ጅማ ከተማ የደራሽ ውሃ መጥለቅለቅ አደጋ ደረሰባት

ጅማ ከተማ የደራሽ ውሃ መጥለቅለቅ አደጋ ደረሰባት

ነሐሴ 17፣2009

በጅማ መሃል አቋርጦ የሚያልፈው የአዌንቱ ወንዝ በደራሽ ጎርፍ በመሞላቱ በጀማ ከተማ ንግድ ቤቶች እና መኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት አደረሰ፡፡

(EBC) — አደጋው በሰው ህይወት ላይ ያደረሰው ጉዳት የለም፡፡

ሊሙ አካባቢ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ወንዙ ሞልቶ አደጋ ማስከተሉ ታውቋል፡፡

የከተማ አስተዳድሩ በአደጋው የተጠቁ የማህብረሰብ ክፍሎችን ለማቋቋም እየሰራ መሆኑን ገልጿል፡፡

ጎርፉ በመሃል ከተማዋ የደረሰ በመሆኑ በንግድ ቤቶች ላይ ያደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል ተሰግቷል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ ግብረ ኃይል አደራጅቶ ለተጎጅዎች ምላሽ ለመስጠት መዘጋጀቱ ታውቋል፡፡

አደጋው ዛሬ ነሐሴ 17፣2009 ከቀኑ 8 ሰዓት አካባቢ ነው የደረሰው፡፡

ሪፖርተር፡- ደረጀ ግዛው(ከጅማ)