GMO: ዘረመሉ የተቀየረ የጥጥ ዘር በኢትዮጵያ

ዘረመሉ የተቀየረ የጥጥ ዘር በኢትዮጵያ

(dw)-ኢትዮጵያ እንደብዙዎቹ ሐገራት ዘረ-መሉ የተቀየረ ዘር ወይም ሰብል አገልግሎት ላይ እንዳይዉል ለረጅም ጊዜ ስትከለክል ነበረ።በጀርመን የኢትዮጵያ የሠብአዊ መብቶች ኮሚቴ እንደሚለዉ ግን የኢትዮጵያ ግብርና ሚንስቴር ያሰራጨዉ የጥጥ ዘር ቢያንስ በበኒሻንጉል ጉሙዝና በጋምቤላ ክልሎች ተዘርቶ የጥጡን አበባ የሚቀስሙ ንቦች የሚያመርቱት ማር እየተበከለ ነዉ

የኢትዮጵያ መንግሥት ዘረ-መሉ የተቀየረ (Genetically modified) የጥጥ ዘር ከዉጪ አስገብቶ በማሰራጨቱ በሐገሪቱ የተለያዩ ግዛቶች በሚመረቱ ሰብሎች በተለይም በማር ምርት ላይ ጉዳት ማድረሱን በጀርመን የኢትዮጵያ የሠብአዊ መብቶች ኮሚቴ አጋለጠ።ኢትዮጵያ እንደብዙዎቹ ሐገራት ሁሉ ዘረ-መሉ የተቀየረ ዘር ወይም ሰብል አገልግሎት ላይ እንዳይዉል ለረጅም ጊዜ ስትከለክል ነበረ።በጀርመን የኢትዮጵያ የሠብአዊ መብቶች ኮሚቴ እንደሚለዉ ግን የኢትዮጵያ ግብርና ሚንስቴር ያሰራጨዉ የጥጥ ዘር ቢያንስ በበኒሻንጉል ጉሙዝና በጋምቤላ ክልሎች ተዘርቶ የጥጡን አበባ የሚቀስሙ ንቦች የሚያመርቱት ማር እየተበከለ ነዉ። ኮሚቴዉ ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትርና ፕሬዝደንት በፃፈዉ ደብዳቤ መንግስት ፈጣን እርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል።የኮሚቴዉን ሰብሳቢ አቶ ሥዩም ኃብተማርያምን በስልክ አነጋግሯቸዋል።