የ460 ሺህ ካሬ መሬት ጉዳይ: ሚዲያዎች ይህን ጉዳይ ቢመረምሩ ብዙ ጉድ የሚያወጡ ይመስለኛል

የ460 ሺህ ካሬ መሬት ጉዳይ: ሚዲያዎች ይህን ጉዳይ ቢመረምሩ ብዙ ጉድ የሚያወጡ ይመስለኛል

የ460 ሺህ ካሬ መሬት ጉዳይ…ይህን ዶክመንት ሰው ልኮልኝ አየሁት። ነገሩ እንዲህ ነው። ይህ መሬት ‘በቀድሞ ዘመን’ በኢንቨስትመንት ስም ከገበሬዎች ተነጥቆ ነበር። ባለፈው አመት ገበሬዎቹ በፍርድ ቤት ከሰው አሸንፈው መሬቱ ተመለሰላቸው። በአክሲዮን ተደረጅተውም ማልማት ጀመሩ። በመሃል የክፍለ ከተማው አስተዳደር ካሳ የተከፍለበት እና ወደ መሬት ባንክ የተዛወረ ነው በማለት የአክሲዮኑን ታፔላዎች ነቃቅሎ መሬቱን እየሸነሸነ ለሌሎች ማከፋፈል ይጀምራል። አሁንም ገበሬዎቹ ፍርድቤት ሄደው እንዳሸነፉ ሰነዱ ያሳያል።
ይህ ነገር ጥያቄ ያጭራል።

1) ) በፍርድ ቤት ክርክር ሲካሂድበት የቆየን እና ውሳኔ ያገኘን ጉዳይ መንግስት የማያውቀው ይመስል የመንግስት ሚዲያዎች ለምን በድብቅ የተካሄደ የመሬት ዘረፋ እና ማጫበርበር አስመስለው ዘገቡት?

2) ፖሊስ ይህንን በፍርድቤት እልባት ያገኘን ጉዳይ ለምን ከኢዝሂ በፊት እንደማያውቀው እና አሁን ገና የደረሰበት ወንጀል አስመስሎ አቀረበ?

ሚዲያዎች ይህን ጉዳይ ቢመረምሩ ብዙ ጉድ የሚያወጡ ይመስለኛል