ጀዋር መሀመድ እና በቀለ ገርባ ታመው ህክምና በመከልከላቸው የረሃብ አድማ ላይ ናቸው

ጀዋር መሀመድ እና በቀለ ገርባ ታመው ህክምና በመከልከላቸው የረሃብ አድማ ላይ ናቸው
 
አቶ ጀዋር መሀመድ ስለታመመ አስቀድሞ ፍ/ቤት ባዘዘው መሰረት የግል ሃክሞቹ እንዲመጡለት መልዕክት አስተላልፎ ነበር። ይሁንና ሁለት ሃኪሞቹ በትናንትናው ዕለት ቃሊት ማረሚያ ቤት ቢመጡም ማረሚያ ቤቱ ከ 2 ሰዓት ተኩል በላይ ካቆያቸው በኋላ ከልክሎ መልሷቸዋል።
አቶ በቀለ በበኩላቸው አአራት ቀን በፊት እግራቸው አብጦ እንደሚያማቸው ቢያሳውቁም እስከዛሬ ህክምና አላገኙም። ከዚህ የተነሳ ዛሬ ከቤተሰብ ምግብ አልተቀበሉም የረሃብ አድማ ላይ በመሆናቸው ከክፍላቸው ወጥተው ቤተሰብና ጠያቂዎችን አላናገሩም። በእስር ቤቱ ያለው የህክምና ሆኔታ አጠቃላይ የታሳሪዎቹ አያያዝ እያሽቆለቆለ መሆኑን መገንዘብ ችለናል።

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.