ESAT Daily News Amsterdam January 15,2018

ESAT Daily News Amsterdam January 15,2018


Hiber Radio Daily Ethiopian News January 15, 2018


A prominent Ethiopan opposition leader is among those to be released from prison following a government call for dialogue, but there is demand for further change

የትግራይ ነፃ አውጪው ህወሃት መናቆር ተባብሷል! የወያነ ሰዎች በመቀሌ ስብሰባ ላይ ስልክ ይዘው እንዳይገቡም ተከልክሏል::

Etiopia : የመቀሌው ኮንፈረስ ችግር ከመቅረፍ ይልቅ አለመተማመን መጠራጠር ቡድናዊነት እና ከሁዋላ መወጋጋት ነግሶነታል። የደብረጺዮንን የዝሙት ሚስጥሮችን ኢሳት ካፈነዳው በሁዋላ የኮንፈረንሱ ተሳታፊ ዋነኛ የሹክሽታ ርእስ በመሆኑ ደብረጺዮን ተረጋግቶ አመራር መስጠት ተስኖታል። እንደውም ታመምኩ እያለ እንደሚሰወር ይነገራል። በህወሃት መሪነት የመቀጠሉም ጉዳይ አጠያያቂ ሲሆን አንዳንዶች ጉዳዩ ሃሰት ከሆነ በይፋ እንዲይስተባብል ቢጠይቁትም አጥጋቢ መልስ መስጠት ተስኖታል። በይፋ ለማስተባበልም አቅም ማጣቱ ግልጽ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አንዱ በሌላው መረጃ ማሾለኩን ቀጥሏል። ሚስጥራዊ የህወሃት ማእከላዊ ኮሚቴ የግምገማ ቃለ ጉባኤ በሃዱሽ ካሱ ፌስ ቡክ ላይ ተለቋል። ከትግሪኛ ወደ አማርኛ አስተርጉመን በቅርቡ እንለቀዋለን ኢሳት ላይም በዝርዝር እንደሚገመገም ይጠበቃል። 

የመሪዎቹም ሆኑ ከድሃው አንጡራ ሃብት ለጥቃቅን የፌስቡክ እና የብሎግ እንቅስቃሴዎች በሺ የሚቆጠር ብር የሚከፈላቸው ቅልብ የህወሃት የሽልንግ ሰራዊት አባላት የሆኑት እነ ዳንኤል ብርሃኔ፣ ዳዊት ከበደ (እነሱ እንዳሉት ይሁዳው) እነ ዘርአይ፣ ፍጹም ብርሃኔ ሳባዊ እና መሰሎቻቸው ሳይቀሩ እየተናቆሩ ነው። የትግራይ የህዝብ ግንኙነት ሃላፈው ገብረሚኪያኤል መለስ እና የፈዴራል ኮሚዩኒኬሽን ካድሬው ሃዱሽ ካሱ ትልቅ እራስ ምታት ገጥሟቸዋል። መናቆሩ ተባብሷል! ዘርአይና ዳንኤል ብርሀነን ጨምሮ አብዛኞቹ የትግርኛ ተናጋሪ ብሎገሮች እነሆ ከሶሻል ሚዲያ ከጠፉ ዛሬ አምስተኛ ቀናቸውን ይዘዋል::


ህወሀት ተዝረክርኳል። ገመናው አደባባይ ተሰጥቷል። በታሪኩ እንዲህ ሆኖ የሚያውቅ አይመስልም። ድብቁ ህወሀት መለመላው ተገላልጦ መታየት ጀምሯል። የመሪዎቹን ቅሌት በየዕለቱ አጀብ እያልን እየተከታተልን ነው። ፍትህ ቢኖር ኖሮ የደብረጺዮን ቅሌት ወንበሩን በማስለቀቅ የሚቆም አልነበረም። ጸጉሩን ተላጭቶ ቀሪ ዘመኑን በእስር ቤት ይጨርሳት ነበር። እዚህ አሜሪካን ተሻሸኝ፡ጎነተለኝ የሚሉ ሴቶች ስንቱን ታላላቅ ፖለቲከኛ ከጨዋታ ውጪ እንዳደረጉ ሰሞኑን ታዝበናል። የወሲብ ብልግና ምህረት የሌለው ወንጀል ነው። አሜሪካን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያመሳት ያለ ጉዳይ ይሀው የወሲብ ቅሌት ነው። ትራምፕን ከኋይት ሁውስ ያፈናቅላሉ ተብለው ከሚጠበቁ ጉዳዮች አንዱ የትራምፕ ቅጥ ያጣ የወሲብ ህይወቱ ነው።

የደብረጺዮን ግን ይለያል። የደሀ ህዝብን ገንዘብ ለዝሙት አዳሪዎች የሚያከፋፍል መሆኑ ሃጢያቱን ከፍ ያደርገዋል። የደበረጺዮን ዓይነት ዓለም ዓቀፍ ተዘዋዋሪ የወሲብ ልክፍተኛ እዚህ አሜሪካ እጅ ከፍንጅ ቢያዝ የሚገጥመውን መገመት ቀላል ነው። ደብረጺዮን ግን አይኑን በጨው አጥቦ ከረባቱን ገጭ አድርጎ ”ጥልቅ ተሀድሶ፡ ስምጥ ግምገማ” እያለ ማለዘን እንጂ ከቦታው ንቅንቅ የሚል አይመስልም። ግን ማን ነው ይህን ገበና እያጋለጠ ያለው? ህወሀት እንዴት መቆጣጠር ተሳነው? የእርጅና ምልክት ሊሆን ይችላል። ጨቋኝ ስርዓቶች የመጨረሻው ዙር ላይ መዝረክረካቸው የተለመደ ቢሆንም የህወሀት ግን ያስደነግጣል። ያሳፍራል። ስለኢትዮጵያ ወደ ውስጥ ያስለቅሳል።

በእርግጥ የተመታው የአባይ ወልዱ ቡድን ቅሌቶችን መዘርገፍ መጀመሩን የሚያመላክቱ ፍንጮች አሉ። ጋዜጠኛ አበበ ገላው ያጠናቀረው ሰፊ ዘገባ ላይ እንደተብራራው የአባይ ወልዱ ካቢኔ አባል የሆነ በስም የተጠቀሰ ግለሰብ ቅሌቶቹን እየዘረገፋቸው ነው። መጀመሪያ ላይ ሀክ ወይም የተሰበረ የመረጃ ፍሰት እንደሆነ ተገልጾ ነበር። በኋላ ላይ ተጨማሪ መረጃዎች ሲወጡ ግን ሆን ተብሎ እንደሆነ የሚያረጋግጥ ነው። የሚወጡት መረጃዎች የግለሰብን ገበና ከማጋለጥ ባለፈ በሀገር ላይ እየተፈጸመ ያለውን ሸፍጥ እስከዛሬ በምናውቀው ላይ ተጨማሪ ነው ማለት ይቻላል።

የደብረጺዮን ቅሌት የህወሀት መሪዎችን በሙሉ የሚመለከት ነው። ነገ ከነገ ወዲያ የሌሎቹንም መስማታችን አይቀርም። የጫካ ብልግናቸው ቤተመንግስት ድረስ ሰተት ብሎ ገብቷል። ሚስት ሲቀማሙ፡ የአንዱን አንዱ እየመነተፈ አንሶላ ሲጋፉ የኖሩ፡ በስተርጅና ”ሹገር ዳዲ” ሆነው የስንቷን ኢትዮጵያዊት ህይወት አጉል ያደረጉ መሆናቸው ሚስጢር አይደለም። በኢትዮጵያ አርዓያ የሚሆን አንድ መሪ መጥፋቱ ያሳዝናል። ህጻናት እያዩ የሚያድጉት፡ ነገን ብሆን ብለው የሚመኙት ማጣታቸው፡ አርዓያ፡ ሞዴል አድርገው እያከበሩት የሚደርሱበት አንድ ባለስልጣን አለመኖሩ በመጪው ትውልድ ህይወት ላይ ክፍተኛ የሞራል ክስረት እንዳይፈጥር እሰጋለሁ።

መቼም ሃይለማርያምን እያየ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን የሚመኝ ህጻን አይኖርም። የሳሞራ የኑስን ሞራል አልባ፡ ድንቁርና የሸበበው ጄነራልነት ”ነገ ሳድግ ብሆነው” ብሎ የሚናፍቅ ልጅ አይገኝም። የደብረጺዮንን የወሲብ ቅሌት እየሰማ የቴክኖሎጂ ሚኒስትር ለመሆን የሚጓጓ ትውልድ ይኖር ይሆን? ህወሀቶች ትላንትን ማጠልሸታቸው፡ ዛሬን ማጨቅየታቸው ብቻ ሳይሆን ነገንም ለማጨለም መትጋታቸው ሲታሰብ ወንጀላቸውን ምህረት የማያሰጠው ያደርገዋል።

በተረፈ እየወጡ ያሉት ውስጣዊ መረጃዎች የህወሀትን መዝረክረክ በግልጽ ያሳያል። መዝረክረክ የውድቀት አቋራጭ መንገድ ነው። የሚቆም አይመስልም። ህወሀት መንደር አንድነቱ ተንዷል። ሚስጢር በማሾለክ፡ ገበናን ለአደባባይ በማስጣት መጠቃቃት ተጀምሯል። ጥርጣሬው ሰፍቷል። ሽንቁር ወጥቷል። ቀዳዳ ተፈጥሯል። የሚደፈን አይሆንም። የበለጠ እየሰፋ እንደሚሄድ ጥርጥር የለውም። በስብሰባ፡ በግምገማ፡ በህንፍሽፍሽ፡ በልመና፡ በሽምግልና፡ በየትኛውም መንገድ የሚቆም አይመስልም።

Mesay Mekonnen