ጽንፈኛው ኢዜማ በሚስጥራዊ ዶክሜንቱ ሙስሊሙን በአክራሪነት (በሀገር ደህንነት ስጋት) መፈረጁን አበሰረ!

ጽንፈኛው ኢዜማ በሚስጥራዊ ዶክሜንቱ ሙስሊሙን በአክራሪነት (በሀገር ደህንነት ስጋት) መፈረጁን አበሰረ!

“እኔ መንግስት ከሆንኩ ኢስላማዊ ባንክ እንዲኖር አልፈቅድም” ያለው ኢዜማ ወቅታዊ ሀገራዊ ደህንነትን በተነተነበት ሰነድ ውስጥ የሀይማኖት ፅንፈኝነት አንዱ የሀገሪቷ ደህንነት ስጋት መሆኑን ጠቅሶ የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን ፖለቲካዊ ተሳትፎ፣ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እና ማህበራዊ መስተጋብር በአጠቃለይ በአክራሪነት ፈርጆታል።
.
ዶክተር ብርሀኑ የግንቦት 7 መሬ ሆነው ኤርትራ “በትግል” ላይ ሳሉ ኤርትራን ለትግል ለምን እንደመረጡ ተጠይቀው ሲመልሱ “የቤተክርስትያን ደውል የሚቀሰቅሳቸው መሆኑን” እንደምክንያት ያቀረቡት የአሁኑ የኢዜማ ፓርቲ መሪ ድርጅታቸው በሰነዱ ላይ “ሙስሊሞች ጽንፈኛ እንቅስቃሴያቸዉን የሚያደርጉት መስጂዶችን ተገን አድርገው ነው” በማለት መስጂዶችን የጽንፈኞች መፈልፈያ እንደሆኑ አድርገው አቅርበዋል፡፡
.
ሙስሊም ባለሃብቶችንንም የኮነነው ይህ ሰነድ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የማይታመኑ መሆናቸዉን በሚገልጽ መልኩ ከግብጽ ጀምሮ ከተለያዩ የአረብ ሃገራት ጋር ግንኙነት እንዳላቸዉ እና የገቢ ምንጫቸዉም እነሱ እንደሆኑ ያትታል፡፡
ነገር ግን ሰነዱ ለዚህ ውንጀላው ያቀረበው ምንም አይነት መረጃ እና ማስረጃ የለም፡፡
.
በሌላ በኩል ዶ/ር ብርሃኑ በግል የቀድሞው ፓርቲያቸው በጥቅል ከግብጽ ጋር ከፍተኛ ፍቅር የነበራቸዉ መሆኑንን እና ለድርጅታቸዉም ይሁን ለኢሳት ሚድያቸው ግብጽ የገንዘብ ምንጫቸው እንደነበረች ድፍን ኢትዮጵያዊ የሚያውቀው እነሱም ከተጋለጡ በሁዋላ ያልካዱት ሃቅ ነው፡፡ አሁንም ያንን ወዳጅነት ተጠቅመው ከግብጽ ጋር ምን እየሰሩ እንደሆነ የደህንነት መስርያ ቤቱ ህይወት ካለው ዶ/ር ብርሃኑን እና ፓርቲያቸዉን ሊከታተላቸው ይገባል እላለሁ፡፡
.
በአጠቃላይ የአክራሪ ክርስትያኖች ፓርቲ የሆነው ኢዜማ ከዚህ ቀደም ዲያቆን ዳኔል ክብረት በሰነድ አዘጋጅቶ ለህወሃት መራሹ ኢህአዴግ ባቀረበው ሰነድ መሰረት ሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ ያ ሁሉ እልቂት እና መከራ ዘንቦበት ሲያበቃ ሙስሊሙ ከሌሎች ጋር በመሆን ባመጣው ለዉጥ ከወሬ ዉጪ ምንም ተጽዕኖ መፍጠር ያልቻለው የዶክተር ብርሃኑ ፓርቲ ኢትዮጵያ እንዲገባ እና የእልፍኝ ባለሙዋል እንዲሆን ያደረገዉን ማህበረሰብ ህወሃት መራሹ ኢህአዴግ ሙስሊሙን በወነጀለበት እና ባሰቃየበት መንገድ ለመሄድ የተዘጋጀ በመሆኑ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ለዚህ ድርጅት ካርዱን መስጠት ማለት በራሱ ላይ ሸምቀቆ እንደማጥበቅ ሊወስደው ይገባል፡፡
.
ፊንፊኔ ኢንተርሴፕት ያጋለጠው የኢዜማ ሰነድ የሙስሊም ኢትዮጵያዊያንን የፖለቲካ ንቃት መጨመር የሀገር ደህንነት ስጋት ተደርጎ ሊታይ እንደሚገባ ከማተቱም በላይ በሚገርም ሁኔታ የምርጫ ቦርድ ደንብን በሚጥስ መልኩ መረጃ እና ማስረጃ ሳያቀርብ በዛ ያሉ ሙስሊሞች ስላሉበት ብቻ የነጻነት እና እኩልነት ፓርቲን “እምነት ተኮር በመሆኑ ” የሀይማኖት (የእስላም) ፓርቲ ብሎታል፡፡
.
ነእፓ እምነት ተኮር በመሆኑም የሃይማኖት ጽንፈኝነትን ፖለቲካዊ ቅርጽ እንዲይዝ የማድረግ አቅም ያለው በመሆኑ የብሄራዊ ስጋት ደህንነት ዉስጥ ሊካተት ይገባል” ሲል ፈርጆ ታል፡፡
.
እምነት ተኮር በመሆኑ የሀይማኖት ጽንፈኝነትን ፖለቲካዊ ቅርጽ እንዲይዝ የማድረግ አቅም ያለው በመሆኑ የብሄራዊ ስጋት ደህንነት ዉስጥ ሊካተት ይገባል” ሲል ፈርጆ ታል፡፡
.
በመሰረቱ ዶክተር ብርሃኑ እና ፓርቲያቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ ሙስሊሙ ላይ ያላቸዉን ጥልቅ ጥላቻ መደበቅ እያቃታቸው የመጣ ከመሆኑም በላይ ኢዜማ እንደ ፓርቲ ከምስረታው እስከአሁን ድረስ በክርስትያኖች የተሞላ በመሆኑ (አንዳንድ ሙስሊሞች ጣል ማለታቸው ነጻ አያደርገዉም፣ ነጻነት እና እኩልነት ላይ የሌላ እመነት ተከታዮች መኖራቸው በኢዜማ አይን ነጻ እንዳላደረጋቸው ሁሉ ) ፓርቲው ወይንም ኢዜማ ከያዘው ኢስላም ጠል አቅዋሙ አንጻር በአክራሪ ክርስትያን ፓርቲነት ሊፈረጅ ይገባል! ስለዚህ ሙስሊሞች ፓርቲዉን በስሙ ሊጠሩት ይገባል እላለሁ፡፡
.
ሙሉ ሰነዱን ለማየት : https://bit.ly/2QWEMYa