ፌደራሊስቶቹ ኢትዮጵያ ውስጥ አሉ የተባሉ የብሔር ብሔረሰብ ሙሁራን የተሰባሰቡበት ድንቅ ውይይት

ፌደራሊስቶቹ ኢትዮጵያ ውስጥ አሉ የተባሉ የብሔር ብሔረሰብ ሙሁራን የተሰባሰቡበት ድንቅ ውይይት

#አዲስ_መረጃ_ከአዳማ

ማሳንቱ

ላለፉት ሳምንታት በአዳማ ከተማ ሲደረግ በነበረው የብልጽግና ፓርቲ ስብሰባ ላይ የሲዳማ አመራሮችም ሲሳተፉ መክረማቸው ይታወሳል። ስብሰባው ዛሬ ይጠናቀቃል ተብሎ ሲጠበቅ የነበር ቢሆንም አዲስ አበባ በመሄድ አንድነት ፓርክን እና እንጦጦ ተራራን እየጎበኙ ይገኛሉ። መደበኛው ስብሰባ የተጠናቀቀ ቢሆንም የደቡብ ክልል አመራሮች ብቻቸውን ለተጨማሪ 3 ቀናት ከጠ/ሩ ጋር እዛው ስብሰባ ላይ እንደሚቆዩ የተረጋገጠ ሲሆን የሲዳማ አመራሮችም እዛው እንዲቆዩ ትዕዛዝ እንደተሰጣቸው አረጋግጠናል። ይህ ስብሰባ ሆን ተብሎ የስልጣን ርክክቡን ለማዘግየት የሚደረግ እና ከዝያም ባለፈ ለሲዳማ አመራሮች ህዝቡን እንድያሳምኑ አጀንዳ ተሰጥቷቸው ሊመጡ የሚችሉበት ስለሚሆን የሲዳማ ህዝብ የእራሱን አቋም ይዞ ይጠባበቅ።

እስከ የካቲት 15 ድረስ ብቻ የስልጣን ርክክብ ተካሂዶ የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምስረታ የማይከናወን ከሆነ የሲዳማ ኤጄቶ ጋዶ ባንቆ ለመጥራት እንደሚገደድ ያስቀመጠውን የጊዜ ገደብ በመጠባበቅ ህዝቡ ሁሉ የእራሱን ዝግጅት እያደረገ ይቆይ። የሲዳማ ህዝብ ክልል መሆኑን በድምጹ ካረጋገጠ 3 ወራት ቢቆጠሩም ገዢው ፓርቲ የሲዳማን ክልል ለመመስረት እያቅማማ መቆየቱን ተከትሎ ህዝቡ ነጻነቱን በእጁ ለማስጠበቅ ማንኛውንም አይነት መስዋትነት ለመክፈል መዘጋጀቱን ለማሳየት የካቲት 15 የትዕግስቱ የመጨረሻ ገደብ መሆኑን ሁሉም አካል አውቆ ሊጠነቀቅ ይገባል።

“የካቲት 15 ድረስ የስልጣን ርክክብ የማይካሄድ ከሆነ ጋዶ ባንቆ ለማካሄድ መወሰኑን ኤጄቶ መግለጹ ይታወሳል!!”

#በማሳንቱ
#share