይል የማስፈታት እርምጃን ጨምሮ በመላዉ ኦሮሚያ መንገዶችን መዝጋት, የህግወጡ መንግስት መገልገያ የሆኑ የማሰቃያ መስሪያ ቤቶችን የማዉደሙ ድርጊት ተጠናክሮ ቀጥሎዋል::