Ethiopia: You can’t have a free, fair and competitive election having put major political rivals behind bars!

Ethiopia: You can’t have a free, fair and competitive election having put major political rivals behind bars!!
 
Join this twitter campaign tonight and make your voices heard! You can’t have a free, fair and competitive election having put major political rivals behind bars on trumped up charges! Speak up and let the world know!
ዝግጅቱ ደምቋል! ስንቁ ተሰንቋል! ትጥቁ ተሟልቷል!
.
ትዊተር አካውንት የሌለው አንድም እንዳይኖር!
ዘመቻ girrisa ልክ ከምሽቱ 2 ሰአት ሲል ይጀመራል። ግሪሳ ማሩኝ እስኪሉ ድረስ ትዊተር ላይ ይዘመታል።
.
#collection_board በተሰኘ hastag ተዘጋጅተው ያለቁ ትዊቶች አሉ። ቋንቋ ቻልክ አልቻልክ ችግር የለውም። ከእናንተ የሚጠበቀው ልክ 2 ሰአት ሲል በዚህ ሊንክ
እየገባችሁ ክሊክ ማድረግ ብቻ ነው። ጣታችሁን ብቻ ለክሊክ አዘጋጁ ሌላው እዳው ገብስ ነው። ጣ! ጣ! ጣ!
.
ዛሬ ሌላ አጀንዳ አንቀበልም አናስተናግድም!
.
ብልጥግና እና ምርጫ ቦርድ ያለ አማራጭ ምርጫ ሲያምራቸው ይቀራል!
.
ያልሰማ እንዳይኖር የሰማ ያዳርስ!

የምርጫ ቦርድ ሊቀመንበር አዴ ብርቱካን ሚደቅሳ በቅርቡ ስልጣናቸውን በፍቃዳቸው ሊለቁ ይችላሉ የሚል ግምት አዲስ ፎርቹን አስነብቦ ነበር። ሀገሪቱ ግልፅ የሆነ አምባገነናዊ አገዛዝ ስር መውደቋና አዴ ብርቱካን ከዚህ በፊት ለፍትህና ለህግ የበላይነት የነበራቸው ቀናኢነት ከግምት ውስጥ ሲገባ ግምቱ ኢ-ምክንያታዊ አይደለም። ነገር ግን ለቦርዱ ቅርበት ካላቸው ተአማኒ ምንጮች FI እንደሰማው ብርቱካን ከስልጣናቸው የመልቀቅ ሃሳብ የላቸውም። አሁን ባለው ሁኔታ ቦርዱ ስልጣን ከብልጥግና ወደ ብልጥግና ከማሸጋገር ያለፈ ይህ ነው የሚባል ስራ መስራት እንደማይችል እየታወቀ ብርቱካን በሊቀመንበርነት መቀጣላቸው ግርምትን የሚያጭር ነው።

 
ዳኛ ብርቱካን ገና የ 27 አመት ወጣት እያሉ ለስዬ አብርሃ የዋስትና መብት ፈቅደውለት ስዬ የባለቤቱ መኪና ውስጥ ለመግባት ሲራመድ የታጠቁ የፀጥታ ሃይሎች እዛው ፍርድ ቤት ውስጥ መሳሪያቸውን አቀባብለው ወደ ስዬና ወደ መኪናው ጎማ ለመተኮስ ይጋበዛሉ። ይህን የተመለከቱት ዳኛ ብርቱካን ፍርድ ቤት በዚህ ደረጃ መደፈሩ ለሳቸው እጅግ devastating experience እንደነበር ለአንድ የውጭ ሚዲያ ተናግረው ነበር። ወደ ተቃውሞ እንቅስቃሴ ለመግባትም ምክንያት ሆኗቸዋል። ያ ለህግ የበላይነት የነበራቸው ቀናኢነት ፤ ገለልተኝነትና ወኔ አሁንም ድረስ አለ ካሉ ዛሬ የሚድረጉ ወከባዎች ላይ አንድ ነገር ማለት አለባቸው። ለምሳሌ በዚህ ሳምንት ልደቱ አያሌው ለሶስተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት የዋስትና መብት ፈቅዶለት ፤ ገንዘቡ ተከፍሎ፤ ፖሊስ በአደራ ስለተሰጠኝ የፍርድ ቤቱን ትእዛዝ አልቀበልም ብሏል። አንዴ አይደለም፤ ሁለቴ አይደለም ፤ ለሶስተኛ ጊዜ። አስቂኙ ደግሞ ክሱ ነው። መጀመሪያ የቢሾፍቱን ቄሮ ለጥፋት በማነሳሳት፤ ቀጥሎ የሽግግር መንግስት ሰነድ ይዞ መገኘትና “ከድጡ ወደ ማጡ” የሚል ፅሁፍ መፃፍ፤ ይህ አልሆን ሲል ፍቃድ የሌለው ሽጉጥ መያዝ የሚል መላ ቅጡ የጠፋ ክስ።
የኦሮሞ ተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ላይ የተደረገውም ከዚህ የተለየ አይደለም። ጃዋር መሀመድ አስክሬንን ወደ አዲስ አበባ መመለስ በሚል ክስ ተጀምሮ
ወጣቶችን ግብፅ ድረስ ልኮ ማሰልጠን የሚል የፈጠራ ክስ ቀርቦበት ከታሰረ ሶስት ወር አለፈው። ጃዋርን ከፖለቲካ ምህዳሩ ለማውጣት ያልተሞከረ ነገር አልነበረም። መጀመሪያ አብይ አህመድ ጃዋርን ጠርቶ ላንተ ከፖለቲካው ይልቅ ወጣቶችን ማብቃቱ ላይ ብታተኩር ብዙ ትጠቅመናለህ። በመቶ ሚሊዮን ብሮች ስራ ማስኬጃ አስፈላጊው ገንዘብ ይመደብልሃል ብሎት ነበር። ጃዋር አለሰማህም አለው። ብዙ የቀድሞ “ታጋዮች” እዚህ ግባ በማይባል ጥቅማ ጥቅም ህሊናቸውን ሲሸጡ ጃዋር የምታገልለት ህዝብና አላማ አለኝ አለ። በገንዘብ ሊደልለው እንደማይችል የተረዳው አብይ ጠዋት ፓርላማ ላይ ዛቻ አሰምቶ ከሰአት ወደ ሶቺ (ራሺያ) ሲሄድ የጃዋር ጥበቃ በሌሊት እንዲነሳ ትእዛዝ ሰጠ። በጉዞው ላይ የሰሜን መአከላዊን ፖሊቲካል ኢንትሪግ የሚግተው ዳንኤል ክብረትም አብሮት ነበር። አብይ ከራሺያ መልስ እቅዱ ተሳክቶ ጃዋር የሌለባትን utopia እንቀላቀላለን የሚል ተስፋ ነበረው። አልሆነም። ነገሩ የገባው ጃዋር ሴራውን ለህዝብ አሳውቆ ህይወቱን አተረፈ። በነገራችን ላይ የግድቡ ጉዳይ ላይ አሜሪካ በአደራዳሪነት እንድትገባ የተሰማማው በዚሁ በሶቺው ስብሰባ ላይ ነበር። ምናልባት ቀልቡ የጃዋር ጉዳይ ላይ ስለነበር ጥቅምና ጉዳቱን የማሰላሰያ ጊዜ አላገኘ ይሆናል። አብይ ጃዋርን በፖለቲካ እውቀት ፤ ግንዛቤና ማህብራዊ መሰረት ብዛት ፈፅሞ ሊገዳደረው የማይችለው mortal enemy መሆኑን ይረዳል። ያለው ብቸኛ መንገድ በአጋጣሚ እጁ ላይ የወደቀውን የፀጥታ ተቋም ተጠቅሞ ወይ እሰከ ወዲያኛው ማሰናበት ወይ ማሰር ነው።
 
በገንዘብና በግድያ ሙከራ አልበገር ያለው ጃዋር ፖለቲካውን ለመቀላቀል ወስኖ ዜግነቱን regain ለማድረግ እንቅስቃሴ ማድረግ ጀመረ። በዚህ የተደናገጠው አብይ ጃዋር የአሜሪካ ፓስፖርቱን መልሶ ማድረግ ያለበትን ሁሉ ቢያጠናቅቅም እንደ ኢትዮጵያ ዜጋ የፅሁፍ እውቅና ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆን ቀረ። በሶስቱ መንገዶች አልሳካ ያለው ሃይል ሃጫሉ ላይ እርምጃ ወስዶ ጃዋርና የኦሮሞ ተቃዋሚዎችን ባጠቃላይ ከፖለቲካ ምህዳሩ የማውጣት መላን ዘየደ። ለማመጣጠን ያህል ለስልጣን ያን ያህል ስጋት የማይሆኑ ሌሎችንም መረቀበት። የሆነው ይህ ነው።
ዛሬ የኦፌኮ ምክትል በቀለ ገርባና በርካታ አመራሮች ዘብጥያ ወርደዋል። ከኦነግ አብዲ ረጋሳና ሚካኤል ቦረንን ጨምሮ ሶስት የስራ አስፈፃሚ አባላት እንዲሁም በርካታ የአመራር አባላት በሃሰት ክስ እስር ቤት ታጉረዋል። በተለይ በኦሮሚያ ስጋት ይሆናሉ ተብለው የሚታሰቡ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች bogus በሆነ ክስ እስር ቤት ተወርውረዋል። እስር ቤቶች አልበቃ ብለው ትምህርት ቤቶች እስር ቤት ሆነዋል። የነዚህ ፓርቲዎች የክልል መዋቅር ባጠቃላይ በመንግስት እንዲፈራርስ ተደርጓል። በኢህአዴግ ጊዜ ይደረግ እንደነበረው ፓርቲዎች ውስጥ ሰርጎ ገብ በማስገባትና እርጥባን በመወርወር ፓርቲዎችን የማፈራረስ ስራ በስፋት ይታያል። አማራጭ ሃሳብ የሚያቀርቡ ሚዲያዎች ባጠቃላይ ተዘግተው “ከአመት አመት አንተን ነው ማየት” የሚሉ አምልኮተ-አብይ ውስጥ የገቡ ብቻ ቀርተዋል።
 
አዴ ብርቱካን እየሆነ ያለውን መረዳት አንደማያቅታቸው ግልፅ ነው። በተመሳሳይ የፈጠራ ክሶች የተንገላቱ የኢህአዴግ ገፈት ቀማሽ እንደነበሩ ይታወቃል። ቢያንስ ጃዋርና ኦፌኮ በኦሮሚያ ባደረጉት rally ምን ያህል ማህበራዊ መሰረታቸውን እንዳንቀሳቀሱ አይተዋል። ጥያቄው አዴ ብርቱካን ይህንን ፌዝ አይተው እንዳላየ ማለፍ እንዴት ተቻላቸው ነው። ለዚህ መልስ መስጠት የሚችሉት እሳቸው ብቻ ናቸው። ዋና ዋና የሚባሉት የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በዚህ ሁኔታ ከጨዋታው እንዲወጡ በተደረገበት ሁኔታ በምን አይነት መንገድ ነው ቦርዱ ነፃ ፍትሃዊና ፉክክር የሚታይበት ምርጫ ማስፈፀም የሚችለው?! በእውነቱ ከሆነ አብይ ብርቱካን ለተቃዋሚ ያደላሉ የሚል ንግግር ለምክር ቤቱ ሲናገር ነበር መልቀቅ የነበረባቸው። ሰውየው reverse psychology እየተጫወተ እንደሆነ ግልፅ ነው። የተፈለገው አዴ ብርቱካን የተቃዋሚ ደጋፊ አለመሆናቸውን ለማሳየት ለብልፅግና እንዲሳሱ ማድረግ ነው። ለጊዜው የብርቱካንን integrity ጥያቄ ውስጥ መክተት ባልፈልግም ሰውየው ተሳክቶለታል ቢባል ማጋነን አይሆንም። በግላቸው espouse የሚያደርጉት የፖለቲካ አቋም አመራራቸው ላይ ተፅእኖ አድርጎ ካልሆነ በቀር አሁን ባለው ሁኔታ ምድር ከፍ ሰማይ ዝቅ ቢል ብርቱካን ነፃ ፍትሃዊና ፉክክር ያለበት ምርጫን ማካሄድ አይቻላቸውም። የብልጥግና ፓርቲንና የብልጥግና ካዳሚ ፓርቲዎችን አወዳድሬ አብይን መልሼ አነግሳለሁ ካሉ ግን ጥሩ ስማቸውን የሚያጎድፍ ተግባር መሆኑን ለማሳሰብ እወዳለሁ። ጥያቄው ቀላል ነው። ማና ማንን አወዳድረው ነው አሸናፊውን የሚለዩት? ይህንን ተገንዝበው በጉዳዩ ላይ የሚሉት ነገር ካለ እንጠብቃለን።
FI THE FINFINNE INTERCEPT