ይድረስ ለሃገረ ኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴሮች!!Ministry of Education Ethiopia Ministry of Science and Higher Education – Ethiopia

ይድረስ ለሃገረ ኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴሮች!!
Ministry of Education Ethiopia Ministry of Science and Higher Education – Ethiopia

እንኳን ኣሁን ላለንበት ዘመን #ዘመነ_መሳፍንት አደረሳችሁ። ዛሬ በጋዜጣዊ መግለጫችሁ ያወጣችሁት መግለጫ የሚመለከተው ለምታስተዳድሩትን ክልል ኣዲስ ኣበባ ብቻ እንደሆነ እምነቴ ነው። ሌሎች ክልሎችን መቸም ኣይመለከትም ምክኒያቱም ከማንም ጋር አልተማከራችሁም።

ኣሁን ባለው የክልሎች የራስ ገዝ ኣስተዳደርና ሕገ መንግስት መሰረት፡ ክልሎች በራሳቸው ቋንቋ የመናገር፣ የመማር፣ የመፃፍ፣ ቋንቋቸውን ባህላቸውን የማሳደግ፣ የማዳበር፣ የማስፋፋት፣ እና የመንከባከብ ሙሉ መብት ኣላቸው። ይሄ ደሞ በትምህርት ካልተገለፀ ምንም ትርጉም የለውም።

ስለዚህ፣ ክልሎች ከላይ የተገለፀውን መብታቸውን ለማስከበር በሚያመቻቸው መልኩ የትምህርት ስርዓታቸውን የመቅረፅና የመተግበር መብት ኣላቸው። ከፌደራል ስርዓቱ ጋር የሚያስተሳስራቸውን የጋራ መግባቢያ ቋንቋ በጋራ ይወስናሉ /ልጆቻቸውን ኦሮምኛ ይሁን ኣማርኛ ወይ እንግሊዘኛ ወይ ሌላ የተመረጠ ቋንቋ እንዲያውቁ ማድረጉን ለክልሎች ተውላቸው/።

ክልሎች ወይም እያንዳንዱ ብሄረሰብ ኣቅሙ እስካለው እና እስከፈቀደ ድረስ ትምህርትን እስከ የመጨረሻው የትምህርት እርከን ድረስ በራሱ ቋንቋ መማር አለበት። በዚህ መልኩም ሊበረታታ ሊታገዝ ይገባዋል። በውሰት ቋንቋ አሁን ዓለም የደረሰበትን የእውቀትና ስልጣኔ ደረጃ እንኳንስ ልንደርስበት ቀርቶ ጭላንጭልም ማየት ተስኖናል።

ክልሎች ዜጎቻቸውን በራሳቸው ቋንቋ ሂሳብ፣ ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ፣ ስነ ሂወት ሳይንስ፣ ስነ ምድር ሳይንስ፣ ህብረተሰብ ሳይንስ፣ ፖለቲካ ሳይንስ፡ የጤና ሳይንስ፣ ኢንጂነሪንግ፣ ቴክኖሎጂ፣ የሂሳብ ኣያያዝ፣ የባንክና የገንዘብ ስርዓት፣ የኢንቨስትመንት ስርዓት፣ የምጣኔ ሃብት ሳይንስ፣ የሃይል፣ የማዕድን፣ የጠፈር ሳይንስ፣ የሕግ ስርዓትና ኣስተዳደር፣ የሰው ሰራሽ ኢንተለጀንስ ሳይንስ፣ ደቂቅ ረቂቅ ቴክኖሎጂ፣ ወዘተ ወዘተ የማስተማር እድላቸውን አሁን መጠቀም መጀመር አለባቸው።

በውሰት ቋንቋ ህዝቡንና ሃገሩን የቀየረ፣ ያሰለጠነ፣ ያሳደገ ሃገር አንድም የለም።

ይልቅ ቀልዳችሁን ተውትና ድረ ገፃችሁን ወቅታዊ አድርጉት። የያዘው መረጃ ያረጀ ያፈጀ ነው። ለምን ይመስላችኋል?????

የፊንፊኔ ቄሮዎች ማህበር