ዶ/ር አብይ እና ኦቦ ለማ መገርሳ ሕወሐትን ማስጠንቀቃቸው ተሰማ

ዶ/ር አብይ እና ኦቦ ለማ መገርሳ ሕወሐትን ማስጠንቀቃቸው ተሰማ


ከሚልኪ አዱኛ

(zehabesha) –እሁድ የተጀመረው የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ ዛሬ ወይም ነገ ይጠናቀቃል ተብሎ እየተጠበቀ ነው::

በስብሰባው የኢሃዲግ ሊቀመንበር የሚሆነውን መሪ ምርጫን ጨምሮ በሌሎች የተለያዩ የከፍተኛ የፌዴራል መንግስት ስልጣኖችና ተቃማት ላይ ሪፎርም ማድረግን በተመለከተ እልህ አስጨራሽ ድርድር እና ክርክር እየተደረገ መሆኑ ታውቋል::

በትላንትናው እለት ከሞላ ጎደል በቀጣዩ የኢሃዲግ ሊ/መ እንዲሆኑ በዶ/ር አብይ ላይ ከተስማሙና ጋዜጣዊ መግለጫ ለማድረግ ጋዘጠኞች ከተጠሩ በኃላ መግለጫው ተሰርዛል:: ጋዜጠኞችም እስከማታ እደጅ ሆነው የስብሰባውን መጨረሻ ሲጠባበቁ ቆይተው በስተመጨረሻ እንዲሄዱ እንደተነገራቸው ታውቋል::

የውስጥ አዋቂ ምንጮች እንዳሉት ከሆነ ጋዜጣዊ መግለጫው የተሰረዘበት ምክኒያት ስምምነታቸውን የሚያፈርስ ነገር በህወሃቱ ዶ/ር ደብረጽዮን እንደተፈጠረ ለማወቅ ተችሏል::

ይህንንኑ ተከትሎ የኦህዴዶቹ ዶ/ር አብይ እና ኦቦ ለማ መገርሳ “በስምምነታችን መሰረት የማንቀጥል ከሆነ ከኢህአዴግ አባልነታችን እንወጣለን” በማለት ያስጠነቁ መሆኑንን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልፀውልኛል::

ይህ በመሆኑ የስብሰባው ንትርክ ዛሬም ተመልሶ የቀጠለ ሲሆን ምናልባት በድጋሚ የሚስማሙ ከሆነ በዛሬው እለት ወይንም ነገ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል::