የሰሜን አሜሪካን የእግር ኳስና ባህል ዝግዝጅ ላይ ጠ-ሚ ዶ-ር አብይ አህመድ ለመገኘት ጥያቄ እንዳቀረቡ ሰምተናል::ዋና አላማው ዲያስፖራውን መከፋፈልና ለሴኔት ይቀርባል የተባለውን #SR168 ውሳኔ መቀልበስ ነው።

የሰሜን አሜሪካን የእግር ኳስና ባህል ዝግዝጅ ላይ ጠ-ሚ ዶ-ር አብይ አህመድ ለመገኘት ጥያቄ እንዳቀረቡ ሰምተናል::ዋና አላማው ዲያስፖራውን መከፋፈልና ለሴኔት ይቀርባል የተባለውን #SR168 ውሳኔ መቀልበስ ነው።

#NO #PM_ABIY ESFNA Dallas Sport and Cultural Festival
አብይ ዳላስ የሚመጣ ከሆነ ፕሮግራሞቹን እስከመሰረዝ ከዛም በላይ ትልቅ ተቃውሞ እስክመቀስቀስ ይደርሳል። በቀላሉ አንላቀቅም። ይህ ጉዞ ዋና አላማው ዲያስፖራውን መከፋፈልና ለሴኔት ይቀርባል የተባለውን #SR168 ውሳኔ መቀልበስ ነው። ትግሉ ይቀጥላል። በኢትዮጵያ የተረጋገጠ ለውጥ እስኪመጣ ሕዝባዊው ትግል አይቆምም ። በጮሌ ምላስና በጥገናዊ ለውጥ አንታለልም ።ዶ/ር አብይ አህመድ በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን የስፖርት በዓል ላይ ለመገኘት ጥያቄ ማቅረባቸውን ሰማሁ። በተመሳሳይም የአውሮፓውን የኢትዮጵያውያን ፌደሬሽንንም በደብዳቤ እንደጠየቁ ይነገራል። አስገራሚ ነገር ነው። መጠየቃቸው ባልከፋ። ወገናቸውን ለማነጋጋር በዚህ ደረጃ መፈለጋቸው የሚወገዝ አይደለም። ነገር ግን ምን አስበው ነው? ውጭ ላለው ኢትዮጵያዊ እስከአሁን በሀገር ቤት ከተናገሩት የተለየ ምን ሊነግሩት ነው? ቢያንስ የተወሰኑ በህዝብ ዘንድ የሚጠየቁ እርምጃዎችን ከወሰዱና መንገዱን ካለሳለሱ በኋላ ቢሆን አይሻልም? መድረክ እንዲህ የጠማቸው ለምን ይሆን?

የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን የስፖርት ፌደሬሽን የራሱን መተዳደሪያ ደንብ ጥሶ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥያቄ ይቀበላል የሚል ግምት የለኝም። ፌዴሬሽኑን ለሁለት ከፍሎት ላለፉት 7 ዓመታት የዘለቀው ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳን በክብር እንግድነት በጋበዘ ወቅት ከህወሀት ደጋፊ የፌዴሬሽኑ አመራሮች በኩል ተቃውሞ በመቅረቡ ነው። እንደመፍትሄም የፖለቲካ ሰው ከየትኛውም ወገን መጋበዝ አይቻልም የሚል መመሪያ ደንቡ ውስጥ አስቀምጦ ነው የቆየው። በዚህ ዓመትም አቶ በቀለ ገርባን ለመጋበዝ ታስቦ ይህ መመሪያቸው እንደከለከለቸው ሰምቼአለሁ። እስክንድር ነጋ ጋዜጠኛ በመሆኑ ሊጋበዝ እንድታሰብ ታውቋል።

ታዲያ ዶ/ር አብይ ያቀረቡትን ”በእንግድነት ጋብዙኝ” ጥያቄን ፌዴሬሽኑ ምን መልስ ሊሰጥ ይሆን? መመሪያውን ጥሶ ጥያቄአቸውን ሊቀበል? ወይስ ለደንቡ ተገዝቶ በአቋሙ መጽናት? ይህ ፌዴሬሽን በዚህ ውሳኔ ከሁለት ዳግም እንዳይከፈል ስጋት እንዳለ ይሰማል። ዶ/ር አብይ አውቀውትም ይሁን ሳያውቁት የኢትዮጵያውያን መሰባሰቢያ የሆነውን መድረክ ከአደጋ ጋር አፋጠውታል። ዲያስፖራውን ለማዳከም ህወሀት ብዙ ሙከራ አድርጓል። አልተሳካለትም። ዶ/ር አብይ ይህን ያደርጉታል ብዬ አልጠብቅም። ካደረጉት ግን አካሄዳቸውን ብቻ ሳይሆን ያደነቅነውንና ያጨበጭብልነትን አመጣጣቸውንም በጥያቄ እንድንመረምረው የሚያደርገን ይሆናል።

ዶ/ር አብይ መድረክ አብዝተዋል። በእምነት ህይወታቸው የቀሰሙትን የማነቃቂያ ንግግር ክህሎታቸውን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ጉዟቸው አጥበቅው እየተጠቀሙበት ነው። ሆኖም እንዲህ መድረክ የሚያስጠና ውጤት አስመዝግበዋል ብዬ አላምንም። ስራው መቅደም ነበረበት። ቢያንስ ደጋፊዎቻቸው አደረጉ ብለው ነጥብ ከሚሰጧቸው አንዳንድ እርምጃዎች ተሻግረው መሰረታዊ ለውጥ የሚያመጡ እርምጃዎችን በሂደት ደረጃ ሳያሳዩ በየመድረኩ መከሰትና፡ ጋብዙኝ ማለት የሚደገፍ ውሳኔ አይደለም።

ትላንት በኤምባሲ በተጠራ ስብሰባ ላይ ኢሳትና አባይ ሚዲያ እንዳይገቡ ተደርገዋል። ለኢትዮጵያውያን በሙሉ በተጠራው መድረክ ላይ ለምን እንዲህ ዓይነት ክልከላ እንዳስፈለገ ግራ ያጋባል። የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አስተዳደር የለውጥ ምልክት ማሳየት ካለበት ከዚህ መጀምር ይኖርበታል። ኤምባሲው ባልተለመደ መልኩ ደጋፊና አባል ብሎ ልዩነት ሳያደርግ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ያቀረበው ጥሪ የሚበረታታ ነበር። ሆኖም ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ ነገር ሆኖ የህወሀት ሰዎች ከተጣበቀባቸው አባዜ ባለመላቀቃቸው ታጥቦ ጭቃ ሆነው አርፈዋል። ኤምባሲው በር ላይ የሚገባና የሚወጣ የሚለዩ መሆናቸውን ዳግም አሳይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በነሃሴ ወደ አሜሪካ ይመጣሉ በሚል በዋሽንግተን ዲሲ ሽር ጉድ እያሉ ያሉ ግለሰቦችንም ካየን የተለመደው የካድሬ ግርግር ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ መገመት አይከብድም። ከስርዓቱ ጋር በጥቅም የተሳሰሩ ሰዎች ኮሚቴ አቋቁመው ለአቀባበል ወገባቸውን አጥብቀው እየሰሩ ነው። እንደምንሰማው ጠቅላይ ሚኒስትሩም እየመረጡ አንዳንድ አክቲቪስቶች ጋር ስልክ ደውለው እያነጋገሩ ነው። መለየቱ ለምን እንዳስፈለገ አይገባኝም። ለመፍትሄና ለዘላቂ ለውጥ ከልብ የተነሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑ እንዲህ ዓይነት ከፋፋይ መንገድ ተመራጭ አይደለም።

መሪነታቸው ለሁሉም ኢትዮጵያዊ በእኩል መሆኑን ማሳየት የእሳቸው ግዴታ ነው። እዚህ ያለውን አንድነት በማንኮታኮት ላይ የተመሰረተውን የህወሀት ታክቲክ ዶ/ር አብይ እንዳይከተሉት የቅርብ ወዳጆጃቸው ቢመክሯቸው ጥሩ ነው። ኢህአዴግ ከሚባለው የግዑዛን ስብስብ እሳቸውና ቲም ለማ እንደሚለዩ በዚያም የኢትዮጵያን ህዝብ ድጋፍ እንደሸመቱ አይጠፋቸውም ብዬ አስባለሁ። አሁንም በኢህ አዴግ ዜማና ቅኝት እንድንደንስ እየፈለጉ ከሆነ ብዙም ርቀት የሚወስዳቸው አይሆንም። እሳቸው እንዳሉትም ይህ ትውልድ በአዲስ አስተሳሰብ እንጂ ባረጀው ሊመራ አይፈቅድም።

በአጭሩ መድረክ የመጠማታቸውን ያህል ለተግባራዊ መሰረታዊ ለውጦች ቅድሚያ ሰጥተው እንዲተጉ ያስፈልጋል። ዙሪያቸው ተኮልኩለው አላሰራ ያሉ የህወሀት እንቅፋቶችን በሂደት እየጠራረጉ በቃላቸው የዘመሩትን ኢትዮጵያዊ ለውጥ በተግባር እንዲያሳዩ ይጠበቃሉ። ያን ጊዜ በአንደበታቸው ብቻ ሳይሆን በውጤታቸው የሚማረክ ከጥግ እስከ ጥግ ያገኛሉ።
#ግንቦት20የጨለማቀን
Mesay Mekonnen


የሰሜን አሜሪካን የእግር ኳስና ባህል ዝግዝጅ #ESFNA ላይ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ለመገኘት በኤንባሲ በኩል ጥያቄ እንዳቀረቡ ሰምተናል:: ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ በመጀመሪያ ደረጃ ከዲያስፖራው ጋር ለመነጋገርም ሆነ ለመካከር ማድረግ የሚገባቸው ጥቂት ነገሮችን እንሆ

1. በወታደራዊ አገዛዝ ያለውን አስቸኳይ ግዜ አዋጅ ማንሳት

2. መከላኪያውንና ደህነቱን ከህወሀት ውጪ ማድረግ

3. እስካሁን በተለይ በኦሮሚያና አማራ ክልሎችና በሌሎችም ክልሌች ቁጥራቸው ከ 4000 በላይ የፖለቲካ እስረኞችን መፍታት ጋዜጠኞችን ጨምሮ

4. በውጪ በስደት ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞችንና ፖለቲከኞችን ወደ ሀገራቸው ገብተው እንዲሰሩ መፍቀድና ተፎካካሪ ፖርቲ ሆነው እንዲሰሩና መብታቸው እንዲጠበቅ ማድረግ::

5. ኮከብ ያለበትን የወያነ ባዲራ ኮከቡን ማንሳትና ምናልባት ይህን ሁሉ አድርገው በኳስ ዝግጅቱ ላይ ቢገኙ ኮከብ ያለበትን ባንዲራ አለመያዝና በተቃራኒው ኮከብ የሌለበትን ባዲራ መያዝ

6. በየከተማው ያሉ የኢትዮጵያ ኤንባሲዎች አንተ ተቃዋሚ ነህ በማለት የሀገራቸውን ፖስፖርት ለተከለከሉት ኢትዮጵያዊያን የሀገራቸውን ፖስፖርት እንዲሰጣቸው ማድረግ::

7. ማንኛውም ዲያስፖራ በተለይ ተቃዋሚው በኤንባሲ ሊደረጉለት የሚገባውን መብቶቹን እንዲደረግለት መወሰን::

8. ብሔራዊ የመግባባትና እርቅን ማድረግ::

9. በኦሮሚያና በአማራ ክልል በዚህ አምስት አመት ውስጥ መለተፈፀሙት የሰው ልጆች ሞት ምክንያት የሆኑትን የፀትታ አካላትና ሀላፊዎች ለፍርድ ማቅረብ

10. የአንድ ዘር የበላይነት የሌለበት እውነተኛ ዲሞክሪያሳዊ ስረአትን ማስፈን እና አንቀፅ 39 ኝን ከህገ መንግስቱ ላይ ማንሳት::

11. ለአመታት የኢትዮጵያን ንብረትና ገንዘብን ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ ሲበዘብዙና ሲዘርፉ የነበሩትን የህወሀት ሰዎች ለፍርድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል:: ይህ ከሆነ እኛ የመቃወም ሱስ የለብንም እኛም ድምፃችን ላፕቶፖች እንዲሁም ኪሳችንና ጣታችን ያርፈል:: እሳቸውም ዝግጅቱ ላይ መገኘት ይችላሉ:: ለሀገራችን ጥቅም ስንል ገንዘባችንንም በህጋዊ መንገድ በባንክ መላክ እንጀምራለን::

ኢትዮጵያዊነት ይለምልም ጎጠኝነት ይውደም


ESAT DC Daily News Sat 26 May 2018


Seife Nebelbal Radio, May 25, 2018 – Oromo news in Amharic