ይህ ለግላጋ ታዳጊ ጫላ ኤቢሳ ይባላል። ታዳጊው በ1997 ዓም በምስራቅ ሀረርጌ አወዳይ ከተማ ከአባቱ ኤቢሳ እኖሮ እና ከእናቱ ሽኩሪ አብዱራዛቅ ተወለደ።

ይህ ለግላጋ ታዳጊ ጫላ ኤቢሳ ይባላል። ታዳጊው በ1997 ዓም በምስራቅ ሀረርጌ አወዳይ ከተማ ከአባቱ ኤቢሳ እኖሮ እና ከእናቱ ሽኩሪ አብዱራዛቅ ተወለደ።
 
አባቱ ለአምስት አመታት በኦህዴድ (የአሁኑ ኦሮሚያ ብልጽግና) ታስሮ የአካልና የስና አእምሮ ጉዳት ከደረሰበት ቦኋላ ከእስሩ ሳያገግም ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል። እናቱም ምንም ገቢ ስላልነበራ ልጆቿን ማሳደግ አቅቷት ወደ ሱማሌ ላንድ ተሰደደች፣በአሁኑ ጊዜ የት እንዳለች አይታወቅም።
ጫላ ላንጌ ከተማ ከምትኖረው አያቱና ሃሮዋጫ ካለችዉ አክስቱ ጋር እየኖረ እስከ አምስተኛ ከተማረ ቦኋላ የአባቱ ቤተሰቦች ወደምገኙት ቀሌም ወለጋ በመሄድ በአሁኑ ጊዜ ስምንተኛ ክፍል እየተማረ ይገኛል።
 
ጫላ ከአጎቱ ጋር ዳሌ ሳዲ ወራዳ ሃሮ ሳቡ ከተማ እየኖረ እያለ የወረዳዉ አስተዳዳርና ጻጥታ ሀላፊ ኮማንደር አሸናፍ ዱላ በጉልበት አፍኖ ማንም ቤተሰብ ባልሰማበት የ16 አመት ልጅ ለዉትድርና መልምሎ ወደ ማሰልጠኛ ልኳል።
ህጻናትን ለውትድርና መመልመል ክልክል እንደሆነ ኢትዮጵያ ከፈረመቻቸዉ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ መረዳት ይቻላል።
በመሆኑም የሰብአዊ መብት ተከረካሪዎች ይህንን የአትዮድያ መንግስት የሰብአዊ መብት ጥሰትን እንድያጋልጡና በጉልበት ታፍነው የተወሰዱ ታዳጊዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው እንድመለሱ ተፅዕኖ እንዲያደርጉ ቤተሰቦቹ ይማጸናሉ።Military