ፍንፊኔ: የፍቼና ጫምባላላ ክብረ በኣል ፍንፊኔ ኦሮሞ ባህል ማእከል በደማቅ ሁኔታ

#ዜና_ፍንፊኔ #የፍቼና ጫምባላላ ክብረ በኣል ፍንፊኔ #ኦሮሞ ባህል ማእከል በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ነው። በክብረ በኣል በከተማው የሚኖሩ የብሄሩ ተወላጆችና የኦሮሞ አጋር በተሰቦች ተገኝተዋል።

በኣሉ በውይይቶች እና በተለያዩ አዝናኙ ኩነቶች ታጅቦ ቀኑን ሙሉ ይከበራል።

የአዲስ አበባ/ፍንፊኔ ከተማ ከንቲባ አቶ ታክለ ኡማ ዛሬ ጨምባላላ በኣልን አስመልክቶ ከተናገሩት!
አይዴ -ጨምበላላ/ፊቼ -ጨምበላላ
ይህ የሲዳማ አዲስ ዓመት ነው፡፡አዲስ ጅማሬ ፤
የመታደስ ጊዜ ፤ አንድ ሆኖ የመቆም ጊዜ ፤
የተስፋ ጊዜ ፤ የተከበረ ባሕል፤ የፍሰሃ ጊዜ (የዘፈኖች እና ጭፈራዎች) ፤ የጥሩ ቡሪሳሜ ፣ ወተት እና ቅቤ ጊዜ ነው፡፡

በዩኔስኮ ላይ እንደተገለፀው ፊቼ ፍትሃዊነትን ፣ መልካም አስተዳደርን ፣ ማህበራዊ ትስስርን እና በሲዳማ ህዝብ እና ሌሎች ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ ህዞቦች መካከል ሰላማዊ ትስስር እንዲኖር ያደርጋል፡፡

የፊቼ ጨምበላላ ዋና እሴቶቹ ጠንክሮ መሥራት ፣ አካታችነት ፣ውብ የሆነ የማስታረቅ ታሪክ ፣ ውበትና ማራኪነትን ማክበር ፣ ከምንም በላይ ከዚህ ቀደም ስለተፈጠሩ ስህተቶች ሳይሆን ብሩህ የሆነ የወደፊት ተስፋን መሰነቅ ነው፡፡

ፊቼ ለቀደምት ትውልድ ዘለቄታዊ ክብር ስለመስጠት ፣ ተፈጥሮን እና እውነታን(Hallaleን) ስለማክበር ነው፡፡

ይህን በዓል ከወንድሞቼ ከሲዳማ ልጆች ጋር ፊንፊኔ ላይ በማክበረ እኮራለው።

የፍቼና ጫምባላላ ክብረ በኣል ፍንፊኔ ኦሮሞ ባህል ማእከል በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ነው።

Sidama page