ሃይሌ ከኦርቶዶክስ አማኞች ጋር ተጋጨ! Haile about Gete Wami.

ሃይሌ ከኦርቶዶክስ አማኞች ጋር ተጋጨ! Haile about Gete Wami.

Haile Gebresellasie On Gete Wami’s Case – “የሌለ ነገር ነው፤ አትሌቶች ሆይ ዝም ብላችሁ ሥራችሁን ሥሩ”

በመላው አለም እየሄዱ በሩጫው ተወዳድረው የኢትዮጵያን ስም የሚያስጠሩ ለሐገራቸው ሆነ ለራሳቸው የሚጠቅም በሚልዮን የሚቆጠር ገንዘብ ይዘው መተው ኢንቨስት የሚያረጉ አትሌቶች በምቀኛ አይን መግባት ጀመሩ እራሳቸውም በአጉል ፉክክር #ለእርኩስ_መንፈስ ለመተት ገንዘባቸውን በመገበር የሰውን ጉልበት በመንፈሱ ሐይል በመውሰድ በክፋት ድርጊት ተክነዋል እግዚዮ ነው እስኪ እነዚን #ሶስት 3 በሩጫ መተት የተያዙ ልጆች ተመልከቱዋቸው ።

Kirubel Natnael Mebratuሃይሌ ከኦርቶዶክስ አማኞች ጋር ተጋጨ! Haile about Gete Wami.


ከራሱ ሐሳብ የተጣላው ኃይሌ
=============================
አትሌት ኃይሌ በጌጤ ዋሚ መታመም ዙሪያ ጋዜጠኛ አበበ ጊደይ ሸገር ላይ ላቀረበለት ጥያቄዎች አስተያየት ሰጥቷል። ኃይሌ በመልሱ ያነሳቸውን ነጥቦች አንድባ’ንድ እንመልከት

1.”ሶሻል ሚዲያ ሊያጠፋን ነው – scoial media is social crisis”

ይህን ያለው የጌጤን ቪዲዮ ማህበራዊ ድረገጽ ላይ ስለተመለከተው ነው። ይሁን እንጂ ቪዲዮው የተቀረጸው በአባ ግርማ የቪዲዮ/የሚዲያ ክፍል ለመሆኑ ከዚህ በፊት የሳቸውን ስራዎችን የተመለከተ በቀላሉ ይገነዘባል።መውቀስ ካለበት እሳቸውን ብቻ መሆን አለበት። (አበበ ጊደይ እዚህ ጋር የቪዲዮውን ዋና ምንጭ ለኃይሌ ቢነግረው ጥሩ ነበር) አባ ግርማ በበኩላቸው ቪዲዮው እንዲታይ የሚፈልጉት “የፈውስ” ስራቸው እውነተኛነትን ለማሳየት፣ለማረጋገጥ ብለው ይሆናል::
ታዲያ ሰውስ ለምን ያባዛዋል? ሰዎች በYouTube ያገኙትን ቪዲዮ ወደ ፌስቡክና ሌሎች ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚያመጡት በተለያዩ ምክንያቶች ሊሆን ይችላል። በአባ ግርማ “ፈውስ” የሚያምኑ ከሆነ የእምነታቸውን ዋጋ፣ ታምረ አምላክን ለማሳየት። ሌሎች ደግሞ በጌጤ ወቅታዊ ሁኔታ ተገርመው፣ ተደናግጠው…

ኃይሌ ግን ከዚህ ቀደም በኢትዮጲያ የተነሳውን ሕዝባዊ ቁጣ ከሶሻል ሚዲያ ጋር አገናኝቶ የማውገዙን ትክክለኛነት ለማጠናከር በፍጥነት ወደዚያ ገበቶ ሌላ ስህተት ፈጸመ። ማህበራዊ ድረ ገጽ የብዙ ሰዎችን ሰዎች ሐሳብ በአንድ ቋት የምታገኝበት ሰፈር ነው። እንደ ከዚህ በፊቱ ያንተንና የአከባቢህን፣ የመሰሎችህን ብቻ እንደምትሰማው የገሀዱ ዓለም የአካል ግኑኝነት-ንግግር ሳይሆን የሺህዎችን ሐሳብ በአንድ ጊዜ የምትወደውንም የማትወደውንም ይዞ የሚያጎርፍ ነው። በዚህ መድረከ ላይ ቁጥጥር ሊደረግባቸው የሚገባቸውን ነገሮች አስተዳድሪዎቹ ፌስቡክም ሆነ ሌሎች በዝርዝር አስቀምጠዋል። ይህን ተላልፎ የሚገኝ ካለ ሪፖርት ማድረግ ነው። የአባ ግርማ ቪዲዮ ግን ለዚያ የሚበቃ አይመስልኝም። ምክንያቱም የውሸት ነገር አልተሰራጨም (ፈውሱ ሳይሆን ቪዲዮ ቀረፃው:: ስለፈውሱ ኀይማኖተኞች ይወያዩ)። በርግጥ ኃይሌ በድፍረት “ተቀነባብሮ ነው” ሲል ይደመጣል።

የለ ሁኔታውን በኛ ባህል እንዳኘው ካልን ደግሞ ጌጤ የሄደችው ሕዝብ በሚሰበሰብበት የፈውስ አገልግሎት አደባባይ ነው። ቪዲዮውን በማየት ብቻ የሕዝብ ብዛቱን መገመት ይቻላል። ጌጤ ስትሄድ ደግሞ ይህንን አምናበት ነው። ቪዲዮው ሲቀረጽ ትመለከታለች ወይም ይዘዋት የሄዱ ሰዎችም ያውቃሉ፣ያያሉ። አባ ግርማ ከዚህ በፊት ሐሰተኛ የሚል ክስ ቀርቦባቸው ቢታሰሩም በነፃ ተለቀዋል። ተከታዮቻቸውም ሺህዎች ናቸው።በatheist እይታ ከሆነ ደግሞ ጉዳዩ የኢ-አማኒ አማኞችና የኀይማኖት ተከታዮች ክርክር እንጂ ከጌጤ ጋር አይገናኝም።

2. “አጋንንት የለም፣ የት ነው ያለው ጥንቆላ፣መተት የለም ስፖርት ላይ የለም ውሸት ነው፣ወሬ የወለደው ነው”

ኃይሌ “ስፖርት በልፋት፣በስራ የሚገኝ ነው” ማለቱ ትክክል ቢሆንም። ጥንቆላና መተት ለመኖሩ የግድ ያለበት ቦታ መሄድ አያስፈልግም።ኢትዮጲያ ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም አለ። “ጌጤ ያለችው በውስጧ የምታስበውን ነው። እንደዚህ ዓይነት ቦታዎች ስትሄድ የምትናገረው በወስጥህ ያለውን በመድገም ነው” ይላል። እዚህ ጋር ኃይሌ psychiatrist ሆነ:: ድናም ይሁን አለዳነች ጌጤ ራሷ መልስ ይኖራታል።

የፈውስን ጉዳይ ለፈጣሪ የሚተወው ኃይሌ “የሰይጣን ስራ ይባላል። አንዳንድ ጊዜ የሰይጣንና አጋንንት ስራ ለኔ አይገባኝም። እዚያ ላይ የማየው ማን ነው ሰይጣኑ ፣ ማነ ነው አጋንንቱ… የፈጣሪ ስራ ነው። ለገንዘብ፣ለፕሮፓጋንዳ፣ የራስን ተፈላጊነት ለማጉላት… ገንዘብ ለማግኘት የሚደረገው ስራ የፈጣሪ ስራ አይደለም። ይኼ የፈጣሪ ስራ ሳይሆን የአጋንንት ስራ ነው” ብሎ ይደመድማል።

አባ ግርማ ገንዘብ ይቀበላሉ እንዴ? ከተቀበሉ ፣ ልክ ለጠበል ገንዘብ እንደሚጠይቁ ቤተክርስትያኖች መወገዝ አለባቸው። ፈጣሪ የሰጠውን መንፈሳዊ ኃይል ስለምን ይሸጣል?

3.”ጌጤ psychiatrist የአዕምሮ ሕመም ሕክምና ባለሞያ ማየት ይገባታል”

ጀገናው አተሌት ትክክል ነው። ሰዎች በእምነታቸው በመንፈሳዊ ፈውስ እንደሚድኑ ሁሉ ሳይናሳዊ ሕክምና ሊያስፈልግ ይችላል። ዋናው መዳኑ ነው።

ኃይሌ ” ጓደኛዬ ናት” ብሎ እየተናገረ ጌጤ አባ ግርማ ጋ እስክትሄድ፣ ጉዳዩ በቪዲዮ እስኪቀረጽና ለማህበራዊ ሚዲያ እስኪቀርብ ድረሰ ይህ የኃይሌ መፍትሔ የት ሄዶ ነበር?

4.”ጌጤ ኃይለኛ ናት”
ሲጀምር “ማህበራዊ ሚዲያ ሊያጠፋን ነው” ብሎ በሕዝብ አደባባይ የተቀረፀው የጌጤ ጉዳይ በማህበራዊ ሚዲያ መሰራጨቱን የኮነነው ኃይሌ የተናገረውን በደቂቃዎች ውስጥ ዘንግቶ የጌጤን ምስጢር ራሱ መዘርዘር ተያያዘ።
“ኃይለኝነቷ እየጎዳት መጠቷል። በተለያየ ምክንያት በቤተሰብም ለማስታረቅ (ከባሏ ጋር) የሞከርናቸው ነገሮች አሉ:: በሷ ኃይለኝነት ሊሳኩልን አልቻለም:: ትላንት በፊልም ውስጥ ያየሁት ያንን ኃይለኝነቷን ነው።” ይላል ኃይሌ። ለምን ይህን ምስጢር ወይም በግል የሚያውቀውን ጉዳይዋን ለአደባባይ ያበቃዋል? ይህንንም ከማህበራዊ ሚዲያ “ጥፋት” እንመድበው?

ሌላው እውነት ደግሞ ኃይሌ የጌጤን ችግሮች ያውቃል ማለት ነው። ስለዚህ እንደዚያ ከሆነ ለማስታረቅ ከመሞከር ባለፈ መፍትሔ ብሎ ያቀረበውን psychiatrist በተጨባጭ ሞክሯል ወይ?
ኃይሌ ለጌጤ ችግር መፍትሔ ሊሰጥ ወይም የመፍትሔ ሐሳብ ሊያቀርብ ቀርቶ ከራሱ ሐሳብ ጋር መስማማት አቅቶት ተስተውሏል::

“ማህበራዊ ሚዲያ ሊያጠፋን ነው” ብሎ የተንገበገበውን ያህል ሕዝብና ሀገር በጥይት የሚያጠፋውን መንግስት አንድም ቀን አውግዞ አያውቅም። “ሶሻል ሚዲያ ማህበራዊ ቀውስ አመጣ” የሚለው ኃይሌ ሀገራዊ ቀውስ ያንሰራፋውን ህወሓት-ኢህአዴግ አንድም ቀን ወቅሶ አያውቅም። እንዲህም ሆኖ የሀገር ሽማግሌ የሚል ማዕረግ ከተሸከመ 13 ዓመታት ተቆጥረዋል።
ብሔራዊ ጀግናችን እንደመሆኑ ከአንደበቱ የሚወጡ ቃላቶችና የሕይወት ጉዞዎቹ ሁሉ ጥቅም ወይም ጉዳት እንደሚኖራቸው ተረድቶ አስተውሎ ቢራመድ መልካም ነው።

Kassa Yilma