ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አዲስ አበባ በአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ ከተናገሩት

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አዲስ አበባ በአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ ከተናገሩት

ኤርትራን ነፃና ብቸኛ ሀገር ለማድረግ ባደረግነዉ ትግል ደርግን ሀይሉን ለማዳከም የአላማ ጥምረትና ትስስር ካላቸዉ የፖለቲካ ሀይሎች ጋር እንሰራ ነበር። ከነዛ ዉስጥ አንዱ TPLF ነዉ።
በኃላም ትግላችን ተሳክቶ ሀገረ ኤርትራ ስትመሰረት ከኢትዮዽያ ጋር በመልካም ጉርብትና በሰላም ለመጎራበት ብሎም ምስራቅ አፍሪካ ላይ የራሳችንን ሚና እንጫወታለን ብለን ተልመን የሁላችንም ሰላም ይጠበቃል ከሚል ተነሳሳን ።ግን ህወሀት ይህ እዉነት መቀበል አልፈለገችም እኛንም ከምንወደዉ ህዝብ ለየችን 20 ዐመት ረጅም ነዉ።
በመጨረሻም ወያኔ አልተሳካላትም በሌብነት ላይ ተሰማርታ ዝርፌያዉን ቀጠለችበት ይህ እዉነት ነዉ። ዛሬ ከኢትዮዽያ ጋር እርቅ አድርገናል። ህዝቡም ፍቅርና አንድ ህዝብ ነዉ።
ይህን ፍቅር የተመለከተች ህወሀት ዛሬም እኔን ትወነጅላለች እኔ የኤርትራ ፕሬዘዳንት እንጂ ዶ/ር ዐብይ በሚሰራዉ ነገር ምን አገባኝ።
ዐብይ ግን የሰላም የፍቅር ሰዉ ነዉ ። እንደ ወዳጅ ልናግዘዉ ይገባል ኢትዮዽያ ትልቅ ታሪካዊ ጉዞ ላይ ትገኛለች።

Dhábasá Wakjira Gemelal