Site icon Kichuu

ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ፤ ከዴሞክራያዊ መግባባት ውጭ ይታሰባልን ?

ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ፤ ከዴሞክራያዊ መግባባት ውጭ ይታሰባልን ?

ከፊዳ ቱምሳ, ኅዳር 2011

ዛሬ ኢትዩጵያ ዴሞክራሲያዊ ሽግግር ለማድረግ በግድርድር ላይ ትገኛለች። ይህ ሽግግር አንዳንዶች እንደሚያስቡት ቀላል አይደለም። ምናልባትም ኢትዩጵያ እስከ ዛሬ ያልገጠማትና ልትወጣበት ወደማትችለው መቀመቅ ለመግባት የተዘጋጀችበት ወቅት ሊሆን እንደሚችል የተረዱ ጥቂቶች ብቻ ናቸው።እነኝህ ሁኔታዉን በአግባ የተረዱ ወገኖች ደግሞ ሀሳባቸውን ለማካፈል እንዳይችሉ ድምጻቸው በባለጊዜዎች ጩሀት ተዳፍኖአል። ምናልባት አድማጭ ባገኝ፡ እናም የኔንም ጩሀት ብትሰሙ ብዬ ይህችን በጣም አጭር ነጥብ እንድናስብበት ለማቅረብ ዳዳሁ።

እስቲ ሁለት ዓመት ባነስ ጊዜ የሀገራዊ ምርጫ ይ ደረጋል ብለን እናስብ፡ የምርጫ ቦርዱም ተቀይሮ ፤ የምርጫ ህጉም ተቀይሮ፤ የፍትህ ስርዓቱም በምርጫ የሚነሱ ጉዳዩች መዳኘት የሚችል አቋም ኖሮት ….. ወዘተ .. ይህ ምርጫ ይካሄዳል እንበል። ዛሬ ላይ ቆሞ ያለምንም መዳዳት ማመልከት የሚቻለው በኦሮሚያ ኦዴፖ ፣ በአማራ ክአዴፖ፤ በደቡብ ደህዴን የመሸነፍ እጣ ፋንታ እንደሚገጥማቸው ነው። በተአምር ወይም በማጭበርበር ካልሆነ በስተቀር ይሄ የማይቀር ጉዳይ ነው። ይህንን ለማስቀረት ኦዴፓም አዴፖም ደህዴንም እየሰሩ ያሉት ስራ አይታየኝም …….. ትንሽም ቢሆን በዚህ ስራ ላይ ብቅ ጥልቅ የሚል ስራ ለመስራት እየሞከረ ያለው የኦዴፖ አካል ብቻ ነው። ይሳካለት አይሳካለት ወደፊት የምናየው ቢሆንም በኦሮሚያ ውስጥ ካሉ የፖለቲከ ድርጅቶች ጋር መጠነኛ መግባባት እየመሰረተ ያለ ይመስላል። በሌላ በኩል ይሄንን በጎ ጅምር ኦዴፖ ከኦነግ ጋር ያለው ግንኙነት ይፈታተነዋል።

የእነኚህ ዛሬ በአመራር ላይ ያሉ ሀይላት መሸነፍ ሳይሆን፤ ችግሩ አሸናፊዎች ከሆ ኑ ሀግ ሪ ቱ ን ወዴት መውሰድ እንደሚችሉ መተንበይ ላይ ነው;። ለብዙ አመታት በውጪ ሀገራት ዲሞክራሲያዊ በሆነ መድረክ ላይ መወያየትና መግባባት (መስማማት እያልኩ አይደለም) ያልቻሉ አካላት እንዴት አድርገው ሀገርን በጋራ መምራት እንደሚችሉ ከዚሁ መገመት ይቻላል። ዛሬ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ መተለም የሚቻለው እነኚህ ደርጅቶች ሀገርን በጋራ ለመምራት የሚያስችል የጋራ አቋማት platform ለማበጀት የሚያሰችላቸው ቁመና የላቸውም፤። ከዚህ በመነሳታ መተንበይ የሚቻለው ምናልባትም ከዚህ ቀደም አይተን የማናውቀውን ሀገርን አደጋ ላይ የሚጥል መንግስት አልባነት ሊመጣ እንደሚችል ነው”።

እስቲ ይህን በዝርዝር እንመልከት

 1. ለምርጫ የሚደረግ ቅስቀሳ ህዝብን ያቀራርባል ወይስ ያራርቃል በየክልሉ የሚደረግ የፖለቲካ ፉክክሮች ያለምንም ድንበር የሚካሄድ ከሆነ ህዝብን ለማቀራረብ ከሚደረገው ጉዞ ይልቅ ህዝቡን የመበተን እንደሚሆን መረዳት ይገባል። የተከፋፈለ፤ አንድነት የሌለው ህዝብ በክልልም ሆነ በሀገር ደረጃ ለሚፈለግ ተከታታይነት ያለው እድገት ያለመኖርና ከሱ ጋር ተያይዘው ለሚመጡ ችግሮች መንገድ ከፋች ነው።
 2. የክልል መንግስት የሚገጥማቸው ችግሮች ዛሬ በየክልሉ የተነሱ ጥያቄዎች የምርጫ አጀንዳ ሆነው የሚ ቀርቡ በመሆናቸው፤ በዚህ ዙሪያ የህዝብ ድጋፍ አግኝተው የሚመረጡ ወገኖች የገቡትን ቃል ለማሟላት የሚያደርጉት ጉዞ ለዚህ ሽግግር ፈታኝ ይሆናል። ለምሳሌ በደበብ የተለያዩ ዜጎች የክልል እውቅና ጥያቄ….. በኦሮሚያ የራስን እድል በራስ የመወሰን ጥያቄ…. በአማራ የወልቃይት ጸገዴ ጥያቄ .. ወዘተ ማንሳት ይቻላል።
 3. በመግባባት የጋራ መንግሰት ለማቋቀቋም የሚችሉ ፓርቲዎች ይኖራሉን? አስካሁን እየታየ ካለው ጉዞ መገንዘብ የምንችለው ክልላዊ ፓርቲዎች ከሌሎች ክልላዊ ፓርቲዎች ይቅርና ባሉበት ክልልም ካሉ ሌሎች ፓርቲዎች ጋር ክልላቸውን በጋራ የማስተዳደር ፤ የክልላችውን ጥቅሞች በፌደራል ደረጃ በጋራ የማስከበር አላማዎች ላይ ሲወያዩ አይታይም። ከእንግዲህ የአንድ የፖለቲካ ድርጅት በክልል ምክር ቤት ብቸኛ ገዢ መሆን እንደሚያበቃ ብዙዎች አልተረዱም። በጋራ የሚቀረጹ ፖሊሲዎች አስፈላጊነት ሁሉም ወገን የሚግባቡባቸው ጉዳዩች ከመኖራቸው እንደሚመንጭ አልተረዱትም። ብዙዎች ዛሬም ግባችን አንድ መሆኑን ፤ ልዩነቶቻችን ወደዚያ ግብ የሚያደርሱን መንገዶች ምርጫ መሆናቸውን አላስተዋሉም። ይህ የማያስጨንቀው ሰው ካለ … ነገ የሚመጣው ጥፋትና ችግር ላለማየት አይኑን የጨፈነ ሰው… ወይም ማየት የተሳነው ነው፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ ገና ከዛሬ ሀምሳ አመት በፊት የተነሱ የልዩነት ጉዳዩች መቅዋጫ አልተበጀላቸውም። ለብዙ ዘመናት ያልተነጋገረ ፖለትከኛ በበዛበት ሀገር… የጋራ የሚባል አቅዋም ባልተለመደበት ምድር… በብዙ መሰረታዊ ጉዳዮች የተራራቁ አስተሳሰብ ያላቸው ፓርቲዎች ባሉበት ሁነታ ይቅርና እጅግ የሚቀራረቡ አጀንዳ ያላቸው ግን አብረው ለመስራት ካልቻሉበት የፖለቲካ አካላት ባሉበት ሁኔታ ከምርጫ የሚወጣ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ሊኖር ይችላ ማለት ዘበት ነው፡፡

በዛሬይትዋ ኢትዩጵያ ይህንን ችግር ከሚያዋስሰቡት ጉዳዩች አንዱ ራሳ ቸ ውን ሀገራዊ ፓርቲዎች ብለው የሚጠሩ ፓርቲዎችን እውነተኛ ሀገራዊ ፓርቲዎች ያለመሆን ነው። አብዛኛው ራሱን መላውን ኢትዩጵያ እወክላለሁ ብሎ የሚጠራ ፓርቲ፤ ከፍ ሲል የአንድ ብሔር ድርጅት ነው። ከዚያም ካለፈ ራሱን ከብሔሮች በላይ አድርጎ ለመቆጠር የሚዳዳው የከተሜዎች ፓርቲ ነው። እናም ሀገር አቀፍ ራእይ የሰነቀ ተጨባጩን ሁኔታ የገመገመ ሳይሆን … በራሱ አይን፤ በራሱ መልክ ኢትዩጵያን ለማቅረጽ የሚዳዳው ወገነ ነው ። ከከተሞች የለፈ ተስፋ ያለው፤ ሀገርን የሚዳስስ ራእይ ያለው ባለመሆኑ ለግጭት እንጂ ለመፍትሄ የሚሰለፍ ለመሆን ይቸግረዋል፡፡

ብዙ አስቸጋሪ ውስብሰብ በሆነው የኢትዩጵያ የፖለቲካ መስክ አሁን ባለው ሁኔታ በሚቀጥለው ምርጫ ወደኋላ እንጂ ወደፊት መራመድ እንደማይቻል መተንበይ አስቸጋሪ አይሆንም፤። ዋናው ቁምነገር ይሄ እንዳይሆን ምን መደረግ አለበት? አጣዳፊ ተግባራት ምንድናቸው? ብሎ የልሆን ይችላል ትተን ላይ ተመስርቶ መካሄድ ያለባቸው ተግባራዊ ሀሳቦች መሰንዘር ከሁላቻንም የሚጠበቅ ጉዳይ መስሎ ስለታየኝ የሚከተሉትን ሀሳብ ለማቅረብ ተነሳሁ።

 1. በክልሎች ደረጃ ማድረግ የሚገባቸው መሪው ፓርቲ ሃላፊነት በመውሰድ በየክልሉ የሚገኘ የፖለሪካ ፓርቲዎች በክልላቸው ስለሚደረገው ምርጫ ምርጫውን ተከትሎ ቢያንስ ለሚቀጥሉት ሁለት አስርተ አመታት የጋራ ግቦች ላይ መስማማት እዚህ ላይ ግቦች ጋር አንዲሆኑ እንደሚያዳርስ ሳይሆን እንደደረሰ የሚመች ግቦች ላይ መነጋገር እና መግባባት አስፈላጊ የሚያደርገው ምርጫ በማለት ላይ ሳይሆን ወደዚያ ግቦች ባሉ አማራጭ ጎዳናዎች ላይ እንደሆነ ያደርጋልና ነው፣ ከዚህ ጋር ተያይዞ ቢያንስ ለሚቀጥሉት 10 አመታት በክልሉ ስላምን ማስፈን ይቻል ዘንድ ዛሬ ያሉመ ነገም የሚፈጠር የፖለቲካ ፓርቲዎች ራሳቸውን የሚገዙበትን ማለፍ የሚገባችውንና ማንሳት የማይገባቸውን ዝርዝርና ጉዳ ዩን በመዳሰስ ከምርጫ ቅስቀሳ ውጪ መሆን የሚገባቸው ጉዳዩች በፓርላማ መሀል ያሉ ግንኙነቶች የሚገዙበትን የግንኙነት ስርዓት ላይ መስማማት እንዲቻል ተከታታይነት ያለው ውየይት መጀመር ያለባቸው አሁን ይመስላል ይህ ውየይይት ሲደረግና መግባባት ሳይኖር የሚደረግ የምርጫ ቅስቅሳ ህዝብን —— ለዲሞክራሲያዊ ተግባሮችን መንግስት እንደወሰደ የሚጋብዝ ሊሆን ይችላል ልታስቡበት ይገባል
 2. በሀገር አቀፍ ደረጃ ቀዳሚ ተግባር – ዛሬ በሀገር ውስጥ የሚገኙ የፓለቲካ ፓርቲዎች ብዙ ናቸው። በዚህ ላይ የተጨመሩ ከውጪ ሀገር ወደ ሀገር ቤት የተመለሱ ፓርቲዎችና በየቀኑ እየተቋቋሙ ያሉ ፓርቲዎች መታየት የጀመሩበት ሁኔታ ውስጥ እንገኛለን ፡፡ህግ ባለበት ሀገር እንደመኖራችን ሁሉ፤ ሁሉም ድረጅቶች በህግ መሰረት ተመዝግ በ ውና ህጋዊ እውቅና አግኝተው መብታችውን ብቻ ሳይሆን፤ መብት ይዞት የሚመጣውን ግዴታም ለመወጣት ብቃት ያላቸው መሆኑን ማረጋግጥ አስፈላጊ ይሆናል፡፡በዚህ ረገድ ከውጪ ገብተው ያለምንም ህጋዊ እውቅና ከሀገሪቱ ህግ ማ እቀፍ ውጪ የሚደረጉት እንቅስቃሴ ለአደጋ እንዳይጋብዝ ሁሉም በህጋዊው መንገድ ህጋዊ እውቅና እንዲኖራቸው ማድረግ አስፈላጊ ነው ።

  የለዉጡ መንግስትና ፤ይህንን የሽግግር ጊዜ ለመምራት ታሪካዊ ሃላፊነት የ ወ ደ ቀበት አካል በእርግጥ መጪው ዘመን የሠላምና የሽግግር እንዲሆን ከፈለገ የሚከተሉትን ጉዳዮች ቢከውኑ ታሪክ የማይረሳው ውለታ ለህዝቦችና ለሀገሪቱ ውለዋል ማለት እንችላለን።

 3. ሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች (የክልል፤ ራሳቸውን ሀገር አቀፍ የሚሉና የገዥውን ፓርቲ ጨምሮ) ቢያንስ ከሶስት እስከ ስድስት ወር የሚዘልቅ የሀገሪቱን ችግሮች የሚዳስስ የፓርቲዎቹን የውድድር (የፉክክር) ሜዳ ወሰን የሚያበጅ የመግባባት ተከታታይ ውይይት እንዲያደርጉ ሁኔታዎችን ቢያመቻች፤
 4. የዚህ ተከታታይ ውይይት (ያልተቆራረጠ ውይይት) ግቦች
  1. ሀሉም የፖለቲካ ድርጅቶች በሚቀጥለው 20/25 ዓመታት ውስጥ ኢትዩጵያ ልትደርስባቸው የሚገቡ ግብአቶች ላይ መግባባት፤ በፖለቲካ በኢኮኖሚ በማህበራዊ ኑሮ ደረጃ ረገድ ማየት የምንፈልገው ለውጥ ላይ የጋራ ግንዛቤ መፍጠር፤ የፖ ለቲካ ፓርቲዎች የትግል አቅጣጫ ወደነዚህ ግቦች የምንደርስበትን ጎዳና ላይ ያሉ ልዩነቶች ብቻ እንዲሆኑ ለማድረግ መጣር።
  2. ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች በአጭር ጊዜ መወሰድ ባለባቸው እ ርም ጃ ዎ ች ላይ መግባባት። በተለይም የታሪክ ጠባሳዎችን በሚሽሩ ጉዳዩች ላይ መግባባት ላይ ለመድረስ መቻል።
  3. የፖ ለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ወቅት ማለፍ የማይገባቸውን ሀገ ር ንና ህዝብን ለአደጋ የሚዳርጉ ወደ ቀጣይ ግጭት የሚያስገቡ ጉዳዩችን በመለየት ራስን ወደማቀብ ወይም ህጋዊ ሽፋን (ክልከላ) እንዲሰጠው ማድረግ።
  4. እጅግ የተፈረካከሰ በአቋም ምንም ያህል ልዩነት የማይታይባቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች በትብብር መልክ ወደ አንድነት እንድስባስቡ የፓርቲ መሪዎች ጥረት የሚያደርጉበትን መንገድ ማበጀትና ለሌሎችም ተግባራት በዚህ /በሶስት/ ስድስት ወር ውይይት ወቅት መጠናቀቅ ይችላሉ ።

ይህ ወቅት በመንግስት ፤ ከፓርቲዎች ውይይትና መግባባት በሚነሱ ሃሳቦች ላይ በመመርኮዝ ለመጪው ግዜ የሚያገለግሉ መስረታዊ የሆኑ የተቋም ለውጦች/ማሻሻያዎች ወይም የአዲስ ተቋማት ምስረታ ወቅት የሚሆንበት ቢሆን …. ለኢትዩጵያ የወደፊት የፖለቲካ ሂደት መስረት ተጣለ ማለት እንችላለን፡፡

ይህ ሳይሆን ቀርቶ አሁን ባለንበት ተቋም /አቋም ወደ ምርጫ ለመሄድ ብንሞክር ከትርፉ ጥፋቱ ያመዝናል።

እስቲ እናስበው አዲስ አበባ /ፊንፊኔ ላይ የአዲስ አበቤዎች ፓርቲ ነኝ የሚለው ግንቦት አሸንፎ ፤ ፊንፊኔ በቄሮ ተከባ… በል እስቲ አርሰህ አብላት ሲባል

ማየት፤ የምንፈልግ እንኖራለን ማለት ይቻል ይሆን? የአማራ ክልል በአማራ ብሔርተኛ ወገን ቁጥጥር ስር ሆኖ … ወልቃይትና ጸገዴን ለማስመለስ ጦርንት ሲያውጅ ማየት እንመርጣለንን? ኦሮሚያንና ሌሎችም እንዲሁ እርስ በእርስ መነጋገር ባልቻሉ ሃይላት የቀን ተቀን ፍትግያ መቆየታቸውን እንመርጣለንን? እነኝህ በየክ ሉ የሚያሸንፉ ሀይ ላት በመባባት መንግስት ለመመስረት ይቻላቸዋልን? መልሱን ምንነት እና የሚያስከትለዉን ጉዳት እንወያይ በት።

በኢትዮጵያ የፖለቲካ ጫወታው ሜዳ በፖለቲካ ድርጅቶች መግባባት ድንበር ካልተበጀለት ችግሮችን ወደሚያወሳስብ ዘመን እየተጉዋዝን ነው። ይህ ደግሞ ኢትዩጵያን ያለመንግስት አስቀርቶ ወደ ዳግም አምባገነን መንግስት መጋበዝና ወደ መጣንብት መመለስ ምርጫችን እንዲሆነ በራሳችን ላይ መወሰን ልሆንብንም ይችላል፡፡

እናም ጊዜው አሁን ነው። እውነት ዴሞክራሲና ፍትህ ነጻነትና እኩልነት በሀገሪቱ እንዲሰፍን ከተፈለገ የፖለቲካ ማህበረረሰቡ የዚህን ጨወታ ሜዳ ድንበር ማካለ

፤ ማድረግ የምንችለውንና የማንችለው፤ ማድረግ የሚገባንና የማይገባንን …… ከታሪክ አውቀን የማናስታውሰውና የምናሰታውሰውን (የምንረሳው ታሪክ ማለት አይደልም ) በሚገባ በውይይትና በመግባባታ መመለስ ይገባል። ያለዚያ ታሪክ ራሷን ትደግማለች እንዳሉ

66 ትንና 83 ትን በበለጠ መልኩ የጥፋት ዘመን ከፈታችን ያታያል። ጥፋትን መከ ላ ከል የምንችለው እኛው ነን።

ዛሬ ካልሆነ ደግሞ ለነገ የምንለው አይሆንም …….የታሪክ አደራ የወደቀባቸው መገኖች ከዚህ አደጋ እንዲታቀቡን በሀሳብ በተግባር እንርዳቸው።

Exit mobile version