ጃዋር መሐመድን በጥቁር አሜሪካዊ አስገድላለሁ ያለው ሰው ማንነት ሲጋለጥ (ምንሊክ ሳልሳዊ)

ጃዋር መሐመድን በጥቁር አሜሪካዊ አስገድላለሁ ያለው ሰው ማንነት ሲጋለጥ (ምንሊክ ሳልሳዊ) #Ethiopia #OMN #MinilikSalsawi

የዛሬ አጀንዳ ሆኖ የዋለውና በርካቶችን ያስቆጣው የፌስቡክ ጽሁፍ በጃዋር መሐመድ ግድያ ላይ የተለቀቀው ፖስት ነበር። ይህ በፎቶግራፍ ተደግፎ በቤተሰቡ የልደት ምስል ተከሽኖ የቀረበው በጃዋር Jawar Mohammed ላይ ሞት ያወጀበት ግለሰብ የተባለው ሰው በግልጽ ማንነቱ ታውቋል።

ግለሰቡ ጋዜጠኛ ነው ከጀርባው የትግራይን ህዝብ ከሌላው ለመነጠል የሚፈልግ አንድ ሃይል አለ ይህ ሓይል የሕወሃትን ንብረት በበላይነት ከሰላሳ አምስት አመት በላይ የሚያስተዳድረው ሃይል ነው። በገንዘብ የሚደግፉት የሕወሓት ቱባዎችና የአግአዚያን አቀንቃኝ የሆኑ የትግራይ ባለሃብቶችና ጽንፈኛ ምሁራን ናቸው ከነዚህም አንዱ የራያ ቢራ አክስዮን መስራች ባለሃብቱ ዳዊት ገብረ እግዚያብሄር ይገኝበታል። በርካታ ፕሮፋይሎችን በመጠቀም በአማራ ስም ሆኖ ኦሮሞን የሚሳደብበት በኦሮሞ ስም አማራን የሚሳደብበት ፡ እንደለምለም ሃድጉ (በተቀየረው አዲሱ ስም ሓብታሙ ሃይለየሱስ) ባሉት አካውንቶቹ ደግሞ የትግራይ መገንጠልንና የሌላውን ህዝብ የሚያንቋሽሽበት ብዙ አካውንቶች አሉት ። አሁን በጃዋር ላይ ግድያ ምናምን ብሎ ያወጣው የዓውራምባ ታይምሱ ዳዊት ከበደ ነው ። ለዚህ ደግሞ ከዳዊት ከበደ ጋር የሚሰሩና የሚጠቀምባቸውን የመገናኛ መሳሪያዎች በበላይነት የሚቆጣጠሩ የደህንነት ሃይሎች በሰጡት መረጃ ተረጋግጧል።

ይህ ፎቶግራፉ የተለጠፈው ሰው ፈጽሞ የፌስቡክ አካውንት የሌለው ሲሆን ጃዋርን ለማስገደል ቀርቶ አስቦትም አያውቅም ምክንያቱ ግን ምን መሰለህ ይህ ሰው የጃዋር ወዳጅ በሆኑ ቄሮዎች እርምጃ እንዲወሰድበትና የበቀል ጥሙን ፖለቲካዊ በሆነ መልኩ ለመወጣት ነው፥ከዚህም ባለፈ በዋናው አካውንቱ እንደሚታየው የትግራይ ህዝብን ከሌላው ጋር ለመነጠል ። በተለይ በድብቅ አጀንዳው የኦህዲድን እና በአዴን ላይ ንቀት አዘል መልእክቶች እያስተላለፈ የሚገኝ ማንን ሃይ ባይ የሌለው ሰው ነው።

አቶ ሓብታሙ ሃይለየሱስ የዳዊት ከበደ ወዳጅ ነው። ክህደት ልምዱ የሆነው ዳዊት ከበደ ከሃብታሙ ጋር ጋር አለመግባባት ይፈጥራሉ ፡ ይህን ሰው ብር እንዲሰጠው የተለያዩ ማስፈራሪያዎችን በመጠቀም ቢያስገድደውም ሰውየው እንቢ በማለቱ ሊበቀለው በተለያዩ ጊዜያት ስሙን ሲያጠፋ ቆይቶ ዛሬ ደግሞ ፡ ለምለም ሃድጉ የሚባለውን የፌስቡክ አካውንት ስም ቀይሮ በምትኩም የተጣላውን ሰው ሓብታሙ ሃይለየሱስ ስምና ፎቶ እንዲሁም ከሁለት አመት በፊት በዚህ ሰው ቤት ተገኝቶ ያነሳውን የልጅ ልደት ፎቶ ለጥፎ ትክክለኛ የሰውየው አካውንት እንዲመስል ካደረገ በኋላ ፡ የተለያዩ ነገሮችን በተለይ ይህን ሰው ያስወነጅላሉ ብሎ ያሰባቸውን ነገሮች ፖስት እያደረገ ነው ። ከዚያም አልፎ የዚህን ሰው ስምና ፎቶ አሁንም በሌላ አካውንት ላይ በመለጠፍ ጃዋርን ለማስገደል እየሰራ ያለው የኦሮሞ ጠላት ይህ ሰው ነው ። ብሎ ለጥፏል።ሰው ነው ብለህ የልጅህን ልደት የጋበዝከው ሰው ፡ ልጆጭን ሚስትን ፎቶ አንስቶ ከዛ በሆነ ነገር ስትጋጩ ያንተን የልጅህን የመላው ቤተሰብህን ፎቶ በመለጠፍ አካውንቱ ያንተ እንዲመስል ካደረገ በኋላ ሊያስገድልህ የሚችል ነገር ፖስት ማድረግ ምን ያህል ነውረኝነት እንደሆነ አስበው ።

የዓውራምባ ታይምሱ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ትግራይ መገንጠል አለባት የሚል አጀንዳ በማራመድ ይህን ነገር ያጠናክሩልኛል የሚላቸውን የተለያዩ ባለሃብቶችና ምሁራንን በቪዲዮ እየቀረጸ በመለጠፍ ከሱ አላማ ውጭ ያሉ ሰወችን ግን የተለያየ ካባ በመስጠት ላይ ነው።የአውራምባ ታይምሱ ዳዊት ከበደ ነው ። በነገራችን ላይ ይህ ሰው መጥፎ ነገሮችን ለማድረግ ጓደኝነትም ሆነ ውለታ እንደማይዘው ዛሬ ባደረገው ነገር ማወቅ ትችላለህ። ከዚህ ቀደምም በፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ላይ የበላበትን ወጪት ሰብሮ ክህደት የፈጸመ ሰው ነው። ይህ ሰው ፌስቡክን እያተራመሰ ነው። የትግራይን ህዝብ ከሌላው ለመነጠል የተደራጀ ስራ በመስራትና እንደ ኦህዴድ እና ብአዴን ያሉ ድርጅቶችን በማሸማቀቅ ላይ ይገኛል ። ከዋናው ኣካውንት ሌላ ለምለም ሃድጉ የሚለውን አካውንት በተለይ ለዚህ ጉዳይ የሚጠቀምበት ነው።በዚህ አካውንት በግል ፀብ የተጣላቸውን ሰወች ሰወች ፎቶ በመጠቀም ፡ ከሰወቹ አመለካከት ውጭ የሆነ ነገር በመለጠፍ ሰወቹን ከተለያዩ ብሄሮች ጋር ለማላተም እና ፈጽሞ በማያውቁት ነገር አደጋ እንዲደርስባቸው እየሞከረ ይገኛል ።እርሱ ብቻ የትግራይ ህዝብ ተቆርቋሪ ይመስል ስሙን ከዳዊት ከበደ ወደ ሴፍ ተጋሩ ላይቭስ ቀይሮ የፈለገውን ሲል ይውላል ።

ዳዊት ከበደ አውራምባ ታይምስ የተባለውን ድረገጽ የከፈተለት ብርሃኑ ነጋ እንደሆነ ታውቃለህ በድረገጹ ምርቃት ላይም ንጝግር ካደረጉ ሰወች መሃል አንዱ ታማኝ በየነ ነው መጨረሻ ላይ ግን ብርሃኑ ነጋ በመኖሪያ ቤቱ አንድ ግብዣ ያዘጋጃል ። በዚህ ቀን ከተጋበዙት ሰወች አንዱም ዳዊት ከበደ ነበር እናም ጊዜው ይመሽና ብርሃኑ ነጋ ቤት ያድራል ። ላፕቶፑን ይዞ ባለመምጣቱም ብርሃኑ ነጋ ላፕቶፑን እንዲጠቀምበት ያውሰዋል ። እናም ወዲያው በፍላሽ ላፕቶፑ ውስጥ ያሉትን መረጃዎች ኮፒ አድርጎ ወጣ። ይላሉ ዳዊት ከበደን በቅርቡ የሚያውቁት የደህንነት ሰዎች። በኢሕአዴግ ስልጣን ላይ ያሉት ባለስልጣኖች እስካሁን ድረስ አያምኑትም ። ቀረቤታ ያለው ያስመስላል እንጂ ፈጽሞ እንደዛ አይደለም ። እናም በነሱ ዘንድ ያጣውን ቀረቤታ ለማግኘት ነው እየዳከረ ያለው ። በጎን ደግሞ ከጃዋር ጋር ይሞዳሞዳል መረጃ ይሰጣል ፡ ዞር ብሎ ደግሞ ጃዋር ይገደል ብሎ በውሽት አካውንት ይጽፍና በንጹህ ሰው ያላክካል። መረጃውን ለሰጡን የድሮው አይሮፕላን ማረፊያ ጀርባ የአዲስ አበባ ደህንነት ቢሮ አባላት እናመሰግናለን። (ምንሊክ ሳልሳዊ

Source: ( mereja.com )

March,17-2018

1 thought on “ጃዋር መሐመድን በጥቁር አሜሪካዊ አስገድላለሁ ያለው ሰው ማንነት ሲጋለጥ (ምንሊክ ሳልሳዊ)

Comments are closed.