ይህ ባንዲራ የኦሮሞ ገዳ ስርዓትና የወል መገለጫ ምልክት/ሰንደቅ በመዲናች ሲናኝ ቀላል ሊመስል ይችላል ነገር ግን ለነፃነት በተከፈለ እጅግ ውድ ዋጋ የመጣ ድል ነው።

ከፍ አለ!

ይህ ባንዲራ የኦሮሞ ገዳ ስርዓትና የወል መገለጫ ምልክት/ሰንደቅ በመዲናች ሲናኝ ቀላል ሊመስል ይችላል ነገር ግን ለነፃነት በተከፈለ እጅግ ውድ ዋጋ የመጣ ድል ነው።

የባንድራው ቀለማት

ጥቁሩ ቀለም የዋቃን /የፈጣሪን አለመመርመርና አለመታወቅ፣ ረቂቅነት፣ ሁሉን ቻይነትና ሰፊነትን ማመላከት ብቻ ሳይሆን ኦሮሞ ስለፈጣሪው ያለውን ጥልቅ መረዳትና ግንዛቤ ጭምር የሚያመላክት ትዕምርት ነው።

ቀዩ ቀለም በማህበረሰቡ የተከፈለን መስዋዕትነት፣ የተሰበረን አጥንትና ደም፣ መብሰልና መጎምራትን ምድራዊ ፈተናንና የታለፈውን አስቸጋሪ መንገድና ውጣ-ውረዶች ይወክላል።

ነጬ ቀለም ደግሞ የሰላም፣ የነፃነት፣ የፍፁምነት፣ የፍፅምናና የውጤት መገለጫ ነው።

የገዳ ስርአት ኦሮሞ ከዋቃ/ከፈጣሪው ጋር፣ ከተፈጥሮ ጋር፣ ከሌሎች ማህበረሰቦችና ከራሱ ጋር እራሱን እንዴት አስማምቶ መኖር እንዳለበት ከሞራል፣ ከስርዓት፣ ከስነምግባርና ከፍልስፍና አንፃር ከውልደት እስከ ሞት ብሎም እስከቀጣዩ መንፈሳዊ ህይወት የሚያስተምር ሃገረሰባዊ እሴት ነው።

እሬቻ ደግሞ ለዋቃ ምስጋና የሚቀርብበት ክብረ በዓል ነው።

ጥቅል ጭብጡ ይሄ ሲሆን ባንድራው በየአደባባዩ በመሰቀሉና በፊንፊኔ ሰማይ ላይ በመናኘቱ ምክንያት እንዲሁ ላብ ላብ፣ ብርድ ብርድ፣ የሚንቀጠቀጥና መደንበር መደንበር የሚለውና በያዘው ራስ ምታት ምክንያት እየነሰረው ያለ አካል አለ። ይህ ደግሞ የሚመነጨው ከአሃዳዊና ጨፍላቂ አስተሳሰብ ነውና ምንም ማድረግ አይቻልም!!

በዚያው ልክ ደግሞ በብዝሃነትና በእኩልነት ብሎም በፍትህ ለሚያምን ሙሉ የሆነ የሆነ ሰው ወይም ቡድን ይህ አጋጣሚ የአብሮነት ማጠንከርያ እና ደስታን የሚፈጥር በዓል ነው።

መልካም ዋዜማ!

በላይ ባይሳ
መስከረም 23/2012 ዓ.ም

Belay Bayisa!