ይድረስ በብልፅግና ውስጥ ላላቹ የኦሮሞ ባለስልጣናት በሙሉ:

ይድረስ በብልፅግና ውስጥ ላላቹ የኦሮሞ ባለስልጣናት በሙሉ

ጠ/ሚንስትሩና ደጋፊዎቹ እንደሚፈልጉት አሁን የታሰሩ እስረኞች በሙሉ በእስር ቤት ኑሯቸውን ቢያደርጉ ፣ ቄሮው ዝም ቢል ፣ደያስፖራው ኦሮሞ ድምፁን ቢያጠፋ፣የኦሮሞው ሚድያ በሙሉ አላየውም አልሰማውም ቢል ፣ የኦሮሞው አርቲስት ፓለቲካን መዝፈን ቢተው ፣ የኦሮሞ ምሁራን በኢትዮጵያ ፖለቲካ ምሁራዊ አስተያየታቸውን መስጠት ቢያቆሙ ምን የሚሆን ይመስላችኃል ?

ዛሬ “ሀጫሉ ሞቷል፣ጃዋር ይቀራል ” ያለው ቡድን በቀጥታ የሽመልስ አብዲሳን ቢሮ ወሮ ሽመልስን በጥፊ ብሎ ከፊንፊኔ ያባርራል ። በዛ ግዜ ጠ/ሚንስትሩ እንኳን ሽመልስን እራሱን ስለማዳኑም መገመት ይከብዳል

እንደኔ እንደኔ የሁሉም የኦሮሞ ባለስልጣናት የስልጣን ምንጭ “ፅንፈኛና ዘረኛ” የተባለው የኦሮሞው ክፍል እንጂ የጠ/ሚንስትሩ ኢትዮጵያ አይደለችም ። ዛሬ በሀጫሉ ሞት የሚደሰተውን ለጀዋር ሞት የሚመኘው ሁሉ ቀጣይ ኢላማው አንተ ነህና ጭልጥ ብለህ በጠቅላይ ሚንስትሩ ስብከት አትስከር ። እንደ ጋሪ ፈረስ በአንድ አቅጣጫ ማየትህን ትተህ የኢትዮጵያ ኢምፓየር ወዴት እየሄደች ነው የሚለውን መርምር ፣ ነገ ብገፋ “ለምን ?” ብሎ የሚነሳልኝ ማነው ብለህ ጠይቅ ፣ ለራስህ ስትል ምርኩዝህን አትግፋ ፣ ዛሬ “ዘረኛ ወይም ፅንፈኛ ” ብለህ እያሳደድከው ያለው ቡድን የትላንትም የነገም የስልጣን ምንጭና ዋስትናቹ ነው ።

የታሰሩትን በማስፈታት ፣ ከቄሮው ጋር በመምከር፣ ከደያስፖራው ጋር በመስራት ፣ የኦሮሞ ድምፅ የሆኑ ሚድያዎችን የበለጠ በማጠናከር፣አርቲስቱን በመደገፍ፣የምሁራኑን ምክር በማዳመጥ በኢትዮጵያ ኢምፓየር ፓወር ባላንሳቹን አስተካክሉ ወደዳቹም ጠላቹም ፖለቲካው ጠ/ሚንስትሩ እንደሚለው የሀሳብ ሳይሆን የዘር ነው ። የዘር ፓለቲካ አንፈልግም ሲሉ ምን ማለታቸው እንደሆነ ይግባቹ !

Dábessá Gemelal