ጫጫታው ለአንድነት ነው ወይስ የበላይነት?

ጫጫታው ለአንድነት ነው ወይስ የበላይነት?

የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ሊቋቋም ነው ሲባል አንድ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ የአንድ አከባቢ ሰዎች የሚንጫጬት በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያላቸውን የአማራ የበላይነት ለማስጠበቅ እንጂ፣ ለእምነታቸው ወይም ለቤተክርስቲያኒቷ አንድነት ተቆርቁረው እንዳልሆነ ሳይታለም የተፈታ ነው። የምር ስለ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አንድነት ቢገዳቸው ኖሮ፣ 1) የቤተ ክርስቲያኒቷ መሪዎች የእግዚአብሔርን ቃል እንኳን ጥሰው ሰውን በዘር እየለዩ ፣ ለወገኔ ይጠቅማል በማለት፣ በአድልዎ መንፈስ፣ አማራ ዲያቆናት ፣ ቀሳውስት እና ጳጳሳትን በብዛት ሲቀቡ እና ሲሾሙ ነበር ኧረ ተው ለአንድነታችን አይበጀንም ማለት የነበረባቸው። ይህም ሳያንስ ብዙዎች ጳጳሳት፣ ቀሳውስትና ዲያቆናት 30 እና 40 ዓመት በኦሮሞና በሌላው አማርኛ ተናጋሪ ያልሆነ ህዝብ መሃል ሲኖሩ ፣ ከንቀት እና ከመፀየፍ የተነሳ፣ ለንሰሐ፣ ለኑዛዜ ወይም ለፍትሐት እንኳን የሚሆን የሌላውን ቋንቋ ለመልመድ አለመሞከራቸው ነው።

2) የቤተክርስቲያኒቷ ዲያቆናት ሰውን በዘር ለይተው በስላቅ፣ በአሽሙር እና በግልፅ ሲሳድቡ ነበር ተው ማለት። ለምሳሌ ያህል በአንድ ወቅት በተውሰኑ ፅህሑፎቹ አደንቀው የነበረው፣ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በአፋን ኦሮሞ የዘመሩትን ቄስ፣ ወንጌልን በአፋን ኦሮሞ ለማዳረስ በመጣራቸው እና በመዘመራቸው ፡ ከፋፋይ እያለ ቤተክርስቲያን መድረክ ላይ ቆሞ ሲያጥላላቸው ነበር ። ያኔ ነበር ስለ ቤተክርስቲያን አንድነት ማሰብ። በተጨማሪም ዲያቆን ዳንኤል “ግጥምን በጃዝ” በሚባለው ፓለቲካን በመሃሉ ግጥም (‘ጥ’ ጠብቃ ትነበብ) አድርገው እንደ “ሳንድዊች” ሌላውን በማጥላላት ወገኔ የሚሉትን የአድልዎ ድድስኩር ሲመግቡት ነበር ኧረ ተው ዲያቆን ዳንኤል ለአንድነታችን አይበጅም ማለት። ለምሳሌ ዲያቆን ዳንኤል “ኢየሱስ አሁን ተመልሶ ቢመጣ ፣ ‘ከደብረ ዘይት ወደ ናዝሬት ሄደ የሚለውን ፣ ከቡሾፍቱ ወደ አዳማ ሄደ ይባልልን ይሉታል” ብሎ ሲል በትክክል ኦሮሞ ላይ እንዳነጣጠረ ፣ ንፁህ ሂሊና ያለው ሰው ይገነዘባል። እዚህ ጋር ዲያቆን ዳንኤል ሶሥት ነውረኛ ቅጥፈቶችን ሲሠራ ይታያል። የመጀመርያው: የኦሮሞ ህዝብ የሚቃወመውን indigenous ለሆነ መሬቱ ሌላ የባዕድ ስም መሰጠቱን ዳንኤል በመፅሐፍ ቅዱሳዊ ዘይቤ አስታክኮ ለማጣጣል መሞከሩ ነው። ሁለተኛው: ትክክለኛዎቹ ደብረዘይት እና ናዝሬት እሥራኤል አገር እንዳሉ እያወቀ እንደ ክርስትና ስም ዘመዶቹ በህገ ወጥ ቡሾፍቱ እና አዳማ ላይ ሊያጣብቁ የሞከሯቸውን fake ስሞች የኢየሱስን ስም በመጠቀም ለማፅደቅ መሞከሩ ነው። ሶሥተኛው ቅጥፈቱ፣ ኢየሱስ እንኳን ቢመጣ (በ ዮመል ቂያማ ጊዜ) የኦሮሞ ህዝብ ስለ ሰማያዊ ነገር ሳይሆን ስለ ምድራዊው ( ዱኒያ ነው የሚያስበው/የሚጠይቀው) ለማለት መሞከሩ ነው።

ዳንኤል በተጨማሪ የዚህኑ ቀን “ይሁዳ ኢየሱስን በሰላሣ ብር ሽጦ መሬት እንደገዛ ፣ ያ ልጅ ደግሞ ኢትዮጵያን ሽጦ ፣ ቦሌ አከባቢ ቤት ገዝቷል። ይሁዳ እንኳን ተፀፅቷል። ያ ልጅ እንኳን የሚፀፀት አይመስልም” አለ። ዳንኤል “ያ ልጅ” ሲል ማንን እንደሆነ የማይጠረጥር ያለ አይመስለኝም። ዳንኤል እነዚህን ስድቦች ፣ ሽሙጦች እና አሽሙሮች ከጨረሰ በኋላ ወዲያውኑ: ጨዋ መስሎ : ምናለበት ሁላችን ቅን ብናስብ : እርስ በእርስ ብንተሳሰብ እያለ በማር የተለወሰ መርዙን ስለ ሰላም ሲል ያንጠባጥባል። ጠቅላይ ሚንስተር አቢይ ይህን ሰው ካላራቀ sabotage የመደረግ ችግር ሊገጥመው ይችላል።

ዲያቆን ዳንኤል ብቻ ሳይሆን እሱን የመሳሰሉ ብዙዎች በቤተክርስቲያኒቷ መድረክ ላይ አሊያም እሷ ባዘጋጀቻቸው መድረኮች ላይ ቆመው ተመሳሳይ ድስኩር ሲደሰኩሩ ስንቴ ታዝበን ጊዜ ለኩሉ ብለን ትተን ነበር። ለምሳሌ ዲያቆን ሕዝቅያስ የተባለ የቤተክርስቲያኒቷ አገልጋይ፡ የቤተክርስቲያኒቱ መድረክ ላይ ቆሞ ስብከት ከተባለ፣ በስብከቱ መሃል “ኦሮሞዎች አዲስ አበባ የኛ ነው የምትሉትን እና ሁሉ የኛ ነው የምትሉትን ማቆም አለባችሁ። አለበለዚያ አንላቀቅም” ብሏል። ኦሮሞ የሆነ ሰው: አእምሮው የሞተበት ካልሆነ በስተቀር : ምን በወጣው ነው : እንደዚህ አይነቱን በሃይማኖት ካባ የአድልዎ ፓለቲካ አራማጆችን የሚሰማው? እነዚህ ፓለቲካዊ ዲያቆናት፣ የራሳቸውንም ወገን ፓለቲካ የሌላውን እንደሚተቹት ቢተቹ ኖሮ balanced ናቸው በማላት መቀበል ይቻል ነበር። ሰው ቃለ እግዚአብሔርን ነው የአድልዎ ፓለቲካ ሊሰማ ነው እነዚህ ጋ ቤተ ክርስቲያን የሚሔደው? የዲያቆን ሕዝቅያስ፣ የዲያቆን ሃብታሙ አያሌው እና የዲያቆን ዘመድኩን በቀለ የዘር እና የሃይማኖት ጥላቻ ደግሞ ላይ ከጠቅስኩትም ስለሚብስ ለመዘርዘር ጊዜ አይበቃኝም። ዎቄፈታውን፣ ሙስሊሙን እና ፕሮቴስታንቱን እንዲሁም ኦሮሞን እንዴት እንደሚያንቋሽሹ ለማየት ንግግራቸውን እዩ። እንዴት እንደሚሳደቡ ለማየት ከዲያቆን ዘመድኩን በቀለ ጀምሩና ፔጃቸውን እዩ። ለእነዚህ ያለምንም ጥያቄ ሲያጨበጭብ የሚውል ህዝብ: ቄስ በላይ በቋንቋዬ ላምልክ፣ እራሴን በራሴ ላስተዳድር ስላላ፤ ዛሬ ተነስቶ ከፋፋይ ፣ ከሃዲ የእንትና ፈረስ እያሉ መሳደብ: የቄስ በላይን ትክክለኛነት ያሳያል። የሰይጣ ፈረስ የሆነው ተሳዳቢው ዱያቆን ዘመድኩን ቄስ በላይን አንዴ የጀዋር ፈረስ፣ አንዴ የወሃቢይ እስላም ፈረስ፣ አንዴ የእሬቻ ጠንቋይ አምላኪ ሲለው፣ ዘንዶው የስድብ አፍ ተሰጠው” የሚለውን የራዕይ ቃል አስታወሰኝ። በተለይ በተለይ የቤተክርስቲያኒቷ ሰባኪያን እና ዲያቆናት የአብንን ፓርቲ አቋም የመሰለ ስብከት ሲሰብኩን ፣ ኦርቶዶክስ : ከቤተክርስቲያን ወደ ቤተ አምሐራ መቀየሯ ይሆን እንዴ የሚል አላርም ስላቃጨለብን፣ ለቋንቋ ብቻ ሳይሆን ለመንፈሳዊና ለስነ ልቦናዊ ጤንነት እንዲሁም ለኦሮሞ ህልውና ስንል የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክህነትን መደገፍ ሰብዓዊነት እና መንፈሳዊነት ነው።

ሌላው የሚገርመው “ግጥምን በጃዝ” ላይ: ሰርፀ ሚኒልክ አዲስ አበባን ሲቆረቁሩ፣ በቦታው፣ ድኩላና የሜዳ ወይም እንስሳት ብቻ ነበሩ ማለቱ እና ሌሎችም ድስኩሮች የፕሮግራሙን ዓላማ ለጥበብ ብቻ ሳይሆን ለፓለቲካዊ ወገንተኝነት እንደሆነ ግልፅ ነው። ዲያቆን ዳንኤልን እና ሰርፀን: ብዙ ከሚያውቁት፣ ከሚያመዟዝኑት እና ከማያዳሉት ወገኖች ቆጥረን ያደነቅናቸው፣ ነገር ግን መሠሪነታቸውን በየዕለቱ ስናይ ቱ ብለን የተፋናቸው ብዙዎች ነን። አንዳንዴ ቁም ነገር ሊናገሩ እና ሊፅፉ ይችላሉ። የካህናት እና የዲያቆናት ፓለቲካዊ ወገንተኝነት፣ መሰሪነታቸው እና የፓለቲካ ሽፍጥን በጥበብ አሽሞንሙነው፣ የሃይማኖት ካባ ደርበውለት በመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ሊያወራርዱልን መሞከራቸው ቢያንገሸግሸን ፣ ሸፍጡ ደግሞ ግለሰባዊ ብቻ ሳይሆን ብሔራዊ ማንነት ሃይማኖታዊ እና ድርጅታዊ መልክ ፣ ዓላማ፣ ግብና ጎል እንዳለው ሲገለጥልን: በምድርም በሰማይም ያለንን ቦታ: የሃይማኖት ካባ ካጠለቁ ተኩላዎች ለመጠበቅ : የኦሮሚያ ቤተክህነት መቋቋምን መደገፍ አማራጭ የለውም። ለቋንቋ ብቻ ሳይሆን እላይ የጠቀስኳቸውን ሃይማኖታዊ ካባ የደረቡ፣ በመስቀል የተባረኩ የሚለቀቁ ፓለቲካዊ ሽፍጦችን ለማምከን ሲባል፣ የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክህነት ማቋቋሙ በጣም አስፈላጊ ነው።

ቀሲስ በላይን ሳይሆን ፣ የበላይነትን ተቃወም።

Marii hundeeffama Waajjira Mana Lubummaa Ortodoks Tawaahidoo Naannoo Oromiyaa irratti xiyyeefatu eegalleera. Barsiisaa Haayila Mikaa’el Tafarraa fi Malaaka Hiywot Qomoos Abbaa Waldayyassus Sayifuu Galataa walin jirra. Hirmaadhaa! Walif qoodaa!


How much of Orthodox, as practiced by EOTC, is actually about gospel and Jesus, and how much of it is just simple tradition invented and borrowed from Egypt, Rome, Greek and Syria accumulated over the last 1600 years? Remember, the church only started to name its own Patriarch in 1959. It was under Alexandrian church for almost all of its existence. Anyway, according to some estimate, about 55% of what EOTC does is tradition, it has nothing to do with the gospel.

This % has probably decreased or the church has been forced to actually do gospel works since it lost its land, status as state religion and political power in 1974. That said, there is still an entrenched culture of tradition, protocol and procession obsession within the church.

Ironically, the church lost most of its adherents when it actually started to do gospel works away from its visible political role. After all, religion is a political power play; whoever got the longest and sharpest sword, not really the loudest voice, can impose his religious ideas on others. This is how all religions spread. The only exceptions are Oromos who refused to impose their religion on others even though they could have done it.

Nobody is saying all church tradition is bad. In the contrary actually. The church is the living fascinating history of thousand years of Abyssinian tradition and culture which is Christian i.e what is not Christian is simply Cushitic. So it makes sense if they protect it as they are now fiercely opposing the establishment of Oromiyaa Orthodox Church.

However, for people whose interest is in salivation and are only about ‘sola scruptura’, not tradition and culture, the church has no chance of standing any defense. It loses 10 out of 10 times.

For the southern people such as Oromos, they got two choices 1) to accept all the culture and tradition as foreign (even including Ge’ez) and hence pretty much neutral to anybody in Ethiopia or 2) to demand a very radical reform within the church and create their own church in their own image. I think they have chosen the second route which has provoked an imminent clash with the establishment

Biyya Oromiyaa

የሃበሾች ኣሳሳች ልቤ ወለድ በገሃድ ስጋለጥ. Why these people are lying?

Monoksoonni jaraa gadaamii seentee seexana faana walgahii taa’uutiin Xonnoqolaa kana gadi munaagdeetu jaarraa tokkoo oliif saba biyya sanaa burjaajessite. Mee waaqaa jedhiiti kan isheen munaagde kana dubbisimee


 

1 thought on “ጫጫታው ለአንድነት ነው ወይስ የበላይነት?

  1. Do Orthodox priests and leaders read and believe what is written in Acts chapter 2 in the Bible? When the Holy Spirit landed on those who were worshiping, the holy sprit came down and those who gathered from all over the world started to speak in their own language. This is what is written in Acts chapter 2. I feels as the orthodox leaders do not read or have knowledge of the Bible. Who gave the right to Orthodox Amahra speakers the right to use Geeze or Amharic?

Comments are closed.