Ethiopia: አለም በሞላ ልመክረን ሞከረ ግን አልቻለም! ለምን?

Ethiopia: አለም በሞላ ልመክረን ሞከረ ግን አልቻለም! ለምን?
 
“You can lead the horse to the water, but you can’t make him drink”
አብይ አህመድ አንገቱ በማሰሮ ዉስጥ እንደተቀረቀረ ድመት ነዉ፡፡ ለመዉጣትም ለመራመድም ለመጣልም ለመቀጠልም ሁሉንም ወደማይችልበት ደረጃ ወርዷል፡፡ ግዜ ሳለ ምክርን በመናቁ ዛሬ በአዙሪት ዉስጥ ተቀርቅሮ ሀገርቷንም የማትወጣበት ቅርቃር ዉስጥ ከተዋታል፡፡ የምገረመዉ የዚህ ህመመተኛ እና ህጻን ድንግርግር መሪ ሳይሆን ካዚህ በፊት ግፋ፤ በለዉ፤ግደለዉ፤ቁረጠዉ፤ስቀለዉ፤ ስሉ የነበሩ ጨለምተኛ ስግብግብ ነፍጠኞች ዛሬ ላይ ከደሙ ንጹህ ነን ለማለት የክስ ናዳ ማዉረዳቸዉ ነዉ፡፡ ሀገር ሀገር እያሉ ሀገርን የሚያፈርሱ ከሃዲያን በህዝብ አይን ፊት እንዳልነበሩ አይናቸዉን በጨዉ ታጥበዉ ንጹኃን መስሎ መቅረባቸዉ ደብል ሰታንደርድ መሆናቸዉን በጉለህ ያሳያል፡፡ ብሄር ብሔረሰቦች ሁሉንም በጥሞና እያዩ ነዉ፡፡ ሁሉም ለትግሉ ራሱን እያዘገጀ መሆኑ ግልጽ ነዉ፡፡ የባሰ ቀን ሳይመጣባችሁ ወደ ልቦናችሁ መመለስ ጥቅሙ ከሁሉ በላይ ለራሳችሁ እና ለራሳችሁ ነዉ፡፡
“God help those who help themselves”

በሚቀጥለው ስለ አቶ ሌንጮ ለታ፣ ሌንጮ ባቲ እና ዶ/ር ዲማ ነገዋ ስሙን መጥቀስ ከማልፈልገው የብልፅግና ባለስልጣን ከሆነ የልጅነት ጎደኛዬ ጋር ስንጨዋወት የነገረኝን ለእናንተ አካፍላለው ባልኩት መሰረት ዛሬ ይዤ ቀርቤያለው።
.
እኔ – “የሌንጮ ለታ እና የዲማ ነገዋ ጉዳይ እንዴት ነው?” አልኩት
.
እሱ – “እነሱ እኳ የብልፅግና የእደጋ ግዜ ተጠሪዋች ናቸው” አለኝ እየሳቀ።
.
እኔም – “ምን ለማለት ፈልገህ ነው የአደጋ ግዜ ተጠሪ ስትል” ብዬ ጠየኩት
.
እሱም – በቃ ኦሮሚያ ላይ ችግር ሲከሰት ይጠሩና “በቲቪ ወይም በጋዜጣ ላይ ሄዳችሁ አብይን በመደገፍ መልስ ስጡ” ይባላሉ። እነሱም ይህን ትእዛዝ ተቀብለው እንደተነገራቸው ይተግብሩታል። በሌላ ቋንቋ በኦሮሚያ የብልፅግና የእሳት ማጥፊያ መኪና ናቸው አለኝ።
.
እኔ – “ለምሳሌ ይህ የአደጋ ግዜ ተጠሪነት ስራ ምን ምንን ያካትታል” ብዬ ጠየኩት
.
እሱ – የአደጋ ግዜ ተጠሪነት ስራ የቄሮን ትግል ማኮላሸት፣ የኦሮሞ ነፃነት ጦርን (WBO) ስም ማጥፋት፣ ስለታሰሩት እና ስለሞቱ ሰዋች አለማውራት፣ አብይን አለመቃወም ወይም ድጋፍ መስጠት ነው።
.
እኔ – “በአንተ አስተያየት እስካሁን ለብልፅግና የሰሩት ስራ አመርቂ ነው ብለህ ታስባለህ? “
.
እሱ – “ችግሩ ድሮ በኦሮሞ ማህበረሰብ ውስጥ የነበራቸው ተሰሚነት ተሟጦ እንዳለቀ እና ተፆእኖ መፍጠር እንደማይችሉ አውቀዋል። ብልፅግና ጋርም ሙሉ በሙሉ ተአማኒነት የላቸውም። በጥርጣሬ ነው የሚታዩት። ብልፅግና እና የኦሮሞ ህዝብ ላይታረቅ ተጣልቷል። እነሱ ደግሞ ሁለቱንም ማስቀየም አይፈልጉም። ብልፅግናን ይፈራሉ። የኦሮሞን ህዝብ ይፈራሉ። ከሁለት ያጣ ጎመን ሆነዋል። ለዚህ ነው ፈራ ተባ፣ ብቅ ጥልቅ ሲሉ የሚውሉት። እራሳቸውን መሆን አልቻሉም። ስለዚህ እስካሁን ስራቸው አመርቂ አይደለም።
.
እኔ – “መቼም ይህን የካድሬነት ስራ በነፃ አይሰሩም። የቤት ኪራይ ገንዘብ እና ደሞዝ ይሰጣቸዋል ወይ?” ብዬ ጠየኩት።
.
እሱም – “የቤት ከራይ ገንዘብ አንሰጣቸውም። የመንግስት ቤት ውስጥ ነው በነፃ የሚኖሩት። ደሞዝ ግን እንከፍላቸዋልን” አለኝ።
.
እኔም – “በየወሩ ነው እየመጡ ተሰልፈው ደሞዛቸውን ፈርመው የሚቀበሉት?” አልኩት በመገረም።
.
እሱ – “አሁን እኮ ትንሽ በቴክኖሎጂውም ሰልጠን ብለናል። ስለዚህ በባንክ አካውንታቸው ነው ገንዘቡን የምናስገባላቸው። እንደድሮ እንዳይመስልህ” አለኝ ከሀገር ከወጣው ረጅም ግዜ እንደሆነ ስለሚያውቅ።
.
እኔ – “የሌንጮ ባቲስ ጉዳይ? “
.
እሱ – “በጠቅላይ ሚኒስትሩ ዙርያ ያሉት ሰዋች ብዙም አይወዱትም። ለዚህ ነው የአንባሳደርነት ማእረግ ተሰቶት ከሚኒሊክ ቤተ መንግስት ርቆ ወደ ሳውዲ አረቢያ እንዲሄድ የተደረገው። አምባሳደር ቢሆንም አሁንም የአደጋ ግዜ ተጠሪነት ስራውን ግን በተደራቢነት ተግቶ ይሰራል” አለኝ እየሳቀ።
.
እነዚህን ሶስት ሰዋች ከዚህ በፊት ለኦሮሞ ህዝብ ትግል ያበረከቱትን አስተዋፆ እና አሁን ያሉበትን ሁኔታ አስቤ አዘንኩ። በበስተርጅና ግዜያቸው ታች ወርደው እና የብልፅግና ተላላኪ ሆነው፣ ከጀርባቸው ደግሞ ካድሬዋች “የእሳት ማጥፊያ መኪኖች” እያሉ ያሾፉቡባቸዋል ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር። ለማንኛውም እነዚህን ሶስት ሰዋች በቲቪ መስኮት ብቅ ብለው ስታይዋቸው የአደጋ ግዜ ተጠሪነት ስራቸውን እያከናወኑ እንዳለ እንድታውቁ ብዬ ነው።
.
ፈልመታ ቢያ