ያምርብናል- “ኢትዮጵያን ወደ ቀደመ ክብሯ እንመልሳት!”

ያምርብናል- “ኢትዮጵያን ወደ ቀደመ ክብሯ እንመልሳት!”

ትርጉም፡- “ያምርብናል ባዮች” ማለት ባዮችን እንጂ ሌላዉን ግለሰብ፣ እምነት፣ ቡድን፣ ጎሳ ወይም ህዝብን አይጨምርም!

እንደዚያ ያምርብናል ባዮች “ኢትዮጵያን ወደ ቀደመ ክብሯ እንመልሳት!” ሲሉን በወቅቱ የቀደመ ክብራችን የአሁኑ ምናችን እንደሆነ እና እንዳልሆነ ተናገርን። አሁን የደረስንበት አንዳንድ ሆኔታዎቻችንን ከቀድሞ አንዳንድ ሁኔታዎቻችን ጋር እናስተያይ

እንደማሳያነት የሃይማኖታችንን ጉዳይ እንመልከት። በቀድሞ ስርዓት ሃይማኖት (እንደ ተቋም) ስርዓተ-መንግስት (theocracy) ነበረ። ጦርነት እንኳን በሃይማኖታዊ ስርዓት ይታጀብ ነበር።

አሁን በሃይማኖት ጉዳይ የዘመነ የፖለቲካ ዓለም የሚከተለዉ የሃይማኖትና የመንግስት መለያየትን (secularism) ነዉ። አሁን ስራ ላይ ያለዉ የኛ ሕገመንግስትም በአንቀጽ 11፣ የመንግስትና የሃይማኖት መለያየት፣ በማለት እንደ አንድ የሕገመንግስቱ መሰረታዊ መርህ ተደንግጓል። አሁን ያለዉ የመንግስት ስርዓት ይህን የሕገመንግስቱን መርህ በመጣስ የሃይማኖት መሪዎችን የመንግስት እና የእምነት ስራዎችን በፈረቃ ያሰራል። የሃይማኖት መሪ ቀን ቢሮ ተቀምጦ የህዝብን ሚስጥር ሲሰበሰብ ዉሎ ማታ በእምነት ስፍራ ተገኝቶ ያንኑን ሚስጥር እንደ ትንቢት ይሰብካል። ሲመሽ በእምነት ስም መሬትን ከገበሬ ቀምቶ፣ ጧት ቢሮ ገብቶ ሰነድ ይሰራል ወይም ያሰራል።

እና ኢትዮጵያ ወደ ቀደመ ክብሯ ስትመለስ፣

1. ሃይማኖትና መንግስት የፖለቲከኞች (theocratic politicians) ሁለቱ እግሮች ይሆናሉ፣
2. የሃይማኖት ተዋህዶ የፖለቲካ ዉህደትን ያስተምራል፣
3. አንዱ ህዝብ እንደ “የተመረጠ ህዝብ (chosen people)” ሌለኛዉ ደግም “አሸባሪ፣ መንጋ፣ … (heretic people)” ተብሎ ይሰየማሉ፣
4. የአንዱ ክልል መሬት ገነት (paradise) የሌላዉ መሬት ደግሞ ሲዖል (hell) ተብሎ ይለያሉ፣
5. የዓለም ህዝብ ችግሮች መፍቻ ስርዓት የሆነዉ ፌዴራሊዝም እየተተቸ የተሻለ አማራጭ ስርዓት ግን አይቀርብም።

እንደ ቀደመ ወይም እንደ አሁኑ፣ እንደዚያ ወይም እንደዚህም አያምርባቸዉም። ዳግም መወለድ ያስፈልጋቸዋል!

Betru Dibaba

1 Comment

  1. There seems only one and one effective solution if the country has to continue to exist in its current form, and if there is any hope to democratize it. The church must refrain from interfering in politics and ensure that its flag and the flag of certain political parties be differentiated. Otherwise nation nationalities, who are members to the church are exploited into advancing political agendas of certain group just due to their membership to the church. Either the Ethiopian Orthodox church has to give up the green, yellow and red flag or the political parties using it must find alternatives. There should be no hide and seek drama. If the Ethiopian Orthodox church or any other religious institutions fail to separate themselves from the political parties or partisan politics, nation nationalities whose interests are not represented by the political parties which the church is affiliated to must stop and think about their options. Nation nationalities, beware; “in politics, being deceived is no excuse”!

    OA

Comments are closed.