አጃይብ ነው: ሕወሓቶች በሀሰተኘ ዘገባቸው መቀሌ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ

Ethiopia: አጃይብ ነው። ሕወሓቶች በሀሰተኘ ዘገባቸው መቀሌ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራታቸው ምን ያህል በፖለቲካ ኪሳራ እየተንገዋለሉ መሆኑን በቂ አመላካችም ነው።

በደህንነት ሹሙ ሳይታለም የተመለመለው ኦቦ ለማ መገርሳ ጠቅላይ ይሆናል የሚለውን ሰምተን እጃችንን ከመዳፋችን ሳናጋጭ አሊያን አሽሟጠን ሳንጨርስ ሕወሓቶች በሀሰተኘ ዘገባቸው መቀሌ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራታቸው ምን ያህል በፖለቲካ ኪሳራ እየተንገዋለሉ መሆኑን በቂ አመላካችም ነው። ሕዝቡ በወያኔ ድራማ ላይ በቂ ግንዛቤና ንቃት ያስፈልገዋል። በርካቶች በተደጋጋሚ በሚለቀቁ የውሸት ወሬዎች እውነት መስሏቸው ሲሸወዱ እያየን ነው።

ሳኢዲ አረቢያ ኤምባሲ በር ላይ ስለ ወገኖቹ ሰልፍ የወጣን ኢትዮጵያዊ በቆመጥ ያራወጡት ሕወሓቶች ፣በአማራ ክልል በተደረገ ንቅናቄ በጥይት ለተፈጁ ሰማእታት ሰልፍ የወጣን ወጣት በጥይት የፈጁት ፣ ስለ ኦሮሞ ሕዝብ እልቂት የጮሐን የኦሮሞ ወጣት በጥይት የቆሉ ሕወሓቶች በሐሰት ፕሮፓጋንዳ ጅጅጋ ላይ ታሞ የሞተን ፤ ሐረር ላይ በመኪና አደጋ የሞተን ነቀምት ላይ በድንጋይ ተደብድቦ ሞተ በሚል የውሽት ወሬያቸው የትግራይን ህዝብ ከሌሎች ለመለየትና ቂም ለማስቋጠር የሚያደርጉት ጥረት ስኬት ግብዓት ሰላማዊ ሰልፍ መጥራታቸው የፖለቲካ ድራማቸው እንደተበላበት አለማወቃቸው ምን ያህል እንደከሰሩ ስራቸው ምስክር ነው። የተረጋገጠ መረጃ ይፋ ማድረግ ሲገባ በተዛባ መረጃ ሕዝብን ማሳሳት የሕወሓት ዋና ተግባር መሆኑ የታወቀ ነው።

ሓይለማርያም ደሳለኝ ነጠላ ቢስ ነው የሚሉት ሕወሓቶች በተለያየ ጊዜ የስድብ ውርጅብኝ ሲያወርዱበት ነበር ፤ ጠረጴዛ ደብዳቢው ደብረጺሆን እንዲተካው በሕወሓት ውስጥ ግፊቶች እንዳሉ ይታወቃል። ሆኖም ሕወሓት የጀመረችውን ሀገር የመበታተን ስራ ለማሳካት መስመሯን ሊያቃናላት የሚችለው ኦሕዴድ ብቻ ስለሆነ ሃይለማርያምን በኦሕዴዶች ለመተካት ወገቧን አስራ እየሰራች ነው። ይህ ጉዳይ ሰፊ መረጃ እየተሰበሰበበት ስለሆነ ወደፊት ተመልሶ መምጣቱ ሳይሻል አይቀርም።

ሕወሓት ብአዴን ኦሕዴድ እየባሉ ነው የሚለው የስልጣን ሽኩቻው ወደ አንድ ስልቻ መጥቶ እየተስተካከለ መሆኑ እየተነገረ ነው። ሕወሓት በዝበዝ የምትችልበት መንገድ በሱማሌ ክልል ያለው የሕገወጥ ንግዶች በሙሉ በድል አጠናቃዋለች። በኦሮሚያ ክልል ኮንትሮባንድ አላሳልፍ ቢሉ ጅጅጋ ድረስ አምጥቶ በኤሮፕላን ወደ መሃል ሃገርና ሰሜን ኢትዮጵያ ማሰራጨትም እንደሚቻል ሕገወጥ ነጋዴ ወታደራዊ ጄኔራሎቹ በተግባር እያሳዩን ነው። ሌላም ሌላን ብዙ ነው። አጃኢብ ያሰኛል። ስለሃገርና ስለ ህዝብ ደንታ ቢስ የሆኑ የኢሕአዴግ ባለስልጣናትን ከስልጣን አባሮ በምትኩ በሕዝብ እኩልነት የሚያምን ስርዓት መመስረት የሁላችንም ኃላፊነት ስለሆነ በጋራ እንቁም።

Via: MinilikSalsawi

መቀሌ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ