#DireMassMedia
በድሬዳዋ አስተዳደር የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር የተቋቋመው ግብረኃይል ዛሬ ተጨማሪ ውሳኔዎችን አስተላልፏል:
ከነገ መጋቢት 23/2012 ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆኑ የተላለፉ ውሳኔዎች:-
1- ወደ ድሬዳዋ ከተማ የሚገቡም ሆነ የሚወጡ ከፍተኛ እና መለስተኛ ሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፓርት አገልግሎት ዝግ ሆኗል::
2- ማንኛውም አይነት የድሬዳዋ ከተማ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ከባጃጅ እስከ ሚኒባስ ላልተወሰነ ጊዜ ምንም አይነት አገልግሎት መስጠት እንዲያቆሙ::
3- በየትኛውም አቅጣጫ የሚገኙ የድሬዳዋ መግቢያ በሮች ከነገ ጀምሮ ከእንቅስቃሴ ዝግ ተደርገዋል::
4- የእለት ተእለት መሰረታዊ ፍጆታ እቃዎችን መሰረት ያደረጉ የግብይት ስፍራዎችን ሳይጨምር እንደ ታይዋን አሸዋ እና ሌሎችም የገበያ ቦታዎች ከነገ ጀምሮ ዝግ እንዲሆኑ ተወስኗል::
5- ከፍተኛ የሰው ኃይል ያላቸው ፋብሪካዎች እረፍት በመስጠት እና በሽፍት በማሰራት የሰው ኃይል ቁጥር እንዲቀንሱ ተወስኗል::
መግለጫ:- በጅቡቲ መስመር እና በሌሎች መግቢያዎች የሚገቡ የተለያዩ ለሀገር ጠቃሚ የሆኑ ነዳጅ እና እህልን ጨምሮ ሌሎች የሎጂስቲክ እንቅስቃሴዎችን ይህ ክልከላ አይመለከትም::
በመጨረሻም ግብረኃይሉ በመልእክቱ ከላይ የተዘርዘሩትን ውሳኔዎች መላው የድሬዳዋ ህብረተሰብ እና የፀጥታ አካላት ተግባራዊ እንዲሆን በማድረግ የኮሮና ቫይረስን በመከላከል ሂደት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ አሳስቧል::
አሰግድ ከድር