ድፍድፍ ነዳጅ የማውጣቱ ስራ በይፋ ተጀመረ።ፖሊ ጂሲ ኤል ፔትሮሊየም ኢንቨስትመንት ኩባንያ በኦጋዴን ድፍድፍ ነዳጅ የማውጣቱን ተግባር ዛሬ በይፋ ጀምሯል።

ድፍድፍ ነዳጅ የማውጣቱ ስራ በይፋ ተጀመረ።

ፖሊ ጂሲ ኤል ፔትሮሊየም ኢንቨስትመንት ኩባንያ በኦጋዴን ድፍድፍ ነዳጅ የማውጣቱን ተግባር ዛሬ በይፋ ጀምሯል።
ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አሕመድ በትላንትናው ዕለት ከኩባንያው የስራ ኃላፊዎች ጋር በፅህፈት ቤታቸው ከመከሩ በኋላ ስራው ዛሬ እንደሚጀመር ገልፀው ነበር።
የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ድፍድፍ ነዳጅ የማውጣቱ ስራ ተጀምሯል።
በሙከራ ደረጃ በቀን 450 በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ የማውጣቱ ስራ ይከናወናል።
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ትናንት ይፋ ባደረጉት መሰረት ዛሬ በሙከራደረጃ በሚጀመረው ድፍድፍ ነዳጅ ለዓለም ገበያ ሲቀርብ በዛሬው የዓለም የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ መሰረት ኢትዮጵያ በየወሩ ከ28 ሚሊዮን ብር በላይ፤ በአመት ደግሞ 344 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘት ያስችላታል።
በፌቨን ተሾመ

Source: Ethiopian Broadcasting Corporation