ይህ የሾለከ ሰነድ የፒፒን ወቅታዊ ሁኔታ በተወሰነ መልኩ ያሳያል። በአዴፓና ኦዴፓ መሃል ሽኩቻው በርትቷል።

ይህ የሾለከ ሰነድ የፒፒን ወቅታዊ ሁኔታ በተወሰነ መልኩ ያሳያል። በአዴፓና ኦዴፓ መሃል ሽኩቻው በርትቷል።

ኦዴፓ በውስጣዊ መድረኮች በሌሎች የክልል አመራሮች በኩል የአዴፓን አመራሮች ያስወቅጣል። ባለፈው በተካሄደው የሁለት ቀናት የማኮ ስብሰባ ከኦዲፒ ኦቦ ሞገስ ኢደኤና የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚን እንዲመራ የተመደበው ግለሰብ ብቻ ሲናገሩ በርካታ የሰላ ትችቶች ወደ አዴፓ የወረወሩት የሌሎች ክልሎች የፒፒ አመራሮች ነበሩ። በዚህ የተበሳጨው የአዴፓ አመራር በአብን አመራሮች ፤ በአክቲቪስቶችና በሚቆጣጠራቸው የሚዲያ ተቋማት በኩል ኦዲፒን እያደባየ ይገኛል። አዴፓ የተወሰኑ የኦዲፒ አመራሮችን “ኦነጋዊ አስተሳሰብ ያለቸው” በሚል በስም ዘርዝሮ ከነዚህ ጋር በውህድ ፓርቲነት መቀጠል ያስቸግረኛል የሚል አቋም ለመያዝ እየተውተረተረ ነው። ጥያቄው አብይ አህመድ እንደተለመደው እነዚህን የኦዲፒ አመራሮች “በሬ ሆይ ሳሩን አይተህ ገደሉን ሳታይ” ብሎ ይቀረጥፋቸዋል ወይስ ከብቸኛ ማህበራዊ መሰረቱ (የአማራ ክልል) ጋር መላተምን ይመርጣል ነው። ጊዜ ይፈታዋል።