ይቺ ባንዲራ : አብዛኛው ኦሮሞ ልብ ውስጥ ያለ ምልክት ነው- Mahlet Fantahun

ይቺ ባንዲራ: አብዛኛው ኦሮሞ ልብ ውስጥ ያለ ምልክት ነው- Mahlet Fantahun

 

ይቺ ባንዲራ

አብዛኛው ኦሮሞ ልብ ውስጥ ያለ ምልክት ነው። በድሮው ኢህአዴግ ዘመን ባንዲራው እቤታቸው የሆነ ቦታ ሻንጣቸው ውስጥ ሳይቀር ተገኝቷል እየተባለ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው የረጅም አመት የእስር ፍርድ ይቀጡ ነበር። ሊያስሯቸው ሲፈልጉ አሳሪዎቹ አካላት ባንዲራውን ይዘው መጥተው ከቤታቸው እንደተገኘ አስመስሎ አስቀምጦ ለቀረበባቸው የሽብር ክስ እንደማስረጃ የተወሰደባቸውም ግለሰቦች በግሌ አውቃለው። እቤት ተገኝቷል በሚል ሰበብ ብቻ አይደለም የኦነግ ባንዲራ የሚያሳስረው፤ የባንዲራው ስእል በስልክ ላይ ከተገኘ እንዲሁም ባንዲራው ያለበት ክሊፕ በሞባይል ወይም በላፕቶፕ የተገኘባቸውም የሽብር ክስ ሰለባ ሆነዋል። የኦነግ ባንዲራ ምስል የያዙ ክሊፖች እንደ ማስረጃ ቀርበው በእነ አቶ ጉርሜሳ አያና መዝገብ የተከሰሱ ግለሰቦች ማስረጃ በሚቀርብበት ጊዜ በችሎት የታደምን ሁሉ ቁጭ ብለን ያየን አይተነዋል። እንዲሁም ሆኖ ተቃውሞዎች በሚኖሩበት ቦታ ሁሉ ባንዲራውን ይዞ መውጣት አንደ የተቃውሞ ምልክት ያገለግል ነበር። እያገለገለም ነው። በባንዲራው ሰበብ ህይወታቸውን ያጡ፣ አካለ ጎዶሎ የሆኑ፣ ያሉበት የማይታወቅ፣ በእስር እድሜያቸውን ያሳለፉ፣ የተንገላቱ …. ቤቱ ይቁጠራቸው።
አሁን ደግሞ ጊዜው የለውጥ ነው ተብሎ ኦነግም ከሽብርተኛ ድርጅት ስለተሰረዘ ያው ባንዲራውም በህግ ማስቀጣቱ በቀረበት ሰአት አዲስ አበባ ላይ እንዲታይ የማይፈልጉ ሰዎች መኖራቸው በጣም ነው ሚያሳዝነው። የሚያሳፍረው። ታዲያ መንግስትን ብቻ አፋኝ እና ጨቋኝ የምንለው ለምንድን ነው? እንደመር ተደምረናል ጂኒጃንካ በምንልበት ዘመን ከኛ ውጪ የሆነን አመለካከት የያዘ ባንዲራ እንዲህ አምርሮ መጥላት ለማየት አለመፈለግ ምን ይባላል? የእውነት ያሳፍራል።
★★★★★★

ማንኛውንም ሃሳብ የያዙ ባንዲራዎች/ አርማዎች እርስ በርስ ሳይገፋፉ በየትኛውም የሃገራችን ክፍል አንድ ላይ መቆም የሚችሉበትን ጊዜ እናፍቃለው።

Via Mahlet Fantahun

A guide to Oromo Freedom


Oromoo Freedom Fighters in Oromia jungles


After a teaching stint Addis Ababa University (in the College of Law and Governance) and sojourn in 10 regional universities in Ethiopia (Haramayaa University, Jimma University, Wallagga University, Wallo University  Madda Walabu University, Bule Hora University, Dembidollo University, Ambo University, Mekelle University, Adama Science and Technology University), I returned to Michigan. I thought I’d missing being home. But home had overtaken me to Michigan, where the Oromo Community Association of Michigan (OCAM) is holding its annual summer celebration. We are everywhere. You just have to get used to it.