ፊንፊኔ/ሸገር/አዲስ አበባ ከ 1973 -2017

ፊንፊኔ/ሸገር/አዲስ አበባ ከ 1973 -2017

አዲስ አበባ ከአንድ መቶ አመት በፊት ጀምሮ የወቅቶቹን አስተዳደራዊ ሁኔታ ተንተርሶ በተለያዩ መንገዶች በኦሮሞ መሬት ላይ ስትስፋፋ ነበር።
ከ1991 ወዲህ ግን አስተዳደራዊ መዋቅሩ ስለተቀየረ /ህግ መንግስቱን በሚፃረር ንዑስ ህግ ቢሆንም/ ከተማይቷ በራሷ የአስተዳደር መዋቅር ስለተደራጀች አንዲት ስንዝር የምታደርገው መስፋፋት ህገ መንግስቱን የጣሰ ወንጀል ነው የሚሆነው። በዚህም አግባብ ከ1991 ወዲህ ያደረገችው መስፋፋት በህጋዊው የኦሮሚያ ክልል ላይ ስለሆነ በጉልበትና ህገወጥ መንገድ የያዘቻቸውን ይዞታዎች የመቆጣጠርና የማስተዳደር ህጋዊ ውክልና የላትም።
 
ባጠቃላይ ሲታይ የከተማይቷ የቆዳ ስፋቷ አሁን ባለችበት ሁኔታ 54 ሺህ ሄክታርን የምትሸፍን ሲሆን በ1991 20 ሺህ ያክል ብቻ ነበረች። የከተማይቷ ህገወጥ መስፋፋትና የመሬት ወረራ እስከ 2000 ድረስ በጣሙን የተስፋፋ ሲሆን ከ 2000 እስከ 2017 እና አሁን እስካለንበት ጊዜ ድረስም ያለ ከልካይ ከልክ በላይ የኦሮሚያን አርሶ አደር በማፈናቀልና ከአካባቢው በማፅዳት የለየለት የዘር ማጥፋት ወንጀል በመፈፀም ላይ ትገኛለች። የከተማይቷ የመሬት ወረራ ዓመታዊ ስፋቷ ባለፉት 20 ምናምን ዓመታት በአማካይ 1,700 ሄክታር ይሆናል።
የከተማይቷ የ1991 የቆዳ ስፋት ከ2017 ጋር በንፅፅር ሲታይ በፊት ባላት ቁመናዋ መሸፈን ከሚገባት ዛሬ ላይ ካሉ ከ 10 ክፍለ ከተሞች 5 ቱን ያህል ብቻ የሚያካትት ነው።
 
ከ 1991-2017 ብቻ አ/አ ተማ ወደ ጎን የተለጠጠችበት በፐርሰንት ስታይ ከ 2500% ሲሆን ይህ ሁሉ የተደረገው ኦሮሞን በማፈናቀል ሲሆን ዛሬም ከአባይ ማዶ የመጡት ፖለቲከኞች አ/አ ከኦሮሞ ውጪ አድርጎ ደሴት ከተማ ለመፍጠር ይሞክራሉ።
ፊንፊኔ/ሸገር/አዲስ አበባ የኦሮሚያ ዋና ከተማ: የፌዴራል መንግስት ዋና መቀመጫ/የኢትዮጵያ መዲና ፣የአፍረካ ህብረት ዋና መቀመጫ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫ ናት።

1 Comment

  1. የአምሀራ ክልል ሁለት ዞኖችን ማለትም የራያ ዞን እና የምእራብ ትግራይ ዞንን በጦርነት ከትግራይ ክልል በቀማበት በዚህ ስርኣት አልበኝነት በሰፈነበት ጊዜ የኦሮሞ ክልል የክልሉን ህገመንግስት ለማስከበር አለመቻሉ እና እምብርቱን ቅድስት ፍንፍኔን ወይም የቅዱስ ሸገርን መንበር ለማስተዳደር የማይችል አድር ባይ ቅጥረኛ መሆኑ የኦሮሞ ህዝብን የትጥቅ ትግል አቀጣጥሎታል::

Comments are closed.