Jimma University: ሞራ ግርዶሽና ግላኮማ ቀዶ-ጥገና እና አጠቃላይ ዓይን ምርመራና ህክምና አገልግሎት (የካቲት 30- መጋቢት 4፣ 2012 ዓ.ም.)

ከ1000 በላይ ለሚሆኑ ወገኖች ነጻ የአይን ሞራ ግርዶሽና ግላኮማ ቀዶ-ጥገና እና አጠቃላይ ዓይን ምርመራና ህክምና አገልግሎት (የካቲት 30- መጋቢት 4፣ 2012 ዓ.ም.)

አሁንም ማህበረሰብን የማገልገል ባህላችንን በማጠናከር ኮቪድ-19ን በመዋጋት ላይ እንገኛለን!

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ዓይን ህክምና ክፍል ከየካቲት 30 እስከ መጋቢት 4/ 2012 ዓ.ም. ለተከታታይ አምስት ቀናት ባካሄደዉ የነጻ ዓይን ህክምና ዘመቻ ከ 1 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወገኖች አገልግሎት ሰቷል፡፡ የዓይን ህክምና ክፍሉ ተመሳሳይ የበጎ አድራጎት ዘመቻዎች በማካሄድና ማህበረሰቡን በማገልገል የሚታወቅ ሲሆን እንደ አገር ተምሳሌት የሚሆኑ ተግባሮችን እየፈጸመም ይገኛል፡፡ ት/ት ክፍሉ በ2020 (2012/13 ዓ.ም) ጅማን ጨምሮ በተለያዩ በደቡብ ምዕራብ የአገራችን ክፍሎች ሰባት ዙር የነጻ ህክምና አገልግሎት ለመስጠት አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን፣ በመጀመርያ ዙር ለ5 ቀናት ከሌሎች ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ባደረገዉ የነጻ ህክምና ዘመቻ ከአንድ ሺህ በላይ ለሚሆኑ የማህበረሰባችን አካላትን ተጠቃሚ አድርጓል፡፡ ከነዚህም የነጻ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ዉስጥ ከ500 በላይ ሰዎች የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና ተደርጎላቿል፡፡

የት/ት ክፍሉ ሃላፊ የሆኑት ዶ/ር ኩመሌ ቶለሳ የዘመቻዉ ዋና አላማ በራሳቸዉ ወጪ ህክምና ማግኘት የማይችሉ እና በቤተሰብ ድጋፍ የሚንቀሳቀሱ ወገኖችን በማገዝ ከጥገኝነት የማላቀቅና የእለት ተእለት ኖሮአቸዉን እንዲመሩ ማስቻል መሆኑን ህክምና እየሰጡ ባሉበት ወቅት ገልጸዋል፡፡ ለባለሙያዎቹ እና ለክፍላቸዉ ባልደረቦች በሙያቸዉ እገዛ በማድረግ ለረዥም አመታት ማየት ተስኗቸዉ የነበሩት ሰዎች ማየት በመቻላቸዉ የሚታይባቸዉ ደስታና የሚሰጡት ግብረ-መልስ የበጎ አድራጎት ስራዉን በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥሉ አቅም የሚሆናቸዉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ህክምና እየሰጡ በነበሩበት ወቅት ያነጋገርናቸዉ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ማዕከል የአይን ህክምና ስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር አዕምሮም ይህንኑን ሃሳብ ያጋሩን ሲሆን የማህበረሰቡን ደስታ መጋራትና ነጻ የሙያ አገልግሎት በመስጠት ለማህበረሰቡና ለአገር አቅም መፍጠር የሚያስደስታቸዉ መሆኑን ገልጸዉ በዚህ ረገድ ሁሉም የተቻለዉን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ትምህርት ክፍሉ የነጻ ህክምና ዘመቻዉን ያካሄደዉ ከሂማሊያን ካታራክት ፕሮጀክትና ቪዥን ኬር ሰርቪስ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ሲሆን ዘመቻዉ ሲካሄድ በነበረበት ወቅት የዩኒቨርሲቲዉ ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳና የዩኒቨርሲቲዉ ከፍተኛ አመራሮች በቦታዉ በመገኘት ተመሳሳይ ስራዎች እንደ አገርም ምሳሌያዊ ስለሆኑ መደገፍ እንዳለባቸዉ በመጥቀስ ለባለሙያዎቹ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

Jimma University


ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ፦

• በጅቡቲ 162 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 9 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

• በኬንያ 362 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 12 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

• በኢትዮጵያ 74 ብቻ የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 6 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Test test test

Ethiopia Physicians Union – የኢትዮጲያ ሀኪሞች ህብረት