ጋዜጠኛ ማሰር ይቁም!

ጋዜጠኛ ማሰር ይቁም!
በቃሉ አላምረውና አበበ ባዩ ጋዜጠኞች ናቸው። በሙያቸው ሕዝብን ያገለገሉ ታጋዮች ናቸው።
ባስቸኳይ ይፈቱ!
የጎጃም ልጆችን እየነጠሉ ማሰር ይቁም!
በቃሉ አላምረውና አበበ ባዩ የጎጃም ልጆች ናቸው። በሙያቸው ጋዜጠኛ! አብዛኛዎቹ ጎጃሜዎች እንዳደረግነው የትግራዩን ጦርነት ተቃውመዋል። የህወሓት ደጋፊ አይደሉም። ሰላማዊ የትግራይ ተወላጆች ላይ የደረሰውን ሰቆቃ ግን እንደሁላችንም ተቃውመዋል። ምን የሚያሳስር ወንጀል ሰርተው ነው ታድነው የሚታሰሩት? መፍትሄው ውይይት ነው የሚለውን ሀሳብ አሁን ላይ መንግስትም እያንፀባረቀው ነው። በይፋ ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩት እነ ጌታቸው ሺፈራው በነፃነት በሚንቀሳቀሱበት ሀገር እነዚሀን የጎጃም ልጆች ነጥሎ ማሰር ውስጡ ፀረ ጎጃሜነት ያለበት አካሄድ ነው። ባስቸኳይ ይፈቱ!