ESAT Daily News Amsterdam January 16,2018

ESAT Daily News Amsterdam January 16,2018

Ethiopia ዶክተር መረራ ጉዲና አይፈታም ጉዳዩ የሚታየው ከኢሕአዲግ ጉባዬ በኃላ ነው ። ዶ/ር መረራ ይፈታሉ የተባለው በስህተት ነው ሲል ነገሪ ሌንጮ መግለጫ ሰጥቷል ።

ህወሃት መራሹ ቡድን ማጭበርበሩን አጠናክሮ ቀጥሏል የተፈጠረበትን አጣብቂኝ አጭበርብሮ ለማለፍ ቀደም ሲል የፓለቲካ እስረኞችን እፈታለሁ ካለ ቡሃላ እንደገና መልሶ የፓለቲካ እስረኞች የሉኝም በማለት መካዱ ይታወሳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም እንደገና በድጋሜ ሰሞኑን የፓለቲካ እስረኞች ይፈታሉ በሚል አስገራሚ መግለጫ መስጠቱን ተከትሎ የዶክተር መረራ ጉዲና ክስም መቋረጡ እና በነገው እለት ሮብዕ ይፈታሉ የተባለ ቢሆንም በዛሬው እለት የኮሙኒኬሽን ሚኒስተሩ ዶክተር ነገሬ ሌንጮ ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ዶክተር መረራ ጉዲና አሁን አይፈታም የርሱ ጉዳይ ከሁለት ወር ቡሃላ ነው የሚታየው የሚል አሳዛኝ መግለጫ ሰጥቷል ።

ህወሃት መራሹ ቡድን በተለይም በኦሮምያ እና አማራ ክልል ላይ የተፈጠረበትን ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞና ቅራኔ በዘዴ ለማለፍም ታድሻለሁ እስረኞችን እፈታለሁ ማእከላዊን እዘጋለሁ በሚል የማደናገሪያ ተከታታይ መግለጫ ቢሰጥም ይሄ መግለጫ በተሰጠ ማግስትም በርካታ ዜጎች ስርአቱን ተቃውማችሗል በሚል ወደ እስር ቤቶች እየተጋዙ ይገኛሉ

#BBN #MinilikSalsawi