Dhugaa Kana Beektuulaa?Qoree irraa ija harbuu akka eeguti!!

Dhugaa Kana Beektuulaa?
(By SG)
——————-
#Mehaazaa_Ashannaafii irraa waan gaariin eegamu hin jiru. Qoree irraa ija harbuu akka eeguti. Heera mootummaa kana diiguun hawwii ishee ganamaati.
Sababiin isaa isheen kutaa Wallaggaa durii Asoosaatti dhalattee, boodaarra haatii ishee ijoollee fudhattee Mandiitti galte. Achi irraa Najjoo irraa Finfinneetti galaan. Afaan Oromoo akka afaan dhalootaatti

Dubbaatti. #Hiddaan_garuu_haadhanis_abbaanis_amaara. Haatii ishee kan Qixaawu Ijjiguuti. Isaan kun nafxaanyaa dur gara kutaa Wallaggaatti ergamanii sirnicha tajaajilaa turaniidha. Qajeellootti nan beeka. Kanaaf waan gaarii qabattee as baate abdii jedhu hin qabu. Terguwamim asterguwamiwun yandi santim getsita nachewu.
#Simbirtuubarii irraa

#Inbox

“ህሊና ቢስ “ምሁራን”
“የኢትዮጵያ “ምሁራን (የ ዩነቨርስቲ መምህር ነኝ)” በመንግስት ሚዲያ እየቀረቡ ያልተጻፈ የሚያነቡ ህሊናቸውን የሸጡ ደንቆሮዎች ናቸው፡፡ “ምሁርነት” ያልተነገረን ነገር በሚዲያ እየወጡ ህዝብን ማሳሳት ከሆነ ከዚህ በላይ ወንጀል ከየት ይመጣል፡፡ የሀሰተኛ መረጃ ህግ ፤ የጸረ ሽብር ህግ ወዘተ እያሉ መንግስትን በሚደግፍ መልኩ መተርጎም ላለፉት 30 አመታት የተለማመድናቸው እውነታዎች ናቸው፡፡ የዚህ አይነቶቹን ግደፈቶች ምሁራን ተብዬዎች ፊት ማይክ ደቅነው ኢንተርቪው የሚያደርጉት ሆድ አደር ጋዞጠኞችም የሙያ ስነምግባራቸውን አክብረው ሊያርሙዋቸው (በጥያቄያቸው) አይሞክሩም፡፡ የዚህ አይነቱ የሀሰት ፕሮፐጋንዳ ማሽኖች የተለያየ አጀንዳ በየውቅቱ እየፈጠሩ ህዝቡን ማደናገር ስራቸው አስኪመስል ድረስ ህዝብን-ከህእብ ፣ መንግስትና ተቃዋሚን፣ መንግሰትና ህዝብን ለማናከስ ሁሌም በመሽቀዳደም ላይ ናቸው፡፡ ሚዲያዎቹ እና “ምሁራን ፣ የሰባዊ መብት ተሟጋች ነን” የሚሉት በህይወት ያለን ሰው ሞተ፤ ያለታፈነን ተማሪዎች ታፈኑ ያዙን ልቀቁን፤ የልተዘረፉትን የሀይማኖት አባት ተዘረፉ ተደበደቡ፤ አከሌ ከግብጽ ጋር አየሰራ ነው ወዘተ በሚሉ ሀሰተኛ ወሬዎች የሸረቡዋቸው ሴራዎች ለምን እንደነበርና እንደ ሆነ ሕዝብ ጠንቅቆ ያውቃል፡፡

አሁንደግሞ በዚህ ሰሞን ከህውሀት በስተቀር አንድም ተቃዋሚ ፓርቲ ምርጫው አሁን መደረግ አለበት ብሎ ባልሞገተበት ወቅት ፤ መንግስት ብቻውን የምርጫ መራዘሙን አስፈላጊነት እንዳመነበትና ተቃዋሚዎች በደፈናው (ኮረና ኖረ አልኖረ) ምረጫው የግድ አሁኑኑ መደረግ እንዳለበት ሀሳብ ያቀረቡ አስመስለው በማቅረብ ሀሰተኛ መረጃዎችን በሚዲያ ሲቸረችሩ ማየት እጅግ በጣም ያሳዝናል፡፡ ምሁር ከሆኑ ተቃዋሚዎች የሚያነሱት ፓለቲካዊ መፈትሄ፣ የሽግግር መንግስት፣ አብሮ መስራት ወዘተን በምክንያት መሞገት ለምን አቃታቸው? ዳሩ ከነኚህ አይነት “ምሁራን” ነን ባዮችና የሀሰት ሱፕረማረኬት ከሆኑ ሚዲያዎች ምንም አይጠበቅም፡፡ በዚች ሀገር ተነጋግሮና ተከራክሮ ልዮነቶችን ለማጥበብና ለመግባባት ትልቁ ተግዳሮትም እንደነኚህ አይነት የውሸት ፈብሪካዎች መኖራቸውና መበራከት ነው፡፡ ህጉም ቢሆን እንደነዚህ ያሉ ቀጣፊዎችን ለማረም ስራ ላይ የሚውል ሳይሆን እውነትን ለማፈን የሚጠቀሙበት መሳሪያ ነው፡፡ በጣም አስገራሚዊ እነኚህ የሀሰት ፕሮፓጋንዳዎች የሚቦኩትና የሚጋገሩት በቤተ-መንገስቱና በዙሪያው ባሉ ሰዎች ነው፡፡
ለሁሉም ቀን ይፋረዳል፡፡ “እውነትና ፀሐይ . . . ” ነውና፡፡”

~from Bore Borena.

Via: Tsegaye Ararssa

የሕገ-መንግሥት አጣሪ ጉባኤ፣ “የሕገ-መንግሥት ትርጉም የሚያስፈልገው ጭብጥ የለም፣ ወይም በሥነሥርዓቱ መሠረት ያልተሟሉ ነገሮች ስላሉ አያስቀርብም” ብሎ ከወሰነ፣ የሚሰጠው ውሳኔ፣ ውሳኔ ነው እንጂ ምክረ-ሃሳብ አይደለም። (በዚህ ውሳኔ ቅር የተሰኙ ወገኖች በቀጥታ ለፌደሬሽን ምክር ቤት ይግባኝ መጠየቅ ይችላሉ።)

ነገር ግን፣ “ጉዳዩ ያስቀርባል፣ ትርጉምም ያስፈልገዋል” ብሎ ካመነና ሊተረጎም ይገባዋል የሚለውን የሕገ-መንግሥቱን አንቀጽ ወይም ድንጋጌ ትርጉም ከሰጠው በኋላ፣ ለፌደሬሽን ምክር ቤት የሚያቀርበው ሃሳብ አስገዳጅነት ያለው ውሳኔ ሳይሆን “የውሳኔ ሃሳብ” ነው።

ላብራራው፦

የሕገመንግሥት አጣሪ ጉባኤ፣ “ትርጉም አያስፈልግም” ብሎ ከወሰነ፣ በውሳኔው ቅር የተሰኙ ባለጉዳዮች ያላቸው የይግባኝ መብት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የሚሰጠየው ብይን፣ ውሳኔ ነው። እንደ ውሳኔም አስገዳጅነት ይኖረዋል።

ጉባኤው፣ “ትርጉም ያስፈልጋል” ብሎ፣ አንቀጾቹን ከተረጎመ ግን፣ ለፌደሬሽን ምክር ቤት የሚያቀርበው ትርጉም፣ የውሳኔ ሃሳብ (Recommendation) ነው እንጂ፣ ውሳኔ አይደለም።

ኢትዮጵያ ውስጥ፣ በሕገ-መንግሥት ትርጉም ጉዳይ፣ ውሳኔ ሰጪው፣ (የሕገ-መንግሥቱና የትርጉሙ ባላደራ የሆነው)፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት ነው እንጂ፣ የሕገመንግሥት አጣሪ ጉባኤው አይደለም።

አጣሪ ጉባኤው፣ በሥሙም እንደተጠቆመው፣ ሥራው፣ ማጣራት ነው እንጂ መወሰን አይደለም።

ሕገ-መንግሥቱ፣ ለፌ/ምክር ቤት ሙያዊ የውሳኔ ሃሳብ እንዲሰጥ እንጂ እንዲወስን ሥልጣን አልሰጠውም (ቁ. 83-84 et seq)። እራሱ የመወሰን ሥልጣን ቢኖረውማ ኖሮ፣ የሕገመንግሥት ፍርድ ቤት ይሆን ነበር። አይደለም። አጣሪ ጉባኤ ነው። (አጣሪ የሚለው ይሰመርበት።)

#ለወንድሜ_ታደሰ_ሌንጮ

ትዕይንቱ ክሹፍ ነበር–በይዘትም በቅርፅም!
እንደሰማሁት፣ ዛሬ ስለ ሕገመንግሥት ትርጉም “የሙያ አስተያየት” አቀረቡ የተባሉት ባለሙያዎች፣ አብይ፣ “4ቱ በባለሙያዎች የቀረቡ አማራጮች” ብሎ ለፓርቲዎች ስብሰባ ያቀረባቸውን ሃሳቦች ያዘጋጁት ናቸው። ሁሉም (ከጌታቸው አሰፋ በቀር)፣ በዚህ ባለፈው ሳምንት፣ በAddis Standard እና በ Ethiopia Insight ላይ፣ ዛሬ ያቀረቡትን ምንም ለጭብጡ አግባብነት የሌላቸውን ክርክሮች አንስተው፣ ጭብጥ አልባ ሙግት (arguing a non-issue) ሲያደርጉ እንደቆዩ ይታወሳል።

ጉባኤውም፣ መጠየቅ ያለበትን (“ሕገ-መንግሥቱ ምርጫ ማራዘምን ይፈቅዳል፣ ወይስ አይፈቅድም?” የሚለውን ቀላል ጥያቄ) ትቶ፣ ለጉዳዩ አግባብነት የሌላቸውን ጥያቄዎች ሲጠይቅ ውሏል። ከጥያቄዎቹ አስቂኙ “አንቀጽ 54 cum 58 ከአንቀጽ 93 ጋር ይቃረናሉ፡ ምን ይሻላል?” የሚለው የአቶ ሰለሞን አረዳ ጥያቄ ነው።

ለተፈለገው የቴሌቭዢን ትዕይንት (spectacle) እንኳን እንዲመጥን አድርገው ቢተውኑት ምን ነበር?

PS. አንድ ቁልፍና ወሳኝ ነጥብ (genuinely critical point) አሁን እዚሁ መንደር ላይ ጃዋር አንስቶ አየሁ ልበል? የኔም ጥያቄ፣ አምስቱም (ባልሳሳት ቢያንስ 4ቱም) የቀረቡት ‘ባለሙያዎች’ ከአንድ ብሔር መሆናቸው በአጋጣሚ ነው ብለን እንለፈው?

#The_spectacle_was_a_double_failure!
#ቁልቁል_አደግ_አገር!

ትላንት የወያኔ አምባሰደር የነበር እና የኦሮሞ ልጆችን ሲያስገድል የነበር የትላንቱ ኦፒዲኦ የዛሬዉ “PP” እኔን ለመተቸት ሞራል የለዉም”

✏️ Tsegaye Ararssa PHD የህገ መንግስት ማሻሻያውን በተመለከተ 👇🏽

“በአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ መንግሥት የሚጠቀመው ሥልጣን፣ ሕጋዊ መሠረት ያለው መንግሥት ሥልጣን ነው እንጂ ያልተመረጠ መንግሥት ሥልጣን አይደለም።
=====================
1. በአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ውስጥ፣ አንድ፣ በሕዝብ በተመረጠ ፓርላማ የተሰየመ ሕጋዊ መንግሥት፣ አስቸኳይ ሁኔታውን ያስገደደውን አደጋ ለመቋቋም ወይም ለመመከት እንዲችል፣ የተለየ ሥልጣን ይሰጠዋል።

አደጋውን ለመቆጣጠር አስፈላጊ በሆነ መጠንም፣ አንዳንድ ለመብት እውቅና የሚሰጡ የሕግ ድንጋጌዎችን፣ በተወሰነ ገደብ ውስጥ፣ ለመተላለፍ እንዲችል ይፈቀድለታል።

በምንም ሁኔታ የማይተላለፋቸው ድንጋጌዎችና የማይጥሳቸው መብቶችም በዝርዝር ይቀመጣሉ።

ብቻም አይደለም።

የአስቸኳይ ጊዜ ሥልጣኑን፣ ለተፈለገው ዓላማና በትክክለኛው አግባብ መጠቀም አለመጠቀሙን የሚቆጣጣጠር፣ ይሄንንም ለፓርላማው በዝርዝር የሚያስረዳ፣ የአስቸኳይ ጊዜ መርማሪ ቦርድ ወይም ኮሚሽን ይቋቋማል።

ምንም እንኳን በአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ፣ ለወትሮው የመንግሥትን ሥልጣን በወሰን የሚያቆዩ ገደቦች ላላ (relax) የሚደረጉ ቢሆንም፣ የአስቸኳይ ጊዜ ስላለ ብቻ፣ መንግሥት እንደፈለገ ይሆናል ማለት አይደለም። በአስቸኳይ ጊዜም ቢሆን ለሥልጣን አጠቃቀም ገደብ አለ። የሕዝብ ሥልጣን ይዞ መረን መውጣት አይፈቀድም።
——–

2. በኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት ውስጥ፣ የአስቸኳይ ጊዜን የሚመለከተው አንቀጽም (ማለትም አንቀጽ 93) ይሄንኑ ያረጋግጣል። በዚህም መሠረት፣ አስቸኳይ ጊዜ ሁኔታን በማወጅ፣ መንግሥት (ማለትም ሥራ አስፈፃሚው)፣ ከወትሮው የተለየ ሥልጣን እንዲጠቀም ምክንያት የሚሆኑት፦

ሀ. ጦርነት

ለ. ከወትሮው የሕግ አስከባሪዎች አቅም በላይ ሆኖ፣ ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ውስጥ የሚከት የሕግና ሥርዓት መፍረስ፣

ሐ. የተፈጥሮ አደጋ፣ እና

መ. ወረርሽኝ

ናቸው።

እነዚህ ሁኔታዎች መኖራቸው በተጨባጭ ከተረጋገጠ፣ የምኒሥትሮች ምክር ቤት፣ ይሄን በመግለፅ ያስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጆ፣ በ48 ሰዓታት ውስጥ ለፓርላማው ያሳውቃል። ፓርላማው ካጸደቀው፣ አዋጁ እስከ 6 ወር ለሚሆን ጊዜ ሕግ ሆኖ ያገለግላል። በዚህ ጊዜ ውስጥ፣ ችግሩን መቆጣጠር ካልተቻለ፣ መንግሥት አዋጁን ለተጨማሪ አራት ወራት እንዲያራዝምለት ይጠይቃል።

የመንግሥትን አተገባበር ለመቆጣጠርም አጣሪ ቦርድ ይቋቋማል። ቦርዱም የተከሰቱ መተላለፎችና ተቀባይነት የሌላቸው የመብት ጥሰቶችን ይመረምራል፣ ጥፋቱን የፈጸሙትም እንዲጠየቁ የውሳኔ ሃሳብ ለምክር ቤቱ ያቀርባል።

ጥሰቶች ተቀባይነት አላቸው የላቸውም የሚለውን ለመወሰን ደግሞ፣ ምክንያታዊነትን (rationality, i.e., the existence of causal relations between the violative act and the harm the act was intended to avert)፣ ተመጣጣኝነትን (proportionality)፣ እና የሰብዓዊ ክብርን አይነኬነት (dignity) ከግንዛቤ ይከታሉ።

ይሄም ሆኖ፣ በዚህ ጊዜም እንኳን፣ መንግሥት፣ የማይተላለፋቸው ድንጋጌዎች፣ የማይጥስ-የማያጥፋቸው መብቶች አሉ። እነዚህም፣ በአንቀጽ 93(4) ውስጥ እንዲሚከተለው ተዘርዝረው ይገኛሉ፦

-አንቀጽ 1: የአገረ-መንግሥቱ ኦፊሴላዊ ሥም እና ሥሙ የሚገልጸው (ወይም የተሸከመው) የፌደራላዊ፣ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሥርዓትና የአገረ-መንግሥት አወቃቀር፤

-አንቀጽ 18፡ የሰው ልጅ ሰብዓዊ ክብርን ለማስከበር ዓላማ ተብሎ የተቀመጠ፣ ኢሰብዓዊና ጭካኔ የተሞላበት አያያዝና ቅጣትን ለምስቀረት የተጣለ ክልከላ፤

-አንቀጽ 25፡ የእኩልነት መብትና በማናቸውም ምክንያት የተለያየ አያያዝ እንዳይደረግ የሚከለክል ድንጋጌ፤

-አንቀጽ 39(1)፡ የብሔሮች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት፣ እስከ መገንጠል ድረስ፤

-አንቀጽ 39(2)፡ የብሔሮች የባህል፣ የቋንቋ፣ የታሪክና የማንነት መብት።

(በሕይወት የመኖር መብት ከዚህ የአይነኬ መብቶች ዝርዝር ውስጥ መካተት ሲገባው አለመካተቱ ሥህተት ይመስለኛል።)

ይሄ ሁሉ፣ ከላይ የተቀመጠው ዝርዝር ድንጋጌ፣ የመንግሥት ሥልጣን፣ በአስቸኳይ ጊዜም እንኳን አለገደብ የተለቀቀ ሳይሆን፣ በገደብ ውስጥ ተወስኖ የተቀመጠ መሆኑን ያሳያል።
——-

3. መቼም ቢሆን መረሳት የሌለበት ነጥብ፣ እንዲህ ዓይነቱን የአስቸኳይ ጊዜ ሥልጣን የሚጠቀመው አካል፣ በሕገ-መንግሥቱ ድንጋጌዎች መሠረት በአግባቡ በተመረጠና የሥልጣን ዘመኑም ባላለቀ ፓርላማ የተሰየመ፣ ሙሉ ሕጋዊና ዴሞክራሲያዊ ማንዴት ያለው፣ መንግሥት ብቻ መሆኑን ነው።

በመሆኑም፣ የሥልጣን ዘመኑ ያለቀ ፓርላማ፣ ያስቸኳይ ጊዜ ሥልጣን፣ ለሥራ አስፈፃሚው ለመስጠት አይችልም።

ወይም፣ የራሱንና የሰየመውን መንግሥት የሥልጣን ዘመን ለማራዘም ሲል ብቻ የአስቸኳይ ጊዜ ማወጅ አይችልም። የአስቸኳይ ጊዜ ለማወጅ የሚያስገድዱት ሁኔታዎች ዝርዝር ይሄን አይመለከትምና።

ዘመኑ ባለቀ ፓርላማ የተሰየመ መንግሥትም፣ በአስቸኳይ ሁኔታ ሥም ከተሰየመለት በላይ ስልጣኑን በማራዘም፣ ማገልገል አይችልም።
——–

4. የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ፣ ምርጫን ለመሰረዝ ወይም ለማስተላለፍና የመንግሥትንና የፓርላማን የሥራ ዘመን ለማስቀጠል፣ ምክንያት አይሆንም።

የምርጫ ወቅት፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በታወጀበት ወቅት የሚውል ከሆነ፣ የግድ (ወይም necessarily and automatically) ምርጫን ላለማድረግ ምክንያት ይሆናል ማለት አይደለም።

ለጤና ሲባል የታወጀ የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታም፣ ምርጫን አያስቀርም–በግልፅ፣ በሳይንስ በተደገፈ መልኩ፣ አዋጁን ያስገደደው ምክንያት፣ ከምርጫ ሂደት ጋር ተጨባጭ ግንኙነት እንዳለው ካልተረጋገጠ በቀር።
——–

5. የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመኖሩ ምክንያት የሚገደቡ መብቶችና ድንጋጌዎች እንዳሉ ግልፅ ነው። የማይገደቡም መኖራቸው አይታበልም።

ከማይገደቡ ድንጋጌዎች መካከል ደግሞ አንቀጽ አንድ ዋነኛውና የመጀመሪያው ነው።

በዚህም መሠረት፣ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሥም፣ የአገረ-መንግሥቱን ዴሞክራሲያዊና ፌደራላዊ አወቃቀር መንካት አይቻልም።

ምርጫን በማራዘም፣ ባልተመረጠ መንግሥት ለማስተዳደር መሞከር፣ ዴሞክራሲያዊ አወቃቀሩን፣ ከመሠረቱ መናድ ነው። አይፈቀድም። አያስኬድም።

በተመሳሳይ መልኩ፣ ክልሎች፣ ምርጫ በማድረግ እራሳቸውን የሚያስተዳድሩበትን መንግሥት እንዳያዋቅሩ ማገድ፣ የፌደራላዊ አወቃቀሩን በመናድ፣ ወደ ተማከለ አምባገነናዊ ሥርዓት መመለስ ነው። ይሄም አይፈቀድም። አያስኬድም።

በበሽታ ምክንያት በታወጀ (ያውም በበቂ የህግ አግባብ እንኳን ባልታወጀ) አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሥም፣ የአንቀጽ አንድን ድንጋጌ መተላለፍ፣ በአንቀጽ አንድ ብቻ የሚያቆም አይደለም። ሥልጣን የሕዝብ መሆኑን የሚገልጸውን የዴሞክራሲ መርሕ እና የብሔሮችን ሉዓላዊነት መርሕ (አንቀጽ 8ን)፣ ሕገ-መንግሥታዊነትን (አንቀጽ)፣ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብትን (አንቀጽ 39(1-2)፣ በፌደሬሽን ውስጥ እራስን በራስ ማስተዳደርን (39(3))፣ ወዘተ ይጥሳል።
———–

አንዳንድ የብልጥግና ፓርቲ አጨብጫቢዎች፣ “በአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ውስጥ ስላለን፣ በአንቀጽ 38 የተደነገገውን የመምረጥና የመመረጥ መብት መጣስ ስለሚቻል፣ ምርጫን በአስቸኳይ ጊዜ ሥም ማራዘም ይቻላል” እያሉ ሲከራከሩ ይሰማሉ። (ያላዋቂ ሳሚ ነገር!)

ስተዋል።

ምርጫን ማራዘም ማለት፣ የአስቸኳይ ጊዜ ሥልጣንን የሚጠቀመውን መንግሥት ሕጋዊነት እራሱ መናድ ማለት ነው።

ከላይ እንደገለፅኩት፣ የአስቸኳይ ጊዜ ሥልጣን መጠቀም የሚችለው የሥራ ዘመኑ ያላለቀ ፓርላማ የሰየመው ሕጋዊ መንግሥት ብቻ ነው። ከሥራ ዘመኑ ማለቅ ጋር ተያይዞ፣ የአስቸኳይ ጊዜ ሥልጣኑም ከዋናው የውክልና ሥልጣኑ ጋር ያከትማልና። ዋናው ሥልጣን ዘመኑ አልቆ ካበቃ፣ ተጨማሪው (የአስቸኳይ ጊዜ) ሥልጣን በምን አግባብ (በምን ላይ ተጨምሮ) ይቀጥላል? መልሱ ቀላል ነው፦ አይቀጥልም።

በተጨማሪም፣ ብዙ የዓለም-አቀፍ ሰነዶችም ሆኑ፣ ሰሞኑን አብይ እንኳን ለማጭበርበር ሲል የጠቀሰው የአፍሪካ የዴሞክራሲ ድንጋጌ (Declaration)፣ ምርጫ የሕዝቦች እና/ወይም የአገሮች መብት መሆኑን ያስቀምጣሉ። ሕዝቦች፣ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ (ማለትም፦ ነፃ፣ ፍትሃዊ፣ ፉክክር ያለበት፣ ጊዜውን ጠበቆ፣ በመደበኛነት የሚካሄድ ምርጫ) የማድረግ መብት ከሌላቸው፣ ግለሰቦች፣ የመምረጥና የመመረጥ መብት አይኖራቸውም። The right of nations/peoples to democracy, or to a democratic election (i.e., the right to free, fair, competitive, and periodic elections), precedes the exercise of the right of individuals to vote (in order to elect or be elected).
——–

አስተውል! በአስቸኳይ ጊዜ ሥም፣ ምርጫን በማራዘም የምትጥሰው፣ አይነኬውን የሕዝቦች የዴሞክራሲ መብት (ቁ. 1, 8, 9, 39 (1-3)) ነው። በአስቸኳይ ጊዜ ሥም የምትጥሰው፣ መሠረታዊውን የአገረ-መንግሥቱን ዴሞክራሲያዊ፣ ፌደራላዊ፣ ሪፐብሊካዊ አወቃቀርሩን (Structure) ነው። ይሄን በማድረግም፣ የቆምክበትን መሠረት ነው የምትንደው።

ይሄ ከዚህ በላይ ያለው ነው፣ ትክክለኛውና አዋጭ የሆነው፣ አወቃቀር ላይ የተመሠረተው የሕገ-መንግሥት አተረጓጎም (structural interpretation of constitutions).

(ስለዚህም መፃፍ ያስፈልግ ይሆን?)በአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ መንግሥት የሚጠቀመው ሥልጣን፣ ሕጋዊ መሠረት ያለው መንግሥት ሥልጣን ነው እንጂ ያልተመረጠ መንግሥት ሥልጣን አይደለም።

(ስለዚህም መፃፍ ያስፈልግ ይሆን?) ”

Temesgen Desalegn: ግንቦት 7.. ጸሐፊ: ተመስገን ደሳለኝ | አቅራቢ: ሔኖክ ዓለማየሁ | Ginbot 7 | Kinjit | TPLF | Zehabesha