ድንገተኛው የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኢትዮጵያ ጉብኝት

ድንገተኛው የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኢትዮጵያ ጉብኝት

የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጉብኝቶች ከዚህ ቀደምም ከመቐለ እስከ አዲስ አበባ አከራካሪ ናቸው። በተለይ የኮሮና ወረርሽኝ ሁለቱንም አገራት ባሰጋበት ኢትዮጵያም ከአዲስ ዙር የፖለቲካ ቀውስ አፋፍ በቆመችበት በዚህ ወቅት ኢሳያስ እና ከፍተኛ ሹማምንቶቻቸው ወደ አዲስ አበባ ያመሩበት ገፊ ምክንያት አልተብራራም
ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ትናንት ወደ አዲስ አበባ ያመሩት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በዛሬው ዕለት በኦሮሚያ ክልል የተገነባውን የመቂ-ዝዋይ መስኖ መርቀው ከፍተዋል።

ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ በተጨማሪ ውጭ ጉዳይ ምኒስትሩ ኦስማን ሳሌሕ እንዲሁም የፕሬዝዳንቱ አማካሪ የማነ ገብረአብ አብረው አዲስ አበባ ናቸው። በኢትዮጵያ፣ በኤርትራ እንዲሁም በተቀረው ዓለም የኮሮና ወረርሽኝ እጅግ ባሰጋበት ወቅት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ከፍተኛ ሹማምንቶቻቸው ወደ አዲስ አበባ ለምን አቀኑ የሚለው ጥያቄ ቀጥተኛ መልስ አላገኘም።

ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ “ለሁለት ቀናት በሚያደርጉት ቆይታ፣ በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት እናደርጋለን። የዓለም አቀፋ ማኅበረሰብ አካል በመሆናችን ስለ ተጋፈጥናቸው ፈታኝ ሁኔታዎች እንወያይባቸዋለን” ብለዋል።

የኤርትራ ማስታወቂያ ምኒስትር የማነ ገብረ መስቀል በትናንትናው ዕለት እንዳሉት ሁለቱ መሪዎች ከሚመክሩባቸው መካከል የበረሐ አንበጣ እና የኮሮና ወረርሽኝ ጉዳዮች ይገኙበታል።

የኢሳያስ ጉብኝቶች ከዚህ ቀደምም ከመቐለ እስከ አዲስ አበባ አከራካሪ ናቸው። ሁለቱ አገሮች እርቅ አወረዱ ቢባልም አሁንም መፍትሔ ያልተበጀላላቸው ጉዳዮች አሏቸው። በአሁኑ የኢሳያስ ጉብኝት ኢትዮጵያውያን ምን አሉ?

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

እሸቴ በቀለ


Paartileen mormituu gaazexeessitoota miti, kan wal gahiii boruutif har’a itti himtu.


Ethiopia: ውዝግብ – የንጉሡ ምላሽ ለጃዋር እና ለልደቱ | Nigusu Thilahun on Jawar Mohammed and Lidetu Ayalew