ESAT Daily News Amsterdam March 22,2018

ESAT Daily News Amsterdam March 22,2018

በሶማሌ ክልል ከሚገኙ 16 የጉምሩክ ጣቢያዎች 38 ሃላፊዎች ስራ እንዲያቆሙ ታዘዙ 34 ቱ የትግራይ ብሄር ተወላጅና የኮሎኔልነት ማዕረግ ያላቸው ናቸው። (ኢሳት ዜና ማጋቢት 13 ቀን 2010 ዓ/ም) ምንጮች እንደገለጹት እነዚህ የኮሎኔልነት ማዕረግ ያላቸው አዛዦች ከመከላከያ በጡረታ ከተገለሉ በሁዋላ ያለ ትምህርት ደረጃቸው በትዕዛዝ ብቻ በመላ አገሪቱ ባሉ የጉሙሩክ መስሪያ ቤቶች ተቀጥረው ላለፉት 8 ዓመታት ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ ሲመዘብሩ ቆይተዋል። ዛሬ የትምህርት ደረጃችሁ ስለማይመጥን ከስራ ተቀንሳችሁዋል የሚል ደብዳቤ የደረሳቸው ወታደራዊ አዛዦቹ፣ በፌደራል ፖሊሶች ይተካሉ ተብሎ ይጠበቃል። ትዕዛዙ በመላ አገሪቱ በሚገኙ የጉምሩክ ጣቢያዎች እንደተላለፈም ምንጮች ገልጸዋል። ሁሉም በሃብት ላይ ሃብት የደረቡ በመሆኑ ቅነሳው ይጎዳቸዋል ተብሎ አይጠበቅም። በሶማሊ ክልል ከሚገኙ የጉምሩክ ጣቢያዎች ውስጥ ስራ እንዲያቆሙ ደብዳቤ ከደረሳቸው 38ቱ ኮሎኔሎች ውስጥ 34 ትግሬ፣ 1 አማራ፣ 1 የኦሮሞና 1 ጉራጌ ሲሆኑ፣ የአንደኛው ብሄር አልታወቀም

ESAT