Site icon Kichuu

ጄነራል ሰዓረ መኮንን በጠባቂያቸው በመኖሪያ ቤታቸው ሳሉ መገደላቸውን የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር እና የሕወሓት ሊቀ-መንበር ዶክተር ደብረ ጺዮን ገብረ ሚካኤል ተናገሩ።

ጄነራል ሰዓረ መኮንን በጠባቂያቸው በመኖሪያ ቤታቸው ሳሉ መገደላቸውን የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር እና የሕወሓት ሊቀ-መንበር ዶክተር ደብረ ጺዮን ገብረ ሚካኤል ተናገሩ።

የጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ግድያ በባሕር ዳር ከተሞከረው መፈንቅለ-መንግሥት ጋር ተያያዥ እንደሆነ ዶክተር ደብረ ፂዮን ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በመቐለ ከተማ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።
«ድርጊቱን የፈጸሙት በጉልበት ሥልጣን ለመያዝ የሚታገሉ ጸረ-ሕገ መንግሥታዊ ኃይሎች» ናቸው ያሉት ዶክተር ደብረጺዮን የትግራይ ክልላዊ መንግሥት በጥብቅ እንደሚያወግዘው ተናግረዋል።

የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ ጄኔራል ሰዓረ መኮንን እና በጡረታ ላይ የነበሩት ሜጀር ጄኔራል ገዛኢ አበራ “በተቀነባበረ ሴራ በጄኔራሉ ጠባቂ በተተኮሰባቸው ጥይት” ሕይወታቸው ማለፉን አረጋግጧል።
የኢትዮጵያ መንግሥት «ጉዳዩ የአንድ ክልል ሳይሆን ሀገሪቱን በጠቅላላ ለመበጥበጥ የተደረገ» ነው ሲል በጥብቅ ኮንኗል። በባሕር ዳር የተገደሉት ዶክተር አምባቸው መኮንን እና የአቶ እዘዝ ዋሴ የቀብር ሥነ-ሥርዓት የሚያስፈፅም ኮሚቴ መዋቀሩን የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት መግለጫ ይጠቁማል። የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት «በፌድራል መንግሥት ደረጃ የተሰዉትን ጄኔራሎች በወታደራዊ ሥርዓት ለመሸኘት ዝግጅት እየተደረገ ነው» ሲል አክሏል።


ጄኔራል ሰዓረ መኮንን እና የቅርብ ወዳጃቸው ሜጀር ጄኔራል ገዛኢ አበራ ከምሽቱ 3 ሰዓት አካባቢ ጥቃት እንደተፈጸመባቸው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አረጋገጠ። የሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ሊቀ-መንበር ዶክተር ደብረ ጺዮን ገብረሚካኤል በበኩላቸው ተጨማሪ ግድያ ሊኖር እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የመረጃ ዋና መምሪያ ኃላፊ ጄኔራል ሐሰን ኢብራሒም በባሕር ዳር የተሞከረው መፈንቅለ መንግሥት እና በአዲስ አበባ የተፈጸመው ጥቃት «መንግሥትን ለማዳከም» ያቀደ እንደነበር ተናግረዋል።
ጄኔራል ሐሰን በብሔራዊ የቴሌቭዥን ጣቢያ በሰጡት መግለጫ ኮማንድ ፖስት መቋቋሙን ተናግረዋል። «ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ትናንት በባሕር ዳር የተከሰተውን አደጋ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ሕልፈተ-ሕይወታቸው ጊዜ ድረስ ሥራውን እየመሩ እያለ፤ በሥራው ላይ እያሉ ነው ጉዳቱ የደረሰባቸው» ሲሉ አብራርተዋል።

የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር እና የሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ሊቀ-መንበር ዶክተር ደብረ ጺዮን ገብረ ሚካኤል በበኩላቸው ተጨማሪ ግድያ ሊፈጸም ይችላል የሚል ሥጋት እንዳላቸው ተናግረዋል።
ጄኔራል ሰዓረ እና ሜጀር ጄኔራል ገዛኢ አበራ «ከጸረ- ሕዝብ፤ ከሌላ ጥቃት ይከላከልልኛል፤ ይጠብቀኛል» ባሉት ጠባቂ መገደላቸውን የገለጹት ዶክተር ደብረ ጺዮን ጥቃቱን «የተናጠል፤ የአንድ ጥበቃ ወንጀል ብለን አንወስደውም። ከባሕር ዳሩ ድርጊት ጋር የተያያዘ ነው» ብለዋል። ጄኔራል ሰዓረ በአገሪቱ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ ባላቸው ኃላፊነት ምክንያት በዕቅድ የተያዘ ጥቃት ዒላማ መሆናቸውንም ተናግረዋል። «ይኸን ግድያ የሁለቱ ጄኔራሎች ብለን አንወስደውም። ሌሎች ግድያዎችም ሊኖሩ እንደሚችሉ መገመት እንችላለን» ሲሉ ሥጋታቸውን በመቐለ ከተማ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ አድርገዋል። «በባሕር ዳር ላይ ያነጣጠር አይደለም፤ በአገር ላይ ያነጣጠረ ነው። መንግሥትን የማፍረስ፤ መንግሥትን የማንበርከክ» ጥረት እንደሆነም ዶክተር ደብረ ጺዮን ገልጸዋል።

ጄኔራል ሐሰን በበኩላቸው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራው የኢትዮጵያ ሕዝብ “እርስ በርስ በብሔር እንዲናቆር ወይም ትርምስ ውስጥ እንዲገባ በማድረግ ይፈጠራል ብለው ያሰቡትን ዕድል ለመጠቀም እና ለማሳካት የተደረገ” ነው ሲሉ ተናግረዋል።
«ጥቃቱ በግለሰቦች ላይ የተሰነዘረ» አይደለም ያሉት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የመረጃ ዋና መምሪያ ኃላፊ ጄኔራል ሐሰን ኢብራሒም «የኢትዮጵያን ሕዝብ እርስ በርሱ ለማናከስ፤ የቆየ አንድነቱን ለማፍረስ በሰራዊቱም ውስጥ ጸንቶ የቆየውን አንድነት ለማፍረስ እና በዚህ አጋጣሚ በሀገር ላይ የመፍረስ አደጋን በማስከተል ያሰቡትን ዕኩይ አላማ የማሳካት ዕቅድ ይዘው ያደረጉት ተግባር ነው» ሲሉ ተናግረዋል

DW Amharic

LATEST
State broadcaster EBC says Amhara regional president Ambachew Mekonnin(PhD) and his advisor Azeze Wase have been killed in the last night attack in Bahirdar.

Sources say the army chief General Seare Mekonnin and another retired, Major General Gezae Abera, have been killed in the last night attack in Addis amid coup attempt in Bahirdar.


ሰበር ዜና

ጀነራል ሰዓረ መኮንን እና ዶ/ር አምባቸው መኮንን ተገድለዋል

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ላይየተፈጠረውን ቀውስ ተከትሎ ጀነራል ሰዓረ መኮንን፣ ዶ/ር አምባቸው መኮንን እና ደቡብ ጎንደር የጸጥታ ሃላፊ አቶ አዘዘው ዋሴ ተገድለዋል። የባህር ዳሩ እና የአዲስ አበባው ቶክስ በተመሳሳይ ሰዐት እንደተፈጸመ ነው የሚነገረው።

ጀነራል ሰዓረ መኮንን የተገደሉት በአዲስ አበባ ሲሆን፣ እንደተተኮሰባቸው ወደ ዋሽንግተን ሆስፒታል መላካቸውን ለማወቅ ተችሏል። የፌደራል መንግሥትቀውሱን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ቢለውምተንታኞች ከዚህ ግድያ ጀርባ ሌላ ሴራ እንዳለበት ይናገራሉ።

መፈንቅለ መንግስቱን የመሩት ጀነራል አሳምነው ጽጌ ናቸው እየተባለ ነው።

ይህ መረጃ እውነት ከሆነ ለአገሪቷ እየተደገሰ ያለ ድግስ ስላለ እያንዳንድህ አከባቢህን የመጠበቅ ኃላፊነት ልትወጣ ይገባል::

Sidama page

OMN: Naannoo Amaaraatti yaaliin fonqolcha Mootummaa? (Wax,23,2019)


“Make no mistake – the coup de’ta that was staged yesterday in the Amhara Regional State of Ethiopia is not a simple political altercations between Amhara elites but a well calculated plan born out of months preparation for a greater political power over the country. It was the first stage for Federal take over!

Make no mistake – the Amhara elites who staged this coup are neither Democratic nor progressive. They are nostalgic and backward lookers. They are in capsulatd with political retardation that had ravaged the country for over a century. They have little regards for the rights of others. They have nil plan to transform the country to a democratic state.

Make no mistake – the current ‘no common plan, no common vision & no common mission’ Ethiopian politics is a very compatible fuel for instability such as this coup. The hopeless oppositions in ‘hotels’ have very little awareness of the political environment they residing in let alone the capacity to produce an alternative plan that assist the transition of this country to democracy.

Make no mistake – the Qeerroo movement that purged the TPLF away from the Ethiopian political powerhouse was quashed mischievously by internal and external conspitors without producing the expected results. Replacing EPRDF with EPRDF is in the centre of today’s ongoing instability in the country. The pretense, the appeasement, the attack on those appeared to be weaker, the gift of government departments for undeserving people/groups are all failed tactic in buying peace .They are all the cover up institutional malfunction particular of those law enforcement ones. This has led to the empoverishment self confidence in the Federal government & boosted morales of vigilants.

Make no mistake – The current instability is not the making of the Oromos – it’s not an oromo war. Coup is in the psych of Abyssinian politics. Coup and Abyssinia have co-lived for centuries .The Oromo struggle is for freedom, democracy, equality and rule of law. So, do not try to co-opt the Oromo case for simple preservation of the interest of thise groups claiming to represent the Oromo people. We shall discern carefully between our war and someone’s war. The Oromo have fought wars that had little to do with its strategic interests. EPRDF’s war is not an Oromo in any forms and shapes. We should resist the strategy that is being designed to co-opt us into the war that has little to do with our long term interest.”
Via Kumsa Burayu


You are walking with the devil disguised as a religious person. First, secure your surroundings! Daniel Kebret is a Security threat of the highest order!

Najat Hamza

Ethiopia: ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና | Zehabesha Daily News June 23, 2019

Exit mobile version