ፓርላማው ነገ በምህረት አሰጣጥና አፈፃፀም ስነ-ስርዓት ረቂቅ አዋጅ ላይ ይወያያል

ፓርላማው ነገ በምህረት አሰጣጥና አፈፃፀም ስነ-ስርዓት ረቂቅ አዋጅ ላይ ይወያያል


(fanabc)—-አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ በሚያካሂደው መደበኛ ስብሰባው በምህረት አሰጣጥና አፈፃፀም ስነ-ስርዓት ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ለተጨማሪ እይታ ይመራል።

የምክር ቤቱ ፅህፈት ቤት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፀው፥ ምክር ቤቱ ህገመንግስቱንና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ከአደጋ ለመከላከል የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለመቀበልና ለማፅደቅ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1083/2010 ለመሻር የቀረበን ረቂቅ አዋጅንም ያፀድቃል።

በተጨማሪም በኢትዮጵያ እና በሳዑዲ አረቢያ መንግስታት መካከል የተፈረመውን የቤት ሰራተኞች ቅጥር ስምምነትን ለማፅደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ለተጨማሪ እይታ ወደ ሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ይመራል ተብሎም ነው የሚጠበቀው።