“ድል ለዴሞክራሲ” የሚሆነው፥ከዘመን ጋር ሲዘመን ነው-Sadik Ahmed

“ድል ለዴሞክራሲ” የሚሆነው፥ከዘመን ጋር ሲዘመን ነው

Sadik Ahmed

ሳዲቅ ይህንን ለምን ትጽፋለህ ብሎ የኔን motive ጥያቄ ምልክት ውስጥ የሚያስገባ ይኖራል።በተለያዩ መድረኮችም ላይ ሆነ በbroadcast ስራዎቼ ላይ ስለ እስክንድር ነጋ ነጻነት ብዙ ብያለሁ። ህወሃት እንደ አሁኑ ከመንኮታኮቷ በፊት ሴረኛውንና የጨቋኞች ቁንጮ የሆነውን ስብሃት ነጋን ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ስጋፈጠው “ነጻ እስክንድር ነጋ!” ስል ድምጼን አስተጋብቻለሁ።ይህንን ያስተዋለ ill-intentioned criticism እንድሌለኝ መረዳት ይችላል የሚል ግምት አለኝ።

ታሪካዊና ወቅታዊ ጉዳዮችን የሚያስቃኝ ጽሁፍ ጽፋለሁ ብዬ እያሰብኩ ሳለ ጋዜጠኛ Fatuma Nuryea ትላንት ከእስክንድር ጋር የተጻጻፈቸውን ስትልክልኝ ነገሮችን ቆም ብዬ ለማሰብ ተገደድኩ። (ይህንን በሌላ ጽሁፍ ቃኘዋለህ)

እስክንድር በተለምዶ በፎቶ ላይ በሚያሳየው gesture እነ ጀነራል መንግስቱ ነዋይና ገርማሜ ነዋይ መስዋእት በሆኑለት የለውጥ ጉዞ በ1966 የወደቀውን የዘውድ ስርአት አወዳሽ መሆኑን ይጠቁማል። ይህ ከዘመን ጋር ያልዘመነ እሳቤ እንደምን “ድል ለዲሞክራሲ” ከሚለው የትግል መስመር ጋር ይዋሃዳል የሚል ጥያቄን ያጭርብኛል።ተመሳሳይ በሆነ መልኩ ያ የዘውድ ስርአት ቅዱስ ከለውጡ በኋላ ያሉት መንግስታት እርኩስ መሆናቸውን ለማሳየት ሚዛን ላይ የሚቀመጡ ትርክቶች አሉ።የቀኝ ዘመም እሳቤን አቀንቃኝ የሆኑ ስብስቦች በራሳቸው የህይወት ዘመንና ትውልድ መካከል ታሪክን ሰርተው ማለፍ ሲችሉ በትላንቱ የታሪክ ካቴና እራሳቸውን ይጠፍራሉ። ነገሩ ስላቅ ቢመስልም የስነልቦናቸው መሰረት ግን ሰፊ ጥናት ያሻዋል።

የ1966ቱ አብዮት ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በነቂስ ተሳትፈውበታል።በአጼ-ሐይለስላሴ ዘመነ መንግስት ሙስሊሞች ይደርስባቸው የነበረው በደል በጣሙን አስከፊ እንደነበር ታሪክ ሊሽረው የማይችለው እውነታም ነው። ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በዘመኑ #በኢትዮጵያ #የሚገኙ #ሙስሊሞች መባላቸው እንዲቀር ታግለዋል።የትግላቸውን ፍሬ ከለውጡ በኋላ በማፈስ #ኢትዮጵያውያን #ሙስሊሞች ተብለው፣ ሶስት አመት በአሎቻቸው ብሄራዊ በአል ሆነው እነሆ ዛሬ ላይ ደርሰዋል።

እስክንድር የዲሞክራሲ አቀንቃኝ ነው የሚል ግምት አለ።ዲሞክራሲ ደግሞ #የኋላው #ከሌለ #የፊቱ የለም በሚል ዘልማዳዊ ገመድ ታስሮ መኖርን ይጻረራል። ዲሞክራሲ የሌሎች ሐሳብን በራስ ሐሳብ ላይ መቀየጥን (compromiseን) ይሻል።ስለዚህ በማንኛውም መልኩ ቢሆን ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች #በኢትዮጵያ #የሚገኙ #ሙስሊሞች ከተባሉ ታሪካዊ ቁስላቸው ላይ ጨው መነስነስ መስሎ ስለሚሰማቸው ይንገፈገፋሉ።

በሚዲያ ላይ ነጭ አሜሪካውያን “ኤን ወርድን” ቢጠቀሙ ምን ይከሰታል የሚለውን ንጽጽር እናስቀምጥ።#የኦሮሞ ህዝብ መጠራት የማይፈልግበት ስም በሚዲያ ላይ ጋዜጠኞች ቢጠቀሙበት ምን ይከሰታል?ይህንንም እንመልከት። እኔኑ ጨምሮ በሚሊዮን የምንቆጠር ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች አባቶቻችን በመስዋእትነት ያስቀሩትን መጠሪያ የኛ ትውልድ ሲደግመው ታጋሾች የምንሆንበት አቅም ባይኖረንም ሚዛናዊነትን ማስቀደሙም ተገቢ ነው።ስለዚህ ሌሎች ሚዲያዎች ይህንን አርመውታል እስክንድርም ይህንን ስተት አርሞ ወደፊት መጓዙ ተገቢ ነው። ስተትን ማረም ታላቅነት ነው።

“Victory for democracy” shall be, with the age of the age.

Why don’t you think of this, why are you going to have a sign for the people of the moctive question. It has been a lot of people who have been killed by the broadcast. I just got my voice out. I have a lot of people who don’t understand this. I have a lot of it.

I am surprised that I am looking for a text that has been given to the Ethiopian and the current and the current. I have been able to do this in a while.

The people who have been killed by the people of the people who have been killed by the people of Ethiopia. This is the one that has been given to the age of the age of the age of Ethiopia. There are the people who are trying to change the people who are not able to change the land of the people. The right of the right, the people of the country, and the generation of the people will be saved.

1966 of the revolution of the ethiopians who have been killed by the people of the world, the government of the people, the government of Ethiopia has been killed by the people of Ethiopia. There is a national holiday, three years in the local national holiday.

There is a lot of people who don’t have a democracy. the democracy is also the #one who has been killed by the people of the people who have been killed by the people of others. They will be able to do it. The people of Ethiopia are #in #Ethiopia #Muslims #Muslims. Tell the people who are going to make salt of the people in the country.

What are the people in the dea saying that they are not allowed to the people of the people who are saying that they are in the name of the people. Let’s see this. It is fair to get rid of others in the country. We will not be able to do this. It is fair to get rid of others.