የጉድ ሀገር ገንፎ እያደር ይፋጃል አሉ: ዶ-ር ደብረፅዮን ገ-ሚካየል የመስሪያ ቤት ዶክመንት ስርቆት ጀምረዋል

የጉድ ሀገር ገንፎ እያደር ይፋጃል አሉ: ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካየል የመስሪያ ቤት ዶክመንት ስርቆት ጀምረዋል

በአኮረፉ የህወሀት ካድሪዎች ጉትጎታና ግፊት የትግራይ ህዝብ ሰልፍ ቢወጣም ከሰልፍ ይልቅ የአዲስ አበባን የታክሲ ወረፋ ጠባቂ አስመስሏቸው ውሏል።

Via Ewentu Feleke


የጉድ ሀገር ገንፎ እያደር ይፋጃል አሉ: ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካየል የመስሪያ ቤት ዶክመንት ስርቆት ጀምረዋል

ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ዶ/ር ደብረፅዮን የትግራይ ክልል አስተዳዳሪ ሆኖ ከተሾመ ጀምሮ በሳምንት አንድ ቀን በፊት ሚኒስትር ሆኖ ስሰራበት የነበረ መስሪያ ቤት ሳይጎበኝ የቆየበት ጊዜ የለም፡፡በአሁኑ ሰዓት የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ሆና በማገልገል ላይ ያለችው ወ/ሮ ኡባ ሞሐመድ ቢትሆንም በነፃነት መስራት እንዳልቻለች ግን በተደጋጋሚ ስንገልፅ ቆይተናል፡፡ የመንግስት መኪና እንኳን ካልክሏት ለራሱ ወደ ትግራይ ክልል ይዞ ሄዷል፡፡ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ባለፈው ማክሰኞ የኢህአዴግ ስብሰባ ከተጠናቀቀ በኋላ ከምሽቱ 1፡00 አከባቢ ቀጥታ ወደ ኢትዮ ቴሌኮም ዋና መስሪያ ቤት 7ኛ ፎቅ ያመራል፡፡የበፊቱ ቢሮ እዛው ስለሆነ ቀን ቀን ወ/ሮ ኡባ መሐመድ የሚትጠቀምበትን ዶክምንትና የተለያዩ ደብዳቤዎችን ማታ ማታ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በተመሳሳይ ቁልፍ ቢሮውን ከፍቶ በመግባት ኮፒ እያደረገ ይወስዳል፡፡በጊዜ ህደት ወ/ሮ ኡባ መሐመድ ከፍተኛ ጥርጣሬ እያደረባቸው ይመጣል፡፡ወ/ሮ ኡባ መሐመድ ነገሩ ግራ ስገባት ቀን የተጠቀመችበትን ዶክመንት ማታ ማታ ምልክት እያደረገችበት መውጣት ትጀምራለች፡፡በነጋታውም ተመሳሳይ ነገር ይገጥማታል፡፡ ወ/ሮ ኡባ ከፍተኛ ጥርጣሬ ያድርባቸውና ቀን የሚጠቀሙበትን ዶክመንት ማታ ማታ ስወጡ በጠረጴዛቸው ውስጥ ቆልፈውበት ይወጣሉ፡፡አሁንም ተመሳሳይ ችግር ያጋጥማቸውና ዶክመንቶች ይጠፉባታል፡፡ይሄነ ነው እንግዲህ ወ/ሮ ኡባ መሐመድ ቀለበት ውስጥ መውደቃቸውን ያረጋገጡት፡፡ወ/ሮ ኡባ ችግሩን አይተው ዝም አላሉም፡፡ የቢሮ ቁልፍ እንዲቀየርላቸው ጥያቄ ያቀርባሉ፡፡በተጠየቀው መሰረትም የወ/ሮ ኡባ መሐመድ የቢሮ ቁልፍ ተቀየረላቸው፡፡ዶ/ር ደብረፅዮን የወ/ሮ ኡባ መሐመድ የቢሮ ቁልፍ መቀየሩን ሳይሰማ ነገሩ እንደ ዱሮ መስሎት ከምሽቱ 1፡00 ወደ ወ/ሮ ኡባ መሐመድ ቢሮ ዘው ቢሎ ለመግባት ወደዛው ይምዘገዘጋል፡፡የሴትዮዋን ቢሮም ለመክፈት ቁልፍ ያወጣና ይሞክራል፡፡ ቢሮው አልከፈት አለው፡፡ደጋግሞ ቢሞክርም መክፈት አልቻለም፡፡የቢሮው ቁልፍ መቀየሩን ያወቀው በሩ አልከፈት ሲለው ነው፡፡በዚህ ጊዜ ዶ/ር ደብረፅዮን እልህ ውስጥ ይገባና ቢሮውን በኃይል ለመክፈት ይሞክራል፡፡ ሰውየው ቢሮውን በኃይል ለመክፈት ሲሞክር የኢትዮ ቴሌኮም ጥበቃዎች ይሰሙና በቦታው ይደርሳሉ፡፡ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ቢሮ በኃይል ለመክፈት ስታገል ጥበቃዎች እጅ ከፈንጅ ያዙት፡፡ጥበቃዎቹም ምንም ድምፅ ሳያሰሙ እጅ ወደላይ አሉት፡፡ዶ/ሩም እኔ ነኝ ምን ጣፋ ቢሎ ለመደንፋት ሞከረ፡፡ጥበቃዎቹም የዋዛ አልነበሩምና የፈለገው ይሁን የቢሮ ቁልፍ በኃይል ለመክፈት ሞክረሃልና አንለቅህም አሉት፡፡የዶ/ር ደብረፅዮን ጠባቂዎች ለማገላገል ፈለጉ፡፡የኢትዮ ቴሌኮም ጠበቃ ግን እጅ አልሰጡም፡፡ክርክሩ እስከ ሌሊቱ 4፡00 ቀጥሎ የኢትዮ ቴሌኮም የጥበቃ ሰራተኞች በስተመጨረሻ ከብዙ ጭቅጭቅ በኋላ ለቀቁት፡፡ከዚያን ጊዜ በኋላ ነው ወ/ሮ ኡባ መሐመድ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያመለከቱት፡፡