Bilisummaa!! ሻጥር በየፈርጁ! ኦነግ ህዝብ ነው አይፈርስም!

(Repost) ሻጥር በየፈርጁ¡
ኦነግ ህዝብ ነው አይፈርስም!
 
ኦነግ ሃገር ነው። ኦነግ ከመንግስትም በላይ የሆነ ህዝብ ነው። ኦነግ ግዙፍና ከምትገምቱት በላይ ስለሆነ ተዉት። እኔ የኦነግ አባል አይደለሁም። ኦነግ ግን ሁሌም የኔ ነው። ABO ልክ እንደ እኔው ያልተመዘገቡ 50 ሚሊዮን ዓባላት እንዳሉት ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ። OLF/ABO ህዝብ ነውና አይፈርስም። አትሞክሩ።
ወያኔም ገና ሳታረጅ ያኔ በጉልምስና ዘመኗ “ሰላማዊ ኦነግ” በማለት ዝባዝንኬውን ሁሉ ሞክራ አልተሳካላትም። ከዲሞክራሲ ያፈነገጠውን አስተሳሰቧንና አገዛዟን በስተመጨረሻ ያንኮታኮተው ኦነግ ያሰረፀው አስተሳሰብ ነው። ሚሊዮኖች ታስረው፣ ተገለውና ተሰደው፣ አመራሩን እያደኑና እየገደሉም ኦነግ ነበር። እየሞትንና እየተሰደድን ኦነግ ይበረታ ነበር። የኛም የፍትሕ፣ የሰላምና የዲሞክራሲ ተስፋ አብሮ ይለመልም ነበር።
 
ሁላችንም ኦነጎች ነበርን፣ አሁንም ነን፣ ወደፊትም ላንከዳው ቃል የገባንለት መተኪያ የማይገኝለት ነው። እኛን ለማሰር ገዢዎቻችን እስር ቤቶች ሲጠቧቸው ሃገሪቷን የመላው ኦሮሞና የጭቁን ህዝቦች የዘመናት እስርቤት አድርገው ፈጠሯት። በዚያች ኢትዮጵያ በተባለች ግዙፍ እስርቤት ዉስጥ ሆነን ከመላው የሃገሪቷ ብሔረሰቦች ጋር በመሆን ነጉሱን፣ ደርጉንና ከሁዋላቸው የመጡትን ሁሉ በየተራ ሸኘናቸው።
እኛ ባርነትን ስንፀየፍ ከቀደሙት ነገስታት የሙት መንፈስ ጋር የተቆራኙት ገዢዎቻችን ኦነግን አፍርሶ ለመገንባት የጀመሩትን ፕሮጀክት እንዲያቆሙ ልናሳስባቸው እንወዳለን።


Nuf bishaan gabaterraa tokkuma 😀