ፕሮፌስር እዝቅኤል ገቢሳ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ያደረገው ንግግር Tigrai MediaHouse

ፕሮፌስር እዝቅኤል ገቢሳ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ያደረገው ንግግር Tigrai MediaHouse (TMH) #TMH

በኦሮሚያ እየተካሄደ ያለው የእስር ዘመቻ ይቁም!
—-
ኦዴፓ የሚባለው ድርጅት የሚሰራውንና የሚተወውን አያውቅም። ሰሞኑን በተፈጠረው ሁኔታ ሳቢያ በርካታ ኦሮሞዎች ልዩነታቸውን በመተው ድጋፋቸውን እየሰጡት ነው። እርሱ ግን በግርግሩ ተጠቅሞ ተቃዋሚ የሚላቸውን ሰዎች በብዛት ማሰሩን ተያይዞታል። ዛሬም ኦሮሞች የሚታሰሩበት ሰበብ “የኦነግ አባል ነህ! የኦነግ ደጋፊ ነህ” የሚል መሆኑ ደግሞ ይበልጥ ያስገርማል።

የዞን እና የቢሮ ሃላፊዎች “በወንጀል የተሳተፉ ሰዎች ናቸው የታሰሩት” ይሉልኛል። ቅጥፈት ነው። ሰላማዊ ገበሬዎች ናቸው እየታሰሩ ያሉት። አንዳንዶቹ አራት ወራት ሆኖአቸዋል። በዚህ ዓይነት ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ይቅርና የሰፈር ምርጫ ለማድረግ አይቻልም።
—-
እስሩን በማስመልከት ቪኦኤ ላይ ቀርቦ የተናገረው ኮሎኔል አበበ ገረሱ ከአቦ ዳውድ ኢብሳ ጋር ተጣልቶ ከኦነግ የወጣ ሰው ነው። ታዲያ ከጋዜጠኛው ጋር ሲነጋገር ሃላፊ ሳይሆን ቂሙን ለመወጣት የተቀጠረ mercenary ነው የሚመስለው (ሽሬ ላይ በወያኔ የተማረከ የደርግ አስር አለቃ መሆኑ የተረሳ መስሎታል)።

የዶክተር አቢይ መንግስት ቂም ያረገዙ ሰዎችን መሾም የሚያመጣውን ጉዳት ከጄኔራል አሳምነው ፅጌ ሊማር ይገባዋል። የተቃውሞ ፖለቲካ አራምዳለሁ የሚል ሰው በምርጫ ተወዳድሮ ወንበር መያዝ አለበት።
—-
አዎን! ኦሮሞን “የኦነግ ደጋፊ ነህ” እያሉ ማሰር ይቁም! አራት ነጥብ።

Aladdin Alawi Siddiqi