ይህም የአብይ ፖለቲካዊ ድራማ ነው። በርሱ ቤት “ከለማ ጋር ሰላም ነን”

Above Single Post

For Your Iinformation 👉 ይህም የአብይ ፖለቲካዊ ድራማ ነው። በርሱ ቤት “ከለማ ጋር ሰላም ነን” የምትል የሀሰት ፖለቲካዊ መልዕክት ማስተላለፉ ነው። የኦዲፒ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ከሰሞኑ በውህደት ጉዳይ ላይ ስብሰባ አድርጎ ነበር።
በዚህም የኦቦ ለማ ቲም ውህደቱን ባለመቀበሉ ፓርቲው የውስጥ አንድነቱ ለሁለት ተከፍሎ ነበር ስብሰባውን ያጠናቀቀው። ይህም The Guardian በተሰኘው አለም አቀፍ ሚድያ ራሱ በመዘገብ ላይ ነበር። ስለዚህ ይህ ነገር ለዶ/ር ዐቢይ ስጋት ሆኖበት ስላለ ድራማ በመስራትም የተካነ ሰው ስለሆነ ይህችን ድራማ ለሰፊው እና ሞኙ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው ያስተላለፈው። ከመጋረጃው ጀርባ ያለውን እውነት ግን ሁላችንም የምናውቀው ነው። ኦቦ ለማ መገርሳ በዶ/ር ዐቢይ ለሚድያዎች እንኳን መግለጫ እንዳይሰጥ ተከልክሎ ነው ያለው። ሁሉንም ችሎ ያለው የዚህች ሀገር ፖለቲካዊ አንድነት እንዳይናጋ በማሰብ ነው።

ይህ ሁሉ ሆኖ እኔ አሁንም ቢሆን በኦቦ ለማ መገርሳ እተማመናለሁ። ድንገት የኦዲፒ እና የኢህአዴግ ሊቀመንበርነትን ተረክቦ ሀገራችንን ሲመራ የምናይበት ቀን ቅርብ ነው።

Haweni Dhabessa
መንግስታዊ ድራማ እያየን ያለንበት ሁኔታ ነው ያለው።
ይህ መንግስት ከቀዳማዊ ኃ/ስላሴ መንግስት ጋር በብዙ ይመሳሰላል። ድግስ ይወዳል። ህዝቦች በተለያዩ አካባቢዎች በጦርነት፣ በረሀብ እና በኑሮ ውድነት እየታረዙ፣ የሀገር መሪው ግን በዋና ከተማዋ በየቀኑ ማለት በሚቻል መልኩ ድግስ እና ክብረ በዐል ያዘጋጃል። ኧረ ባካችሁ ድግሱን የህዝባችን መሠረታዊ ጥያቄ ከተመለሰ በኃላ እናድርገው?


 

Below Single Post

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.